ሕወሃት በአማራው ክልል መፈንቀለ መንግስት አደረገ እየተባለ ነው – #ግርማ_ካሳ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የአማራው ክልል ፕሬዘዳንት አቶ ገዲ አንዳርጋቸው ላይ ሕወሃት መፈንቀለ መንግስት እንዳደረገ ዳንኤል ብርሃኔ የተሰኘው አፍቃሪ ሕወሃት ጦማሪ ገለጸ። አቶ ገዱ በአማራው ክልል ምክር ቤት የተመረጡ ሲሆን እርሳቸውን ለማንሳት ስልጣን ያለው የክልሉ ምክር ቤት ሆኖ እያለ ሕወሃት የክልሉን አስተዳደር፣ የክልሉን ምክር ቤት እና የክልሉን ሕዝብ በመናቅ አቶ ገዱን ማንሳቱ በይፋ ብአዴን ከሕወሃት እንደተለየ የሚያመላክት ነው። አቶ ገዱን ተክተው የፓርላም አባል የሆኑት አቶ ደመቀ መኮንን ሃላፊነቱን እንደወሰዱ ነው ዳንኤል የጻፈው። አቶ ደመቀ ለፌዴርራል ፓርላማ አባል እንደመሆናቸው የክልሉ የበላይ ሆነው ክልሉን ለማዘዝ በሕወሃት መመደባቸው ክልል እንደ አዲስ አበባና ድሬዳዋ ሙሉ ለሙሉ በፌዴራል(በሕወሃት ሥር) ሆናለች እንደማለት ንው።
ይህ የሕወሃት መፈንቀለ መንግስትት ብአዴን የተባለዉን ድርጅት ሙሉ ለሙሉ የሚያፈርሠው ሲሆን የብአዴን አብዛኛው አባላት በይፋ ከሕዝቡ ጋር እንዲቀላቀሉም የሚያደረግ ነው:። በአማራው ክልል ያለው ተቃዉሞ የበለጠ ያጠናክረዋል ተብሎም ይጠበቃል።
አቶ ገዱ ሕዝቡ መስሪያ ከማስታጠቅ ጀመሮ፣ ዉስጥ ዉስጡን ሕወሃትን ሲታገሉ የነበሩ እንደሆነ ይነገርላቸዋል። በባዴን መካከለኛዉና ታችኛው አባላት ከፍተኛ ድጋፍ ያላቸው አቶ ገዱ፣ ምን ሊያደርርጉ እንደሚችሉ ባይታወቅም፣ ሕጋዊዉን የክልል ምከር ቤት ጠርተው የሕወሃት እርምጃ መመከት እንደሚኖርባቸው ተንታኞች ይናገራሉ። የክልሉን ምክር ቤት በመሰብሰብ ምክር ቤቱ በይፋ የፌዴራል አጋዚ ጦር ክክልሉ እንዲወጣ አቶ ገዱ እንዲጠይቁም ከሕዝቡ ግፊት እየተደረገባቸው ነው። አቶ ገዱ የቁም እስረኛ ካልሆኑና ከማንም ጋር እንዳይገናኙ ካልተደረቀ በቀር፣ በዚህ መልክ አፍጥጦ የመጣዉን የሕወሃት ጠብ ጫሪነት በዝምታ ይመለከቱታል ተብሎ አይገመትም።
በርካታ የሕወሃት ሜዲያዎች በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና በብአዴን ላይ ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ መጀመራቸው ይታወቃል። ይህ በአቶ ዳነል የቀረበዉን ዘገባ በተመለከተም ከብአዴን ሆነ ከፌዴራል መንግስት የተሰጠ ምንም አይነት መረጃ የለም።