የእኔ ስጋት – ልብ ያለው ልብ ይበል !! በአብይ አበበ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
አለመታደል ሆኖ ሃገራችን የምትኖረው ተነጋግሮ ችግሮችን መፍታት እንደነውር በሚቆጠርበት ፤ እንዲሁም ፖለቲካዊ መፍትሄዎች ሁሉ የጠመንጃ ጉልበት የበላይነት በሆነበት የ ምስራቅ አፍሪካ ቀንድ ቀጠና ውስጥ ነው . ይህ ቀጠና የአፍሪካው ረጅም የእርስ በርስ ጦርነት የተደረገበት [ደቡብ ሱዳንን ከሰሜኑ የነጠለው እንዲሁም እስካሁን ድረስ ሰላም ያልሰፈነበት የዳርፉር ግዛት አፍሪካዊ ህዝብ በካርቱም የአረብ መንግስት ላይ ያመጸበት ] [ ከ 30 አመት በላይ የፈጀው እና ውጤቱም ኤርትራን በማስገንጠል እና ቀሪዋን ኢትዮጵያንም ከ Unitary State ወደ Federal State (ቁዋንቁዋን መሰረት ያደረገ ) የቀየረው የእርስበርስ ግጭት ቀጠናም ጭምር ነው .
በቅርብ ግዜ እንኩዋን አዲስ ሃገር ሆና ብቅ ያለችው #ደቡብ_ሱዳን በፖለቲከኞችዋ ራስ ወዳድነት እንዲሁም የዘቀጠ ዘረኝነት አስተሳሰብ የተነሳ : ይህም በፈጠረው አለመተማመን ምክንያት የህዝቡን ህልውና እንዲሁም የሃገሪቱን የግዛት አንድነት እንደ ቁማር ማስያዣ እየተጠቀሙበት ሰላም ከራቃቸው ቆየ።
እኛም ይሕው የውስጥ ችግሮቻችንን በግዜ ሁሉንም ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ ካልፈታነው ፤ በፖለቲካው ልንሄድ የምንችለው የቁልቁለት ጉዞ ራስን ማጥፋት እንዳይሆንብን እሰጋለሁ .
#1. ፌደራሊዝሙ ሁሉም ሳይሳተፍበት ፤ ያለምንም ታሪካዊ ዳራ በድንበር የተካለሉት ክልሎች እየተነሳ ያለው የመሬት ይገባኛል እንዲሁም ” የማንነት ” ጥያቄዎች በአንድ በኩል
#2. በእየአካባቢው የተንሰራፋው የመልካም አስተዳደር ችግር
#3. ሙስና
#4. የፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል ጥያቄዎች
#5. የፖለቲካ ፓርቲዎች በነጻነት ያለመንቀሳቀስ ችግር
ወዘተረፈ ………
በዚህም ላይ ደግሞ ሃላፊነት ይሰማቸዋል ብዬ በግሌ የማስባቸው በተቃዋሚ ጎራ የነበሩ ግለሰቦች “በእስር መማቀቅ ” ምን አልባት የስልጣን ክፍተት ቢፈጠር እንኩዋን በነውጥ መንጋ እንዳንመራ እና እንደገና ወደሁዋላ እንዳንሄድ እሰጋለሁ።
እነዚህ ሁሉ ትልቅ ማነቆ ሆነውብን እንዚህን ፍትሃዊ ጥያቄዎች ለሚጠይቁትን ደግሞ #መንግስት ምላሹ የሃይል እርምጃ እየሆነ ነገሮች እየተካረሩ እየተካረሩ በመጡ ቁጥር ደግሞ ወደ ግጭት እየተገባ : በዚህም ደግሞ የሰው ህይወት እየገበርን ለቀጣይ ትውልድም የማይሽር ቂም እና በቀሎችን እያስቀመጥን እየሄድን እንዳለን ይሰማኝ ጀምሮዋል።
====================================
#ሶርያን እንደ ሞዴል ?
====================================
በመካከለኛው ምስራቅ የምትገኘው #ሶሪያ እንደዛ ውብ ሃገር እንዳልነበረች ሁሉ ነገር ግን#የሶሪያው_ገዢ__መደብ በሃገሪቱ ላይ #የአናሳዎችን_የበላይነት ኢኮኖሚውንም ሚሊታሪውንም በጥቂቶቹ 8% የሺያ አልዋይቲዎች (ይህ ብሄር ሳይሆን የእምነት ሴክት መሆኑን ልብ ይሏል ) ቁጥጥር ስር በማድረግ የውስጥ ችግሩዋን በውይይት እንዲሁም በህዝብ ይሁንታ መፍታት ተስኖት ፣ የህዝብን የዴሞክራሲ ጥያቄ መመለስን እንደነውር ቆጥሮ ፣ ይህን ወቅት ለራሳቸው አላማ ለመጠቀም ቀን ሲጠብቁ ለነበሩ #ለውጪ_ሃይሎችም ” ትልቅ በር ” በመክፈት ሃገሪቱዋን ወደማያባራ የ Secterian War የርስ በርስ ጦርነት በማስገባት ውብ የነበሩት ከተሞቹዋ ወደ ፍርስራሽነት ፤ ከ 250,000 – 400,000 የሚደርሱ ዜጎችዋን ህይወት ገብሮ እንዲሁም በሚልየን የሚቆጠሩ ዜጎችዋን ለአካል ጉዳተኝነት ዳርጎ እና በአለም ላይ ቁጥር 1 ስደተኛ አድርጎ ይሕው በ Arab Spring (የአረብ ጸደይ አብዮት ) ጀምሮ እስካሁንም 5 አምስት አመት ጦርነት ላይ ትገኛለች ሶሪያ ( #Syria )
====================================
በቅርብ የሚታየኝ መፍትሄ #Abiy1702
====================================
በኢህአዴግ መሪነት ስልጣን ላይ ያለው መንግስት ሃገሪቱዋን ያልምንም ኪሳራ ወደተሻለ መንገድ ለመውሰድ ቁልፉ በእጁ ነው !!!! በተለያዩ አካባቢዎች እጅግ ግዙፍ የተቃውሞ ድምጾችን እየሰማን እንገኛለን ፡፡ ይህ የህዝቦች ድምጽ መሆኑ ላይም አንዳች የጥያቄ ምልክት ሊኖር አይችልም !!!! ህዝብ ሊሳሳት አይችልምና !!!!!
ከሃገሪቱ ህልውና ፤ ከሃገሪቱ ህዝብ አንድነት (Peoples Unity) ፤ ከሃገሪቱ የግዛት አንድነት ደህንነት ( Territorial Integrity ) አንጻር በተቆርቁዋሪነት ከታሰበ የዚህን ህዝብ ፍላጎት “ከስልጣን ጥም” በራቀ ሁኔታ ማየት እና የዚህ ህዝብ የላቀ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ #የህዝቡ_ድምጽ_ሊሰማ_ይገባል !!!