አዲስ አበባን ጨምሮ ኦሮሚያ ክልል በሰላማዊ ሰልፈኞች ሲጨናነቅ አማራ ክልል ደግሞ የጦርነት ቀጠና ሆነው ውለዋል። (ሙሉ ሪፖርት በምስልና ቪድዮ የተደገፈ)


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


አዲስ አበባን ጨምሮ ኦሮሚያ ክልል በሰላማዊ ሰልፈኞች ሲጨናነቅ አማራ ክልል ደግሞ የጦርነት ቀጠና ሆነው ውለዋል። (ሙሉ ሪፖርት በምስልና ቪድዮ የተደገፈ)

በኦሮሚያ ክልል የሰላማዊ ሰልፍ ግንባር ቀደሙ ሻሸመኔ ነበር፥ የኦሮሞ ሕዝቦች ለነጻነታቸውና መብታቸውን ለማስከበር በሚያደርጉት ትግል ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖቻቸው ጋር በመሆን ዋና ከተማዋን አዲስ አበባ ጨምሮ የኦሮሚያን ክልል በሰላማዊ ሰልፍ ሲያደምቁት ውለዋል።

የኣዲስ ኣበባ ውሎ ዛሬ የአዲስ አበባ ፖሊሶች በተናጠል የሚሄደውን ሰልፈኛ እየተደበቁ እየያዙ ጭካኔ በተሞላበት እንደልማዳቸው እየደበደቡና እያፈኑ ነበር።መስቀል አደባባይ ግራና ቀኝ መንገዶች ሰልፍ የወጡ ሰዎች በፖሊስ እገታ ላይ ነበር።ጥቂት ጥቂት እያደረጉ አስቀምጠዋቸዋል። ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሊወስዱዋቸው ነው። አሁንም ሰዎችን እየለቀሙ እያሰሩ ነበር። አዲስ አበባ ስቴዲየም ዙሪያ ያለው የፌደራል ፖሊስ ብዛት ሲታይ ፖሊሶች ራሳቸው ሰልፍ የወጡ ይመስላሉነበር።አብዮት አደባባይ የሚያስገቡ መንገዶች በሙሉ በፖሊስ ተዘግተዋልነበር። እግረኞች ወደ የት እንደሚሄዱ እየተጠየቁ እንዲመለሱ እየተደረጉ ይገኛሉ። ቁጥራቸው በዛ ያሉ ሰዎች በፖሊስ ተይዘዋል። ብሔራዊ ቴአትር አከባቢ ተሰባስበው ሲጓዙ የነበሩ ወጣቶች በፖሊስ ከፍተኛ ድብደባ ሲፈፀምባቸው ተመልክተናል። ወጣቶቹ በድብደባ ብዛት ራሳቸው ስተው ወድቀዋል ነበር።

Minilik Salsawi's photo.
Minilik Salsawi's photo.
Minilik Salsawi's photo.
Minilik Salsawi's photo.
Minilik Salsawi's photo.

 

 

በምእራብ ወለጋ ጊዳ አያና ወረዳ ህዝቡ ተቃውሞውን አስምቶዋል

Hamza Borana's photo.

Hamza Borana's photo.

ደሴ በቅስቀሳ ላይ የነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ ኣባላትን መታሰር ተከትሎ ፖሊስ ጣቢያ በሕዝቡ ማስጠንቀቂያ የደረሰው ሲሆን ውጥረቱ ኣይሏል። ‪#‎MinilikSalsawi‬

ጎንደር፣ ደብረ ታቦር፣ ጋይንት
ጎንደር የጦር ቀጠና እንደሆነች ነው፤ ዐማሮች ዛሬም ለተጋድሎ ወጥተዋል
• ደብረታቦር ሰላማዊ ሊባል በሚችል መልኩ ተጋድሎው እየተከናወነ ነው
• በጋይንት ሕዝብና ፖሊስ ተፋጧል
ጎንደር፡ በጎንደር ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ አለ፡፡ 18 መስጊድ፣ አራዳና ፒያሳ ከፍተኛ የተኩስ ድምጽ የሚሰማባቸው አካባቢዎች ናቸው፡፡ የጎንደር ከተማ ወጣቶች ዛሬም ገንፍለው ለተጋድሎ ሰልፍ ወጥተዋል፡፡ የወያኔ መከላከያ ሠራዊት በንጹሐን ዜጎች ላይ ጥይት እየተኮሰ ነው፡፡ የዐማራ ወጣቶች የጥይትና የአስለቃሽ ጪሱ ብዛት ሳይበግራቸው ተጋድሏቸውን እያሰሙ ነው፡፡ በጎንደር ከተማ እጅግ ብዛት ያለው የመከላከያና የፌደራል ፖሊስ እንደፈሰሰ ነው ከቦታው ያገኘነው መረጃ የሚያመለክተው፡፡

Minilik Salsawi's photo.

ደብረታቦር፡ በደብረ ታቦር ከተማ በታሪኳ ታይቶ

የማይታወቅ የዐማራ ተጋድሎ ሰልፍ እየተካሔደ ነው፡፡ ምን ያክል ሕዝብ ተጋድሎውን እንደተቀላቀለ ለአቀረብንላቸው ጥያቄ ‹‹እስካሁን በደብረ ታቦር እንዲህ ያለ የተጋድሎ ሰልፍ አይቼ አላውቅም፤ የከተማውም የፋርጣም ገበሬ የቀረ አይመስለኝም›› ሲሉ አንድ ተሳታፊ መልስ ሰጥተዋል፡፡ የወያኔ የፌደራል ፖሊስ አስለቃሽ ጪስ ወደ ወጣቶች ሲተኩስ ወደያውኑ ተበትነው እልፍ ብለው ተጋድሏቸውን እንደሚጀምሩ ነው የተገለጸው፡፡ በጠዋት 12 ሰአት በትንሽ ወጣቶች የተጀመረው የተቃውሞ ሰልፍ አሁን ላይ ከሕጻን እስካ አዋቂ፣ ሴት፣ ወንድ፣ ደካማ አዛውንት ሳይል ሰልፉን ሁሉም ተቀላቅሏል፡፡ የጋሳይ እና የክምር ድንጋይ ከተማ ነዋሪዎች የደብረ ታቦሩን ተጋድሎ ለመቀላቀል ቢሞክሩም በወያኔ ታጣቂዎች ታግደዋል፡፡ ሆኖም ባሉበት ሆነው ተጋድሏቸውን እያሰሙ ነው፡፡ ከሞክሼ የመጡት የታጠቁ ገበሬዎች የወያኔን ወታደር ጥሰው ደብረ ታቦር መግባታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በደብረ ታቦር እስካሁን በሰውና በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም፡፡


ነፋስ መውጫ፡ የጋይንት ሕዝብ ዛሬ በማለዳው ነው የተጋድሎ ሰልፉን የተቀላቀለው፡፡ የጋይንት ዐማሮች ትናንት ሰልፍ ያስተባብራሉ ተብለው የታሰቡትን በወያኔ ቅጥረኞች የታሰሩ ወጣቶችን ማስፈታታቸው ታውቋል፡፡ የአየር ንብረቱ ዝናባማ ቢሆንም የጋይንትን የተቆጣ ዐማራ ሊያስቆም የሚችል አልነበረም፡፡ የጋይንት ዐማሮች ድምጽ ጨጭሆን አልፎ ወደ መቄትና ዋድላ ደላንታ መድረሱን ነው የምንሰማው፡፡ በነፋስ መውጫ የቅጥረኛ ፖሊሶች እርምጃ ሕዝቡን የበለጠ አስቆጥቶ ወደ ማይመለስ ግጭት እንዳይገባ ስጋት አለ፡፡
ይህ ሁሉ የመጨረሻው መጀመሪያ ነው!!

Minilik Salsawi's photo.
Hamza Borana's photo.
Hamza Borana's photo.