በአገር ቤት ስላለው ሁኔታ አጭር ዘገባ – ‪#‎ግርማ_ካሳ‬


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


13876663_10209904936370799_8304940350771992382_n

ሐምሌ 4

በአገር ቤት ስላለው ሁኔታ አጭር ዘገባ – ‪#‎ግርማ_ካሳ‬

– በዛሬ እለት በጎንደር ኮሎኔል ደመቀ ፍርድ ቤት መቅረብ ነበረበት። ሆኖም በፍርድ ቤቱ ብዙ ሺህ ህዝብ ስለነበረ ዳኞቹ ፈርተው፣ ዛሬ ሳያቀርቡት ቀርተዋል።፡በጎንደር የደብረጹዮን ቴሌ ኔትዎርክ ዘግቷል።

– በአርማጭሆ ታጣቂዎች እሰር ቤቶችን አጋይተው በዚያ የነበሩትን እስረኞች አስፈትተዋል። በገጠር ዉጊያው ቢቀንስም በአነስተኛ ደረጃ እንደቀጠለ ነው።

– በአማራው ክልል ገጠሪቷ ክፍል ከታቦት ጀርባ በመሆን ወያኔዎች ሕዝቡን ለማግባባት እየሞከሩነው። ጳጳሱም ማስታረቅ፣ “አንተም ተው ፣ አንተም ተው” በማለት ብሄራዊ እርቅ እንዲኖር መስራት ሲጠበቅባቸው፣ በቴሌቭዥን ቀርበው ቆብ የደፉና መስቀል የያዙ ጌታቸው ረዳ ነው የሆኑት። ሕግ ያለ ይመስል፣ ሕዝቡ ለሕግ መገዛት አለበት ሲሉ አስጠንቅቀዋል። በንጹሃን ዜጎች ላይ ሰይጣናዊ የጭካኔ ሥራ የሰሩትን ወንጀለኞች ማውገዙ ግድ የለም ይቅር ፣ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እንኳን ማሳሳቢያ እኝህ ጳጳስ ለመስጠት አልደፈሩም። የካቶሊኩ ፖፑ ያኔ ለፋሺስት ጦር ቡራኬ ሰጥተው ነበር።፡ህዝብ እንዲጨፈጨፍ። አሁንም እኝህ ጳጳስ ለአጋዚ ቡራኬ በመስጠት ከዚያ ያልተናነሰ ነገር ነው ያደረጉት።

በዚህ አጋጣሚ ዉጭ አገር ያለው ትክክለኛው የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ለሕዝቡ ንግግር ቢያደረጉ ጥሩ ነው እየተባለም ነው።

– በጎጃም ለሶስተኛ ቀን ሥራ የለም፣ ሱቅ የለም፣ ሁሉም ነገር እንደተዘጋ ነው።

– የፊታችን ቅዳሜ እና እሁዱ በተለያዩ መርሃ ግብሮች የተለያዩ ሰልፎች ታስበው ነበር። ይህ መርሃ ግብር አንዳንድ ለዉጦች ተደረገዉበታል። ሰልፎቹ በሙሉ የሚሆኑት ነሐሴ 8 ቀን እሁድ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ ከተማን ሰልፍ ይደረጋል።

ሸዋ- አዲስ አበባ፣ ደብረ ብርሃን፣ ሸኖ፣ አንኮበር፣ ደብረ ሲና፣ ሞላለ ና ሸዋ ሮቢት
ጎጃም – ደብረ ማርቆስ፣ ዳንግላ፣ ደጀን፣ኮሶ በር፣ ቡሬ፣ ሞጣ፣ዴት
ወሎ -ከሚሴ፣ ኮምቦልቻ ፣ ደሴ፣ወልዲያ፣ መቄት፣ላሊበላ፣ ሰቆጣ፣ ቆቦ፣ አላማጣ

– የሚደረጉ ሰልፎችን ለማጨናገፍ በወሎና በጎጃም ከፍተኛ የሆነ እንቅስቃሴ ወያኔዎች እያደረጉ ነው። ወጣቶች ማፈስ የመሳሰሉትን ….

– አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ምን ደረጃ ላይ እንዳሉ እስከአሁን በግልጽ የታወቀ ነገር የለም። አቶ ገዱ መፈንቀለ መንግስት እንደተደረገባቸው የሚያመለክት ዜና ከወደ ህወሃት ደጋፊዎች መስማታችን ይታወሳል።