ትድረስ በዚህ ዘመን ላላችሁ ካህናት ባህታዊ አምኃ ኢየሱስ የመምህር ገብረ ኢየሱስን ድምጽ አሰሙ፤ከቀሲስ አስተርአየ ጽጌ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ከቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

ታላቁ ሊቅ ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ በማይነጥፍ ብዕራቸው በዘመናችን በተለያዩ ቤተክርስቲያኖች ላይ እንደ መዥግር ተለጥፈው ነፍሳቸውን ትተው ለስጋቸው ያደሩ “ካህናት ነን” ባዮች በማድረስ ላይ ያሉትን እጅግ የገዘፈ ችግር አበጥረውና አንጠርጥረው አቅርበውልናል። “ትድረስ በዚህ ዘመን ላላችሁ ካህናት ባህታዊ አምኃ ኢየሱስ የመምህር ገብረ ኢየሱስን ድምጽ አሰሙ” በሚል ያቀርቡል መጣጥፍ ላይ እንዲህ ብለዋል “…..በምድራችን ላይ የሚደረጉት ነገሮች በጊዜ፤ በሚፈጸምባቸውና በሚፈጽሙት ሰዎች ይለያዩ እንጅ፤ ድግግሞሽ ናቸው። ባህታዊ አምኃ ኢየሱስ በወያኔ መንግሥት በተበደለው በጎንደር ህዝብ መካከል ቆመው ያሰሙን ድምጽ፤ በጣሊያን ወረራ ጊዜ እነመምህር ገብረ ኢየሱስ ላሰሙት ድምጽ ድጋሚ ነው። ወያኔ በወገን በአገር ላይ የሚፈጽመውን ግፍና መከራ በዝምታ በማለፍ ላይ ያላችሁ፤ ከህዝብ ጋራ አለመታየትን የመረጣችሁ ካህናት ሰባክያንና ጳጳሳትም፤ በጣሊያን ጊዜ ጣሊያንን ላለመስቀየም ዝም ያሉትንና ከህዝብ መካከል የተደበቁትን የካህናትን ዝምታ ደገማችሁ። የተደገመ ነው ብልም፤ ወያኔዎች በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚፈጽሙት መከራና ግፍ፤ ጣሊያኖች ከፈጸሙት መከራና ስቃይ ጋራ ስናነጻጽረው፤ ወያኔዎች የፈጸሙት ከተመሳሳይነቱ እጅግ የራቀ፤ የባሰና የከፋ እንደሆነ፤ በዚህ ዘመን ዝም ያላችሁትንና፤ ከህዝብ መካከል የተደበቃችሁትን ካህናት፤ በጣሊያን ጊዜ ዝም ካሉትና ከህዝብ ከተደበቁት ካህናት እጅግ በጣም የከፋችሁና የባሳችሁ ናችሁ።……”

ሙሉውን ጽሑፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። ትድረስ በዚህ ዘመን ላላችሁ ካህናት

[email protected]

ሐምሌ 30 ቀን 2008 ዓ.ም.