በወልደያ ውጥረቱ ጨምሯል፤ በደሴ በርካታ ወጣቶች በገፍ ታስረዋል


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በወልደያ ውጥረቱ ጨምሯል፤ በደሴ በርካታ ወጣቶች በገፍ ታስረዋል
ደሴ፤ በደቡብ ወሎ በደሴ ከተማ የዐማራ ተጋድሎ ሰልፍ ለማካሔድ አስባችኋል በሚል በርካታ ወጣቶች እየታሰሩ መሆኑን አሁን ከመሸ የደረሰን መረጃ አመልክቷል፡፡ መረጃውን ያቀበሉን የደሴ ከተማ ነዋሪዎች እንደሚሉት በየሰፈሩ ወጣቶች እያታደኑ እየታሰሩ መሆኑን ነው የሚገልጹት፡፡ ለምን እንደሚታሰሩ ለጠየቅናቸው ጥያቄ ‹‹ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ አቅዳችኋል›› በሚል ሰበብ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ወጣቶችን የሚያሳፍሱ ቅጥረኞች ካርድ እየተሞላላቸውና አበል እየተከፈላቸው እንደሚሰሩ ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡
ወልደያ፤ በወልደያ ከተማ ዛሬ ማምሻውን ጀምሮ ከፍተኛ ፍተሻ እንደነበር ለማወቅ ችለናል፡፡ የወልደያ ከተማ ነዋሪዎች እንደሚሉት በባጃጅ የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች እየወረዱ መታወቂያቸውን እንዲያሳዩ ይገደዱ ነበር፡፡ በከተማው አዳጎና ፒያሳ ተብለው በሚጠሩ አካባቢዎች ወጣቶች ተሰባስበው ሲታዩ እንዲበተኑ ይደረግም እንደነበር ተገልጧል፡፡