ጎንደር ለ3 ቀን ደሴ ላይ የሰው እንቅስቃሴ የባጃጅና የከተማ ታክሲ የስራ ማቆም አድማ ተደርጓል ::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


#‎Ethiopia‬ ‪#‎Welloprotests‬ ‪#‎Amhararesistance‬ ደሴ ላይ የሰው እንቅስቃሴ የባጃጅና የከተማ ታክሲ የስራ ማቆምአድማ የንግድ ስራ ቦታወች ሁሉ ዝግ ሆነዋል።የክልሉየፌዴራል ፖሊስ አድማ ብተና አጋዚ መሀል ፒያሳ ጨምር መላው ከተማዋ በሚገኙ ህንፃወች ስር ተቀምጠው በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።

ትላንት ቅዳሜ ጀምሮ ዛሬ ሌሊቱን ወጣቶቺን ለመልቀም የመንግስት ታጣቂዎቺ በፓትሮል መኪና በዬሰፈሩ ሲዞሩ አድረዋል!! እስካሁን ባረጋገጥነው መሰረት በአጠቃላይ 6 ወጣቶቺ ታስረዋል። በአሁኑ ሰዓትም ሃይቅ ከተማ ላይ በየሰፈሩ በገጠር ሚኒሻወች እና ፖሊሶች ተጨናንቃለች ።በዛሬው እለት በወልዲያ ከተማ መንግስት ባደረበት ፍርሃት ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ መከላከያ ወታደሮች፣ ፌደራል ፖሊሶች፣ ደህንነቶች በየመንደሩ መሳሪያ ደግነው በተጠንቀቅ ቁመዋል።ሰላሳ የባጃጅ ሾፌሮች ታስረዋል። አዳኖ የተባለ ሆስፒታል የሚሰራ እንዲሁም ሰማው ተክሌ ታስረዋል።

በሰሜን ወሎ ዞን ሙቁት ከተማ ሕዝብ ተቃዉሞ ለማሰማት ወጥቷል::ሰሜን ወሎ ዞን በመቄት ወረዳ ፍላቂት እና ገረገራ ከተማወች ከ 4000 በላይ ህዝብ ሰልፍ ወጡ። ወልቃይት አማራ ነው አላማጣ አማራ ነው ኦሮሞ እና አማራ አንድ ነው በሚል መፈክር እያሰማ ታጣቂዎች ሰልፉ ለመበተን እየሞከሩ ነው። በቀበሌ 02 ሰዉን እየደበደቡት ነው። ግን ሕዝቡ ሳይፈራ ድምጹን እያሰማ እንደሆነ መረጃዎች እየደረሱ ነው።ጎንደር ፅጥ ረጭ ብላለች የከተማ ታክሲዎች ባጃጆች ካፊዎች ሆቴሎች የቢዝነስ ተቋሞች ለ3 ቀን አድማ ተደርጓል :: Minilik Salsawi

Image may contain: crowd, one or more people and outdoor