አቶ በረከት እንደ ሌባ ከስብሰባ ሾልከው ወጡ – #ግርማ_ካሳ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
አቶ በረከት ስምኦን ከ10 ቀናት በፊት ከአገር ሽማግሌዎች ጋር ባደረጉት ንግግር “ጥያቄያችሁን በሙሉ በማስታወሻ ደበትሬ ይዣለሁ። በላይ ላሉት አቅርቤ ተነጋግረነበት መልሱን ይዤ ከሶስት ወራት በኋላ እመለሳልለሁ” ማለታቸውው ይታወሳል። ከሕዝቡ ለአቶ በረከት ከቀረቡ ጥያቄዎች አንዱ የታፈኑ የወልቃይት ኮሚቴ አባላትን ህወሃት እንዲመለስና ኮሎኔል ደመቀ በዛብህም እንዲፈቱ የሚጠይቅ ነበር። ሆኖም አቶ በረከት ወደ አዲስ አበባ ከተመለሱ በኋላ ፣ ነገሮች ተባባሱ። ኮሎኔል ደመቀ ፍርድ ቤት መቅረብ ሲገባቸው ፍርድ ቤቱ በሕወሃት ታዞ ሳያቀርባቸው ቀረ። ህዝቡም በድጋሚ ተቃዉሞዉን ማሰማት ሲጀምር የሕወሃት ጣጣቂዎች ሕዝቡ ላይ መተኮስ በመጀመራቸው ተቃዉሞው ተቀጣጠለ። በርካታ ወገኖችም መቶ።
አቶ በረከት እንደለመዱት ወደ ጎንደር አመሩ። ከበስተጀርባ ሕወሃት ዜጎችን እየገደለ እንደገና ለማረጋጋት ብለው መጡ። ከሕዝቡ ጎን የተሰለፉትን የብዓዴን ታችኛዉና መካከለኛ አባላትን ለማነጋገር በሲኒማ አዳራሽ ደረሱ። በስብሰባው ከነበሩ የብአዴን አባላት ከፍተኛ ዉግዘት ደረሰባቸው። ስብሰባው እየተደረገ መሆኑን የሰሙ የጎንደር ወጣቶች ወደ ቦታው በመሄድ የሲናማዉን አዳራሽ በድንጋይ መደብደብ ጀመሩ። አቶ በረከትም ስብሰባዉ ለመበተን ተገደዱ። እየተዋከቡ እንደ ሌባ በወታደሮች ታጅበ ሾልከው አመለጡ።ዉርድት ይሉትል ይሄ ነው።
በጎንደር ፒያሳ አካባቢ ተቃውሞ ተቀጣጥሏል። “ በረከት ሌባ ፣ የወያኔ ተላላኪ፣ እኛን አትወክሉም ፣ በአስቸኳይ ጎንደርን ለቃችሁ ውጡ? ኮሎኔል ደመቀ ጀግናችን ነው! “ በሚሉ መፈክሮች ወደ አስተዳደር ጽ/ቤት እያመሩ መሆኑ ከጎንደር በሚመጣ መረጃ እየተሰማ ይገኛል፡፡
ከዚህ በታች ያለው አቶ በረከት ከሕዝብ ጋር ባደረጉት ንግግር ሕዝቡ ከተናገረው