ቴዎድሮስ ገብርዬ መሬት ይቅለላችሁ!!!
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ወገራ አሳላፊ ደንቢያ እንጀራ ጣይ
ተበላህ ሃገሬ አትነሳም ሆይ
ይል ነበር ወገኔ ሃገሩ ተቆርሳ ተሸርሽራ ሲያይ፡፡
ጭልጋ ገለድባ አለፋም ተነሳ
በህብረት በመሆን እነደ በሬ አገሣ
ባንዳን ለማንበርከክ ከሃዲን ሊያስፈሳ
ከስሩ ገርስሶ ሊያሳየው አበሳ፡፡
አልሰማም ወይ ቋራ የጀግኖቹ ሃገር
በህወሃት ወንበዴ ሃገር ሲቸገር
ወልቃይት ጠገዴ ዳንሻና ሁመራ ልጁን ሲገብር
ከቀየው ከቦታው በሃይል ሲባረር
ቋንቋና ባህሉን በግዳጅ ሲሽር
ሴቶችንም ሳይቀር ለወሲብ እርካታ በጉልበት ሲደፍር
መላቀቅ አያሻም ሳይወርድ መቃብር፡፡
ወልቃይት ጠገዴ የጀግኖቹ ቦታ
አነጣጥሮ ተኳሽ የማያመነታ
ታግሶ ታግሶ እንዲህ ወደማታ
መግቢያ ያሳጣዋል ነጣቂውን ሽፍታ፡፡
ቴዎድሮስ ገብርዬ መሬት ይቅለላችሁ
ምኒሊክ ዮሐንስ አምላክ አድሎአችሁ
እኒህን ጉዳሞች አለማየታችሁ
ለኢትዮጵያ አንድነት እነዳልታገላችሁ
ጎንደርን ለሱዳን ይከው ሰጡላችሁ
አማራን ትግሬ ነው ብለው ዋሹላችሁ፡፡
ወረታና ጋይንት ማማው ደብረታቦር
አፈረዋናቴው እብናት ደንገልበር
ዳሞትና ሞጣ እንዲሁም ባህር ዳር
ጭስ አባይ ማርቆሴው የበላዩ ሰፈር
ንገረው ለሸዋ ለምኒሊክ ሃገር
አፍጫው ተመቶ እንደማይኖር ባገር፡፡
መልክትን አሰማ ሞረሽ በል ለደሴ
እራያም ይነሳ ቆቦ ከከሚሴ
ጸበሉ ደርሶታል የጎንደር ቅዳሴ፡፡
የአፋሩ ወገኔ ዱፍቲዉና አሳይታ
የሰው ዘር መገኛ የኢትዮጵያ ዋልታ
የሃዳር በርሃ የእነሉሲ ቦታ
አንተ አልነበርክም ወይ የዓለሙ ዋልታ
እምቢ በል ወገኔ እንዳታመነታ
ታሪክህ ሳይፋቅ ያለህ ከበሬታ
ወያኔ መርዝ ነው እንዲሁም ወስላታ
ሊነጥቅህ ይመጣል ከተኛህ ላንዳፍታ፡፡
የዋልድባን ገዳም ወያኔ አረከሰው
መንፈስ ቅዱስ አድሮ እንዳላወደሰው
ዶዘር አስገብቶ ቅርሱን አፈረሰው
ያባቶችን አጽም በእሳት ለኮሰው
የክሰል ማክሰያ እምድጃ አደረገው
ኮሎኔል ደመቀ ግባና ቀድሰው
ታሪክን በመስራት ትውፊቱን መልሰው
ቴዎድሮስ መሆንክን በተግባር አሳየው፡፡
እምዬ ኢትዮጵያ ከቶ እንደምንአለሽ
ነቀዝ አረማሞ እንክርዳዱን ይዘሽ
በዘር በሃይማኖት በቋንቋ ከፋፍሎሽ
አዙሮ ጠምዝዞ አቃጥሎ ለብልቦ አንድዶ ጨረሰሽ
ከሃዲው ሲነቀል አይቀርም ማየትሽ
ሰላምና ፍቅርን ጸጋን ተጎናጽፈሽ
የህይወት እስትንፋስ ትተነፍሻለሽ፡፡
እምነት የለሾቹን ጉዶቹን ጥሎብን
ኢትዮጵያን በቁሟ አጠፏት ህይወቷን
አማራ ኦሮሞ ሶማሌ አኝዋኩን
ወላይታ ሃድያ እንዲሁም ከፋውን
በሰሜን በደቡብ በምስራቅ በምእራብ የሃገር ተወላጁን
አዛውንቱን ሳይቀር እድሜ ጠገቦቹን
ጥይት በመተኮስ በማለት ደረትን
በሳንጃም በመውጋት እርጉዝ እናቶችን
ጫጉላ ቤት እያሉ ወጣት ሙሽሮችን
ለልቅሶ ዳርገዋል የሰርግ እለቶችን፡፡
ሁሉን እየሰማን ይህንን እያየን
ሆድ አምላኩ ሁነን ሆድ ይፍጀው እያልን
ባንድነት ተነስተን መታገል ሲገባን
ባንዳን ለማንበርከክ ችሎታው ሳያንሰን
እስከ መቸ ድረስ ጊዜን እንገፋለን
ከእንገዲህስ ወዲያ መቆዘሙ ይብቃን
ከሃዲ ሽፍታውን እንጣል መንግለን፡፡
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!!!!!
ከመሰንበት ደጉ፣ ኮሎራዶ