ኢትዮሚዲያን (Ethiomedia) የበላ ጅብ አልጮህ አለ? ”503 Service Unavailable”
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ለበርካታ ዓመታት በድረገጽ አማካይነት ለኢትዮጵያዊያን የመረጃ አቅርቦት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሲያበረክት የነበረው ኢትዮሚዲያ ድረገጽ ከአየር ላይ ከወረደ ሳምንት አልፎታል። በተለይ ካላፉት ሁለት ሳምታት ወዲህ ወያኔ ስልጣን ላይ ከተፈናጠጠ ወዲህ ኢትዮጵያዊያን ትጥቅ በማንሳት ከፍተኛ ትንንቅ በማድረግ ላይ በሚገኙበት ወሳኝ ወቅት ላይ ይህ ድረገጽ መሰወሩ/መጥፋቱ ብዙዎችን እያነጋገረ ይገኛል። ምናልባት አዘጋጁ ላይ የጤናም ሆነ ሌላ እክል ገጥሟቸው ሊሆን ይችላል። ቢሆንም ድረገጹ ሳይታደስ መጨረሻ ያወጣውን ዜናዎች ይዞ ይቆያል እንጅ ማለትም አዲስ ዜናዎች ሳይጨመሩበት ይቀራል እንጅ እንዴት ከዕይታ በኖ ይጠፋል? እባካችሁ ይህንን ጉዳይ የምታውቁ ካላችሁ አንድ ነገር በሉን።
ታደሰ ሰብሮ