ህዝብ እያለቀ ዳንኪራ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ይሄ የትግራይ ፌስቲቫል ነው። የተለያዩ ዘፈኖች በአማርኛ፣ በጉራጌኛ በትግሪኛ …እየቀረቡ በአዳራሹ የተገኘው የህወሃት ደጋፊ እየጨፈረ ነው። ዳንኪራ በዳንኪራ ሆነዋል። በጎንደር እና በጎጃም ህዝቡ እያወለቀ የጣለውን ኮከብ ያለበትን ባንዲራ እያወለበለቡ ነው የሚጨፍሩት። አንዳንድ ሴቶችን”ትግራዊነት ኩራት ነው” የሚል ያለበት የአበሻ ቀሚስ አደርገው እስክስታ ሲሉም ነበር።
መዝናናቱ፣ መጨፈሩ ..ችግር የለውም። በአገር ቤት በኦሮሚያ በጎንደር፣ በጎጃም እነርሱ በሚደገፉት የሕወሃት ታጣቂዎች በተተኮሰ ጥይት እንደ ቅጠል ኢትዮጵያዉያን እየረገፉ፣ ሁሉም በየ አብያተ ክርስቲያናቱ በየጸሎት ቤት ጸሎት እያደረገ ባለበት ወቅት፣ ህዝቡ ሁሉ በጭንቀት በተወጠረበት ወቅት በዚህ ቀን እንማ በዚህ መልክ መጨፈር ግን አሳዛኝ ነው።
ልክ ናቸው ትግሬነት የሚያኮራ ነው። ትግሬነት ማለት ኢትዮጵያዊነት ማለት ነው። ሆኖም ግን ከዘር ጋር በተገናኘ ነገሮች በከረሩበት ወቅት፣ ዘር ላይ ከማተኮር በተቻለ መጠን የሕዝቡ አንድነትና ዝምድና ላይ ማተኮር ሲገባ አሁኢን ዘረኘነትን ማቀንቀ አሳፋሪ ነው።
እነዚህ በዉጭ የተቀመጡ የህወሃት ሰዎች አብዛኞቹ ወይ ሌላው ኢትዮጵያዊን ለመሰለል ከሕዝብ ገንዘብ በዶላር እየተከፈላቸው የኤምባሲ ሰራተኞች የሆኑ፤ አሊያም የስርዓቱ ተጠቃሚዎች የሆኑ ናቸው። በምንም መስፈርትና ሚዛን በሕወሃቶች መከራዉን እና ፍዳዉን እያየ ያለውን የትግራይ ህዝብ አይወከሉም።
https://www.facebook.com/alulasolomonk/videos/1082282748476030/
https://www.facebook.com/alulasolomonk/videos/1082258805145091/