በአልሸባብ ሽፋን በኣማራው ላይ ሊሰነዘር የታቀደ ሽብር ??? – አልሸባብ በምሥራቅ አፍሪካ አገሮች የሽብር ጥቃት ‹‹Al-shabab as a Transnational Security Threat››


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በአልሸባብ ሽፋን በኣማራው ላይ ሊሰነዘር የታቀደ ሽብር ???

የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ)፣ አልሸባብ የቀጣናው የፀጥታ ሥጋት መሆኑ እንደጨመረና የሽብር ጥቃት ሊፈጽም እንደሚችል አሳሰበ፡፡

የኢጋድ የፀጥታ ዘርፍ ይፋ ባደበአልሸባብ ሽፋን በኣማራው ላይ ሊሰነዘር የታቀደ ሽብር ረገው ሪፖርት ዋነኛ መቀመጫውን ሶማሊያ ያደረገው አልሸባብ፣ አሁን አሁን የምሥራቅ አፍሪካ አጠቃላይ ቀጣና ከፍተኛ የፀጥታ ሥጋት እየሆነ መምጣቱን አሳውቋል፡፡

‹‹Al-shabab as a Transnational Security Threat›› በሚል ርዕስ የወጣው ሪፖርት በፀጥታው ዘርፍ አማካይነት ሰኞ ነሐሴ 9 ቀን 2008 ዓ.ም. ይፋ የተደረገ ሲሆን፣ ከዓለም አቀፉ አሸባሪ ድርጅት አልቃይዳ ጋር ትስስር እንዳለውና የአልሸባብ ተፈጥሮም በተወሰነ ደረጃ ከአይኤስ ጋር እንደሚመሳሰል በሪፖርቱ ተጠቁሟል፡፡

እስካሁን በአብዛኛው የሶማሊያ የፀጥታ ሥጋት ተደርጎ ሲታይ የቆየው አልሸባብ፣ አሁን ግን እንቅስቃሴው በአጠቃላይ በቀጣናው መስፋፋቱና ወጣቶችን እየመለመለ አደገኛ የሽብር ድርጊቶች ይፈጽማል ተብሎ እንደሚሠጋ አዲሱ ሪፖርት ያመለክታል፡፡

ይኼው ሪፖርት በማጠቃለያው ‹‹አልሸባብ የሶማሊያ የፀጥታ ሥጋት ብቻ አይደለም፡፡ በመሆኑም አካባቢያዊ የተቀናጀ ምላሽ ይጠይቃል፤›› ብሏል፡፡ አልሸባብ በኬንያ፣ በኢትዮጵያ፣ በጂቡቲ፣ በታንዛንያና በኡጋንዳ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ የገለጸው የኢጋድ ሪፖርት፣ በተለይ በአፍሪካ ቀንድ ከፍ ያለ የፀጥታ ሥጋት ለመሆን መብቃቱን ያስረዳል፡፡

ብሩንዲን ጨምሮ እነዚህ አገሮች በሶማሊያ አልሸባብን በመዋጋት ላይ ላለው የአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ኃይል (አሚሶም) ወታደሮች ማዋጣታቸው ይታወሳል፡፡

አልሸባብ በኢትዮጵያ ወታደሮችና በኅብረቱ ሰላም አስከባሪ ኃይል የተከፈተበትን ወታደራዊ ዘመቻ መቋቋም ቢያቅተውም፣ የሽብር ጥቃቱ በሌሎች የምሥራቅ አፍሪካ አገሮች ላይ ሊሰነዝር እንደሚችል ሪፖርቱ ይገልጻል፡፡

አልሸባብ ከሰነዘራቸው ጥቃቶች የከፋው ባለፈው ዓመት በኬንያ ጋሪሳ ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች ላይ የፈጸመው የሽብር ተግባር ሲሆን፣ በወቅቱ የ248 ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል፡፡

ይኼው ጥቃት ቀደም ሲል አልቃይዳ ናይሮቢ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ካደረሰው ጥቃት ቀጥሎ የከፋ መሆኑ መገለጹም ይታወሳል፡፡