­

አንዴ ሲሰረቅ አንዴ ቀን ሲቀየርለት የነበረው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ አስታወቀ።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገብረእግዚአብሄር ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት፥ ብሄራዊ ፈተናውን የወሰዱ ተማሪዎች ውጤታቸውን በኤጀንሲው ድረ ገፅ እና በሞባይል አጭር የፅሁፍ መልዕክት ከዛሬ ጀምሮ ማወቅ ይችላሉ።

በዚህም መሰረት በኤጀንሲው ድረ ገፅ www.neaea.gov.et በመግባት አልያም በነፃ አጭር የፅሁፍ መልክት 8181 ላይ RTW ብለው በመፃፍ ስፔስ በማድረግ የመለያ ቁጥራቸውን አስገብተው በመላክ ማወቅ እንደሚችሉ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥቡ በቅርቡ ይፋ እንደሚሆንም ነው አቶ አርአያ የጠቆሙት።

ዘንድሮ ወደ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተናን 253 ሺህ 424 ተማሪዎች መውስዳቸውን ኤጀንሲው ያደረሰን መረጃ ያመለክታል።