በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የተነሳው አለመግባባት ቅራኔ ፈጥሯል።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የተነሳው አለመግባባት ቅራኔ ፈጥሯል። #Ethiopia #Oromoprotests #Amharaprotests #TPLFArmy #EthiopianArmy #MinilikSalsawi
Minilik Salsawi – mereja.com ከኬንያ የድንበር ኣከባቢና ደቡብ ሱዳን ቅጥረኛ ወታደሮችን ገዝተን ማሰራት እንችላለን ፌዴራል ፖሊስ ውስጥ ያደረግነውን በመከላከያ ውስጥ እንደግመዋለን የሚሉ ከፍተኛ የሕወሓት ጄኔራሎች በሰሜን እዝ እና ምእራብ እዝ ከሚገኙ ወታደሮቻቸው ጋር በተነሳው ኣለመግባባት ቅራኔ መፈጠሩን የወታደራዊ ደህንነት ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል፥ ጉዳዩ የከረረ መሆኑ ለሕዝቡ ትግል ኣንድ እመርታ ያሉት ምንጮቹ የሃገር ውስጥ የተቃዋሚ ሃይሎች ስልታቸውን እንድፈትሹና እንዲቀይሩ ኣስፈላጊ ወቅት ላይ መሆኑን ጠቁመዋል።
የወታደራዊ ደህንነት ሱፐርቫይዘሮች የሆኑ ምንጮች በኣማራ ክልል የተነሳውን የሕዝብ የለውጥ እና የመብት ጥያቄ ተከትሎ በሰራዊቱ ውስጥ ያለውን እንቅስቃሴ ለመገምገም በተሰማሩበት የምእራብ እዝ እና የሰሜን እዝ ውስጥ ያለው ሁኔታ ኣደገኛና ሰራዊቱ ማብራሪያ በተከታታይ እየጠየቀ የሕወሓት መኮንኖችን መረበሹን ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል። በማስፈራሪያና በዛቻ ተከበን ማገልገል ኣንፈልግም ወደቀያችን መልሱን የሚሉ ወታደሮች እየበረከቱ የመጡ ሲሆን ከኦሮሚያ ክልል የተቀጠሩ ወታደሮች በይበልጥ ሰራዊቱን መልቀቅ እንፈልጋለን በማለት በሕወሓት መኮንኖች ላይ ጫና እየፈጠሩ በመገኘታቸው ኣለመግባባቱ በርትቶ ቅራኔዎች እየሰፉ መምጣታቸው ታውቋል። #ምንሊክሳልሳዊ
