የወቅቱ የኃይል አሰላለፍና ተለዋዋጭ እውነታወች! ( አለበል አማረ – ኮ/ል)


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የወቅቱ የኃይል አሰላለፍና ተለዋዋጭ እውነታወች! ( አለበል አማረ – ኮ/ል)

ባለፉት ጥቂት ወራቶች አገራችን ውስጥ የተፈጠሩት ፖለቲካዊ ትኩሳቶች በአገር ውስጥ ታምራዊ ለውጥና መነሳሳት ከመፍጠራቸውም በላይ የአለምን ማህበረሰብ ትኩረት ስቧል።
በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደ ሰደድ እሳት በሁሉም የአገራችን ክፍሎች የተቀጣጠለው የህዝብ አመፅ በድርጅት ሳይመራና በአደረጃጀት ሳይደገፍ እዚህ ደረጃ ላይ ደርሶ ማየት ከሩብ ክፍለ ዘመን በላይ የደረሰበት የግፍ ፅዋ ሞልቶ መፍሰሱን ያረጋግጣል። ህዝቡ የደረሰበት ውሳኔና ተግባራዊ ክንውኑ ሲታይ የትግሬ ወያኔ አገዛዝ ባሳለፉት የአገዛዝ ዘመናቸው ህዝቡ ምን ያክል በግዞት እንደተሰቃየ እንደተማረረና ይህንን ዘራፊና ጎጠኛ ቡድን ከእንግዲህ ተሸክሞት ለመኖር የማይችልበት የመጨረሻ ደረጃ ላይ መድረሱን ያሳያል። ህዝባዊ ትግሉ ወደ ግልፅና አዋጭነት ያለው የኃይል አሰላለፍም እየመጣ ይመስላል። በግልፅ እንደሚታየው፤ የትግራይ ነፃነት ግንባር በአብዛኛው የትግራይን ተወላጆች ይዞ በአንድ ሰልፍ የቆመ ሲሆን የአማራና የኦሮሞ ህዝብ እንዲሁም የተወሰኑ የብአዴን አባላት በሌላው ተቃራኒ ሰልፍ የቆሙ ይመስላል (እርግጥ ነው የአማራንና የኦሮሞን ህዝብ ለማቀራረብ የበለጠ ብዙ መስራት ይጠይቃል) በሶስተኛ ረድፍ ደግሞ በሰላምም ይሁን በትጥቅ እንታገላለን ያሉ ተቀዋዋሚወች መሃል ሰፋሪ የሆኑ ይመስላል። ምክንያቱም የህዝቡን ትግል በመምራት ወይም ጠንክሮ በመደገፍ ኃላፊነታቸውን ሲወጡ አይታዩም ፤ እንዴውም ሂደቱን የፈሩት ይመስላል። ፍርሃቱ ከተለያየ ነገር ሊታይ ይችላል፤ በአንድ በኩል የትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር በህዝባዊ ትግሉ እየደረሰበት ያለውን ሽንፈት በምክንያት አድርጎ ቁጭቱን እኔ ላይ ሊወጣል ይችላል ከሚል የሚነሳ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ብዙ የሂወት ኪሳራ ይገጥማል አገርም ወደ አልተፈለገ ቀውስ ይገባል ከሚል ሊሆን ይችላል። እኔ እንደሚመስለኝ ግን አንድን ሊሆን የሚችል ነገር ፈርተን ዝም ስላልን የሚቀር አይመስለኝም፤ ኢትዮጵያ ውስጥ መሬት ላይ ያሉት ነባራዊና ህሌናዊ ሁኔታወች ለህዝባዊ ትግልና ለውጥ ተመቻችተዋል። ይህንን እውነታ በመቀበል የመከራን ጊዜ ለማሳጠር፤ የሃብትና የሰው ኃይል ኪሳራን ለመቀነስ እጅጉን ስለሚጠቅም የአገራችን የፖለቲካ ኃይሎች ከወቅታዊ ጠንካራ የትግል ስትራቴጅ ጋር ቆራት አመራር መስጠት ያስፈልጋል። በሌሎች አገሮች እንደምናየው የፖለቲካ መሪወች በማንኛውም የህዝብ እንስቃሴ ፊት ሁነው ሲጋፈጡ፤ ህዝቡን ሲመሩ ይታያሉ። ህዝቡም እነዚህን በተግባር ቆራጥነታቸውን ያረጋገጠላቸውን መሪወቹን ይጠብቃል፤ የተግባር መመሪያቸውንም ይሰማል ተግባራዊ ያደርጋል። በዚህ በተመቻቸ በአሁኑ ሁኔታ በእኛ አገር እንዲህ አይነቱ ሁኔታ አለመታየቱ ያጠያይቃል። የጎንደር ህዝብ ኮ/ል ደመቀን ጥላና መከታ ሁኖ አሳልፈን ለትግሬ ወያኔ አንሰጥም በማለት እየከፈለ ያለውን ውድ ዋጋ እያየን ነው፤ ሌሎች የፓርቲ መሪወች እንዲህ አይነት ተግባር ቢፈፅሙ ህዝቡ ከነሱ በፊት መስዋት እንደሚሆን የሚያጠራጥር አይመስለኝም።
የወቅቱ አንገብጋቢና ተፈላጊ ጉዳዮች፤
1.አመራር
ህዝቡ ባልተደራጀና በተበተነ መንገድ ህዝባዊ ትግሉን እያጦፈው ነው፤ ይህ ግን በብስለት ከጠላት በሚበልጥ ብስለት ያለው ቁርጠኛ የተደራጀ አመራር ካልመራው ውጤቱ ብዙ ችግሮችን ይወልዳል። ለገዥወቻችንም የተሻለ እድል ይፈጥርላቸዋል። ከላይ እንደገለፅኩት በተለይ በአገር ውስጥ የሚገኙ የፖለቲካ ድርጅት አመራሮች ይህንን ወርቃማ ዕድል ተጠቅመው ብቁ አመራር በመስጠት ዘረኛና ዘራፊውን የትግራይ ነፃ አውጭ ግንባርን ማስወገድ ካልቻሉ የሚኖራቸው አመኔታ የወረደ እንደሚሆን ሊያውቁት ይገባል።
ስርዓቱን በትጥቅ ለመታገልና ለማፍረስ በመወሰን በተለያየ አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችም የተግባር ስራ ለመስራትና ተጠናክሮ ለመውጣት ከዚህ በላይ የተመቻቸ ሁኔታ ያለ አይመስለኝም። ህዝቡ ለማንነቱና ለአገሩ ነፃነት ሲል እስካፍንጫው የታጠቀውን፣ የሰለጠነውን እና የተደራጀውን አፋኙን የትግሬ ነፃ አውጭ ወታደራዊ ኃይልን ገጥሟል፤ በብዙ አካባቢወችም አስደናቂ ገድል ሰርቷል። ውትድርና ስሜትና ጀግንነት ብቻ ሳይሆን ሳይንስም /ዕውቀት/ ነውና በዚህ መስክ የሚረዳው የሚያደራጀውና የሚያስተምረው ኃይል ያስፈልገዋል፤ ይህም በትጥቅ ለመታገል ከተሰለፉ ኃይሎች የሚጠበቅ ጉዳይ ነው፤ ህዝቡም በተደጋጋሚ በተግባር እንዲደርሱለት ወገናዊ ጥሪ ሲያቀርብ ቢሰማም ተስፋ ያለው ነገር አልታየም። እነዚህ
ኃይሎችም የቆሙለትን አላማ ለማሳካት ከዚህ በላይ የተመቻቸ ነገር የለምና ብዙም ጠንክሮ ባልተደራጀ በወኔና እልህ የጋራ ጠላታችን እየተፋለመ ያለውን ወገናችን መድረስና መደገፍ ያስፈልጋል።
2. ትብብር
አሁን በአለንበት ሁኔታ ለእኛ ለኢትዮጵያኖች ከትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር ውጭ ሌላ ጠላት የለንም። ህወኃት የሁላችንም ዘራፊ፣ ገራፊ፣ ገዳይና የአገራችን የጋራ ጠላት ነው። አሁን ከምናየው ልምድ እንደምንረደው ደግሞ ሁላችንም በያለንበት በተመሳሳይ ጊዜ የአፈና፣ የስለላና የፖለቲካ መዋቅሩ ስናፈራርሰው የመሞቻ እድሜውን እናፈጥነዋለን። ይህን ስኬት የምናገኘው ደግሞ ስንተባበርና ሁላችንም የየአቅማችን ስንታገልና ስንተጋ ነው።
3. ጠላት
ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደሚያውቀው የህዝቡም የአገራችንም ነቀርሳ የትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር ነው። ይህን ክፉ ጠላት በጥንካሬ በመያዝ የአገዛዝ እድሜውን ለማራዘም ጉልህ ሚና ከሚጫወቱ አካሎቹ አንዱ የፋይናንስ አቅሙ ነው። ስለዚህ ጠላታችን ለማዳከም የኢኮኖሚ አቅሞቹን ያለ ምህረት ማጥቃት አለብን፤ ህወኃት እንደምናውቀው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የአገራችን ሃብት ተቆጣጥሯል፤ እነዚህ ሃብቶቹን በተገቢው ሁኔታ እየለየን በከባድ ሁኔታ ማንኮታኮት አለብን።
ሌላው የስርዓቱ የጥንካሬ ምንጭ ደግሞ በተለያዩ የስራ መስኮች ተሰማርተው የሚኖሩ ግልፅና ድብቅ ሰላዮቹ ናቸው። እነዚህ ነፍስ አስገዳዮችና አገር አጥፊወች ላይ በኃብትንብረታቸውና በነፍሳቸው ላይ ቆራጥ የሆነ የማያቁአርጥ የመመንጠር ጠንካራ ዘመቻ ማካሄድ አለብን።
በሶስተኛ ደረጃ በተለይም በብአዴን እና በኦህዴድ ውስጥ የአማራና የኦሮሞ ካባ ለብሰው ለህወኃት የሚሰሩ ቅጥረኞችን ማስወገድ ነው። ሲጀምር ትግራይ መዋቅር ውስጥ ለአማራና ኦሮሞ ቦታ እንደማይኖረው ሁሉ ትግሬም በሌሎች ድርጅቶች /ክልሎች/ ቦታ ሊኖራቸው አይገባም። ሲቀጥል እነዚህ ሰወች ላልተወለዱበት አካባቢና ህዝብ ሊገዙት እንጅ ሊሰሩለት አይችሉም ውክልናም ሊኖራቸው አይገባም።
4.ስልት
ትግሉ አገር አቀፍ እና ህዝባዊ ቢሆንም የበሰለ አመራር ይኑረው እስካልን ድረስ የአመርር አንዱና ዋና ስራው አዋጭ የሆነ ተለዋዋጭ ስልት መንደፍና ተግባራዊ ማስደረግ ነው። -ትግሉ አገር አቀፍና አለም አቀፍ እንዲሆን ማድረግ ለውጩም ለውስጡም ህዝብ ተገቢ ዕቅድ ማዘጋጅትና ፈፃሚውንም መለየት ይገባል። እርግጥ ነው ስለ ስልት በአደባባይ መግለፁ ተገቢነት አይኖረውም፤ ግን እየተካሄደ ያለው የለውጥ እንቅስቃሴ በድርጅት እየተመራ ስላልሆነ ይጠቅማሉ የሚባሉ ዋነኛ ጉዳዮችን መግለፅ ለህዝብ ይጠቅማሉ ብየ አምናለው፤ ለምሳሌ አሁን እየተካሄደ ያለው ህዝባዊ ንቅናቄ በማቀናጀትና በማጠናቀር ማህበራዊ የመገናኛ ዘዴወች ከፍ ያለውን ድርሻ እየወሰዱ ነው። የድርጅትና የአመራር ችግራችን እስኪፈታ ይሀው ተጠናክሮ ቢቀጥል ጠቀሜታው የጎላ ነው ብየ አስባለው። የምንፈልገውን ድል ለመቀናጀት ከወያኔ ባሃሪና ተፈጥሮ አንፃር ብዙ የተወሳሰቡ ችግሮችን በፅናትና በጀግንነት ማለፍ የሚጠበቅ ሲሆን የጠላትን የአገዛዝ ዕድሜ ለማሳጠርና የሚያጋጥመንን ኪሳራም ለመቀነስ በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ትኩረት ማድረግ ይረዳል ብየ አስባለው።
-በአገር ውስጥ እንደ ጠላት ተግባርና አቅም የተገናዘበ ስልት መቀየስ ( ሁለ ገብ) የትግል ስልት ይበልጥ ተግባራዊ የሚሆንበት ሁኔታ ጥረት ማድረግ።
-በየአካባቢው በገጠርም በከተማም ትግሉን የሚመሩ ብዙ የጎበዝ አለቆች እንዲመረጡ ማድረግ እና መሪወቹ የተለያየ ችግር ሲገጥማቸው በቀላሉ እንዲተካኩ ማድረግ።
-በትምህርት ተቁአሞች በከፍተኛ ትምህርት ተቁአሞችና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ትኩረት ሰጥቶ መስራት።
– በሲቪል ሰርቫንት መስሪያ ቤቶች፣ በኢንዱስትሪና ፋብሪካወች ፣በመያዶችና በኃይማኖት ተቁአሞች ወዘተ ያሉ ሰራተኞች ተገቢ ሚናቸውን እንዲወጡ ማስቻል።
-በጠላት የፀጥታ ኃይሎች ፖሊስ ፣ደህንነት ፣መከላከያ ፣ሚሊሻ ፣የክልል የፀጥታ ኃይሎችና የፖለቲካ መዋቅሮች የሚሰሩ ኢትዮጵያኖች የትግራይ ነፃ አውጭ ዘረኛና ዘራፊ ቡድን በወገናቸውና በእነሱም ላይ የሚያደርሰውን በደል ተረድተው በሁሉም መስክ ከህዝብ ጋር ተባብረው እንዲሰሩ ማስቻል።
-ጠቀሜታ ያላቸው አገር አቁአራጭና ክልላዊ መንገዶችን መሬቶች እየተመረጡ ብዙ ቦታ ላይ መዝጋትና የጠላትን ኃይል መበታተን፣ አንዱ ለሌላው እንዳይደርስና እንዳይደጋገፍ ማድረግ፣ ቁልፍ ቁልፍ በሆኑ ብዙ መሬቶች ላይ ጥቂት ጥቂት ሰወችን በማስቀመጥ መንገዶችን በተኩስና በመሰናክል ጭምር መዝጋት።
-የመገናኛ ዘዴወች ላይ ትኩረት መስጠት ለምሳሌ፣ ሎካል የሆኑ የአገዛዙን የሬዲዮና ቴሌቪዥን ጣቢያወች መቆጣጠርና መልክቶችን ማሰራጨት። የኢንተርኔት አገልግሎት ሊቁአረጥ እንደሚችል በመረዳት ሌሎች አማራጮችን ቀድሞ ማዘጋጄት።
-ማህበራዊ ሚዲያወችንና የታወቁትን ኢሳትን እና ኦሚኔ /OMN/ ከእስካሁኑ በተሻለ በጥራትና በአደራጃጀት መደገፍ በተገቢው ስራውን እንዲያቀናጁ መርዳት።መላ ድምዳሜ
ድምዳሜ
የትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር ህዝባችን ለመከራ አገራች ለውድቀት የዳረገ ደመኛ ጠላታችን ነው። ከዚህ በኃላ የዚህን ግለኛና ለአገርና ህዝብ ክብርና ግዴለሽ አገዛዝ ዝም ብሎ ማየት የባርነት ቀንበራችን ማጥበቅና የአገራችንም ውድቀት ማፋጠን ነው። መላ ህዝባችን ከመቸውም ጊዜ በላይ ይህንን አረመኔያዊ አገዛዝ ለመጨረሻ ገርስሶ ለማንኮታኮት ቆርጦ ተነስቷል። በዚህ ግፈኛና አረመኔ ስርዓት የሚማቅቅ ህዝብ ሁሉ ተመቻችቶ ባለው የህዝብ ንቅናቄ የበኩሉን ድርሻ መወጣት ይጠበቅበታል። ተቀዋዋሚ ኃይሎችም ከወቅቱ ጋር የሚስማማና የጋራ የትግል ስልት አቅደው የሚወክሉትን ህዝብ ማስተባበርና መምራት የሚገባቸው ምዕራፍ ላይ መሆናቸውን መረዳት ያስፈልጋል።
ድል ለህዝብ!