አምነስቲ ኢንተርናሽናል በኦሮሚያ እና አማራ የተገደሉ ሟቾች ትክክለኛ ቁጥር ደርሶኛል አለ::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Image may contain: 1 person , outdoor

ዓለም ዓቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል በሳምንቱ መጨረሻ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች የተፈጸሙት የግድያ ቁጥሮች እንደደሩሰት አስታወቀ፡፡ በኦሮሚያ ከ67 እንዲሁም በአማራ ክልል ከ37 ሰዎች በላይ መገደላቸውን የገለጸው የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ፣ የሟቾችንም ቁጥር ከታማኝ ምንጮቹ እንዳገኘ ተናግሯል፡፡
‹‹ቅዳሜ እና እሁድ በኦሮሚያ ክልል በተካሔዱ የተቃውሞ ሰልፎች ፖሊስ በተቃዋሚዎች ላይ በከፈተው ተኩስ 67 ሰዎች መገደላቸውን እና ከ100 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ከታማኝ ምንጮቼ አረጋግጫለሁ›› ሲል አምነስቲ በመግለጫው አትቷል፡፡
የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ የሰብዓዊ መብት ገምጋሚ ቡድን የሆኑት ሚሼል ካጋር ‹‹በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በተቃውሞ ሰልፉ የመንግስት ለውጥ እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡ ፖሊስ የወሰደው እርምጃ ከመጠን ያለፈ ነው፡፡ በሰልፈኞች ላይ ጥይት ተኩሷል፡፡›› ብለዋል፡፡


ህገ ወጥ ግድያ እና ከፍተኛ ደም መፋሰስ እንደተካሔደበት አምነስቲ የገለጸው የባህርዳሩ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ 37 ሰዎች መገደላቸውን አስታውቋል፡፡ እንደዚሁም ቅዳሜ ዕለት ብቻ በጎንደር ሰባት ሰዎች መገደላቸውን ከምንጮቼ አረጋግጫለሁ ብሏል ድርጅቱ፡፡ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ቅዳሜ ዕለት በአዲስ አበባ በነበረው የተቃውሞ ሰልፍ የሰው ህይወት ስለመጥፋቱ የደረሰው መረጃ እንደሌለ በመግለጫው ገልጿል፡፡

BBN