አባቶች ስለ ትግሬዎች ጸልዩ!
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
አባቶች ስለ ትግሬዎች ጸልዩ! Muluken Tesfaw
[ካልተሳሳትኩ] ባለፈው ጥር አካባቢ ይመስለኛል ብሔራዊ ካፌ ከዶክተር ያእቆብ ኃይለ ማርያም ጋር ስለ አገራችን መጻኢ እጣ ፈንታ ስናወራ አሁን ያለውን የሕወሓት ዘረኝነት ሳስብ እንቅልፍ አይወስደኝም አሉኝ፡፡ ዶክተር ያቆብ በሩዋንዳ የነበረውን የዘር ጭፍጨፋ በቅርበት የተከታተሉ ሰው በመሆናቸው በፍጅቱ ዋዜማ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ካገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በማመሳሰል እጅግ ይጨነቁ ነበር፤ የጉዳዩን አሳሳቢነት በመገንዘብ እኔም በቀለም ቀንድ ጋዜጣ ሰፊ ሽፋን ሰጥቼው ነበር፡፡ የዶክተር ያቆብ ስጋት አሁን ላይ የብዙዎች ስጋት መሆኑን መገንዘብ ከባድ አይደለም፡፡ እኔም የሚሰማ አንድም እንኳ ቢኖር በማለት ይህችን ጦማር ከተብኩ፡፡
ወያኔ ትግራይን ብቸኛ የአገሪቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ሕዝቡን ደግሞ በዘረኝነት እና በፍቅረ ንዋይ አሳብዶ የአገሪቱ አንደኛ ደረጃ ዜጋ እንዲሆኑ ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ሌት ተቀን ሠራ፡፡ ባለሥልጣን -ትግሬ፣ አስመጭና ላኪ -ትግሬ፣ ኮንትሮባንድ ነጋዴ- ትግሬ፣ ደላላ -ትግሬ፣ ኮንትራክተር -ትግሬ፣ አየር መንገድ የትግሬ፣ ፋብሪካ – የትግሬ፣ አዲስ የሥራ መደብ- የትግሬ፣ ሀብት የሚዘረፈው- ለትግሬ፣ አዋጅ የሚወጣው- በትግሬ፣ የሚገድለው- ትግሬ፣ ማእከላዊ የሚገርፈው – ትግሬ፣ የሚያስረው- ትግሬ፣ ኢምባሲው ሁሉ -የትግሬ…. ነው፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያን የሚመለከት ነገር በሞላ ‹‹በ-››፣ ‹‹የ-›› ወይም ‹‹- ን›› የመሳሰሉ ቅጥያዎችን በማስከተልና በመቅደም ‹‹ትግሬ›› የሚለው ቃል ይመጣል፡፡ በእኛ አገር ለመኖር የትግሬ ፈቃድ ያስፈልጋል፤ ለመቀበርም ቢሆን፡፡ ቤተ መቅደስ ለመግባት ወይም ከእግዚአብሔር ጋር ለመነጋገርም ቢሆን በትግሬ በኩል እንዲሆን ያልተደረገ ነገር የለም፡፡ በአገሪቱ በሙሉ በሚጨፈጨፉ ዜጎች ጀርባ ወይ ትግሬ ነው ወይም በትግሬ ትእዛዝ ነው፡፡ ገድለውም የሚያወግዙ ትግሬዎች ናቸው፡፡ እኛ እንገደላለን፤ እነርሱ ይገድላሉ፡፡ እኛ ሞተንም አስከሬናችን ማግኘት አንችልም፤ እነርሱ ገድለውም ይረግማሉ፡፡ መገናኛ ብዙሃኑም የትግሬ ነው፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ የትግሬ ያልሆነ የለም፡፡ ዳኛውም፣ ቀሚውም፣ ሕግ አውጪውም፣ ሕግ አስከባሪውም፣ ሕግ ተርጓሚውም … ትግሬ ነው፡፡
በዐማራና በኦሮሚያ አስከሬን እንቆጥራለን፤ በትግራይ ፋብሪካ ይመረቃል፡፡ የእኛ እናቶች ሀዘን ተቀምጠዋል፤ የትግሬ እናቶች ዳንኪራ ይደበድባሉ፡፡ እኛ ማቅ ለብሰን ጎዳና ላይ ለማልቀስ ተከለከልን እነርሱ በኢምባሲዎችና በቤተ መንግሥት ይጨፍራሉ፡፡ የእኛ ዘመዶች በርሀብ አንጀታቸው ታጥፏል፤ የእነርሱ ዘመዶች በቁንጣን ተይዘዋል፡፡ የእኛ መንገዶች ላይ የዘመዶቻችን ደም ያፈሳሉ፤ በእነርሱ መንገዶች ላይ ውኃ ውኃ የመሠሉ መኪናዎችን ይዘው ፍስስ ይላሉ፡፡ ብዙ ሊባል ይችላል፤ ልቦና ላለው ግን ይበቃል፡፡ ግፍን ሁሉ የሚሠራ የአንድ ጎሳ አባላት ሆነው የሚገፋው ግን ሌላው ሕዝብ ሲሆን ትግሉ ወዴት ሊሄድ እንደሚችል መገንዘብ አያቅትም፡፡
አንዳንድ ሰዎች ሁሉም ትግራይ አይደለም፤ ግፈኞች ትንሾች ናቸው ይላሉ፡፡ ስለትግሬዎች ትግሬ ያልሆኑ ከተገፊዎች ወገን ይጮኻሉ፡፡ እነርሱ ግን ዝም ብለዋል፡፡ ዘመኑ ይሁን ወይም ሌላ አንዳች አስማት አላውቅም፤ ግን አንድም እንኳ የትግሬ አባት ወይም የሃይማኖት መሪ ‹‹ኧረ ተው ዐማራውን አትግደሉ? እስከ መቼ የወልቃይትን መሬት የዐማራ ገላ ማዳበሪያ አድርገን የሰው ደም አኝከን እንቀጥላለን? እስከ መቼ የዐማራና የኦሮሞ እናቶች ልጄ ልጄ እያሉ ይዘልቃሉ?›› ያለ የለም፡፡ እንዲያውም የዐማራውንና የኦሮሞን መካሪ መካሪ አስተዋይ ሰው በገፍ ይታጨዳል፡፡ ጭፈራ ቤቶች በስካር ያጠራቀሙትን ሽንት በታሠሩ ዘመዶቻችን ላይ ይሸናሉ፡፡ አቤት ግፍ! አቤት ግብዝነት! ወዮ ለእነርሱ! ወዮ በመጨረሻው ሰአት!
በጥፋት ውኃ ዘመን እንደ አሁኑ የእኛ ገዥዎች መሬት ላይ የነበሩ ሰዎች ሁሉ በሀኬትና በእብሪት ተይዘው ነበር፡፡ አንድም እንኳ አስተዋይ ሰው ማግኘት አልቻሉም፡፡ የጥፋት ውኃ እየዘነበባቸው እነርሱ እስክስታን ይመቱ ነበር፡፡ በውኃው ሙሉ በሙሉ እስከሚሰምጡ እንደሚሞቱ እንኳ አላወቁም፡፡ በትውልድ አስተዋይነት ሲጠፋ እንደዚህ ነው፡፡
በእኛ አገር አሁን ያለውን ሁኔታ ከስሜት ወጥቶ ለሚመለከተው ይኼው ነው፡፡ የትግራይ አባቶች ልጆቻቸውን ይመክሩ ዘንድ የሃይማኖት አባቶች ጸልዩ፡፡ ቤተ ክሕነቱን እነርሱ ቢይዙትም በሥልጣን እና በፍቅረ ንዋይ እብደት ያን የሚመለከቱበት መነጸር ተሸፍኗል፡፡ ክርስቲያንም እስላምም የሃይማኖት መሪ ስለ ትግሬዎች ጸልዩ፡፡
ከተራበ ይልቅ ለጠገቡ እዘኑ፡፡ የመበቃቀል ዘመን እንዳይመጣ የትግሬ እናቶች ልጆቻቸውን ይመክሯቸው ዘንድ ምኞቴ ነው፡፡
ስለ ትግሬዎች ጸልዩ! Muluken Tesfaw