የትግሬ ነጻ አውጭ ቡድን ንጹሀን ኢትዮጵያውያንን በአልሸባብ አመካኝቶ በቦንብ ሊያጋይ እንደሆነ የፌድራል ፖሊስ አባል ተናግሯል።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
አደገኛው የትግሬ ነጻ አውጭ ቡድን ንጹሀን ኢትዮጵያውያንን በአልሸባብ አመካኝቶ በቦንብ ሊያጋይ እንደሆነ የፌድራል ፖሊስ አባል ተናግሯል። እንደሚታወቀው በዚህ ሰዓት የኦሎምፒክ ጨዋታ እየተካሄደ ነው። ጨዋታውን በዲኤስ እና ጂ ቲቪ ቻናል ለማየት የሚሰበሰቡ ወጣቶች ወያኔ በአልሸባብ አመካኝቶ ለሚያፈነዳው ቦንብ ሰለባዎች ሊሆኑ ይችላሉ።
ከዚህ በተጨማሪ ህዝባዊ መጓጓዣዎች፣ ስቴዲዮሞች፣ ህዝባዊ ስብሰባዎች፣ ሲኒማና ቲያትር ቤቶች፣ገበያ ቦታዎች፣ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት እንዲሁም ባጠቃላይ ሰው በብዛት በሚሰበሰብባቸው አካባቢዎች ወያኔ ቦንብ ማፈንዳቱ አይቀርም። ነጻ ሊያወጣው ጫካ የገባለትን የትግራይ ህዝብ በሀውዜንና በአይደር ለፖለቲካ ፍጆታ ሲል ያስጨፈጨፈ ግፈኛ ቡድን፤ «በቃኝ!» ባሉት ሌሎች ድሆች ላይ ርህራሔ ያሳይል ተብሎ አይታሰብምና ሁሉም ሰው ህዝብ በብዛት በሚሰበሰብባቸው አካባቢ የራሱን ጥይቃቄ ያደርግ ዘንድ ግድ ይላል።
ይህ ጨካኝ ቡድን ችግር ባጋጠመው ጊዜ ሁሉ ለምሳሌ በ1996 ዓ.ም. አዲስ አበባ ውስጥ ሆቴሎችን፣ ዩኒቨርሲቲዎችን፣ የህዝብ ማመላሻዎችንና የንግድ ተቋማትን ራሱ በቦንብ እያጋየ ኤርትራንና ሌሎችን ተጠያቂ ያደርግ እንደነበር ዊክሊክስ መዘገቡን አንርሳ።