መነሻው በውል ያልታወቀ ተቃውሞ ቀጥሏል – የጎንደር ነዋሪዎች በቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


‹‹ኦሮሚያን የመገንጠል ዓላማ ያላቸው ኃይሎች ታይተዋል››  አቶ ኩማ ደመቅሳ

        ‹‹በኢትዮጵያ አሸባሪ ሥርዓት ነው ያለው›› ዶ/ር መረራ ጉዲና

        ‹‹የተቃውሞ መነሻ የመልካም አስተዳደር ችግር ነው›› አቶ ጌታቸው ረዳ

በጎንደር በተደጋጋሚ ሲካሄድ የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ በአሁኑ ወቅት ቤት ውስጥ በመቀመጥ አድማ ቀጥሏል፡፡ በአካባቢው የሚገኙ ምንጮች ጎንደር ፀጥ ረጭ ብላ ያለፉት ሦስት ቀናትን እንዳሳለፈች ይገልጻሉ፡፡ ከጎንደር ውጪ በተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎች ተቃውሞው የመስፋፋት አዝማሚያን አሳይቷል፡፡ በአገሪቱ አሁንም መረጋጋት ባይታይም ጉዳዩ የሚመለከተው መንግሥት የችግሩን መንስዔ ከመልካም አስተዳደር ጋር ያገናኘዋል፡፡ የቀድሞው የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንትና የአዲስ አበባ ከንቲባ የነበሩት አቶ ኩማ ደመቅሳ በበኩላቸው፣ መንግሥት ከለያቸው መንስዔዎች በተጨማሪ ሁለት ኃይሎች በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች ታይተዋል ይላሉ፡፡ ዶ/ር መረራ ጉዲና መንግሥት እያሸበረ ነው በማለት ሲከሱ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ግን የተደበላለቁ ጥያቄዎች እየተሰሙ ነው በማለት ያስረዳሉ፡፡ ዝርዝሩን ለመመልከት እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡