ሕዝብ በማያውቀው ሕግ ገዢ ነን ባዮች ሊመሩት አይችሉም። ሰልፉ ኣይቀሬ ነው።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ሕዝብ በማያውቀው ሕግ ገዢ ነን ባዮች ሊመሩት አይችሉም። ሰልፉ ኣይቀሬ ነው።
#Ethiopia #Oromoprotests #Amharaprotests #Demonstration #MinilikSalsawi
Minilik Salsawi – mereja.com በኦሮሚያ ክልል ለቅዳሜ ሐምሌ 30 2008 ታላቅ ሕዝባዊና ሰልማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ተጠርቷል። ይህን ጥሪ ተከትሎ የኦሮሚያው ክልል የወያኔ ወኪል ሙክታር ከድር በኦሮምያ ክልል እውቅና የሰጠነው ስልፍ የለም በማለት መናገሩ ተሰምቷል። ሰልፉ ኣልተፈቀደም በሚል ብቻ የሕዝብን መብት እጋፋለሁ የሚል የሕወሓት ኣገዛዝ ኣካል ቢኖር ዋጋ ያስከፍለዋል፥ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ሕዝቦች ነጻነታቸውን እና መብታቸውን ለማስከበር የምንንም ድጋፍ እና ፈቃደኘት ኣይፈልጉም በጎንደር የተካሄደው እና በሚሊዮኖች የተሳተፉበት ሰልፍ ኣልተፈቀደም በሚል ሕወሓትና ኣሽከሮቹ ቢደነፉም የሕዝብ የበላይነት በኣሸናፊነት ገኖ ሕወሓት እንደሚመኘው በደም መፋሰስ ሳይሆን በሰላማዊነት ተጠናቋል።

በኦሮሚያ ክልልም ሕዝብ በገዛ ኣገሩ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ማድረግ ከፈለገ የምንም ፈቃድ እና ድጋፍን ኣይፈልግም የህዝብ ሃይል ታላቅ ድልን እንደሚያጎናጽፍ ዛሬ ላይ በመሳሪያ ሃይል የሚመኩ ነገን እንደሚዋረዱ ሊያውቁና ሕዝብም የድል ባለቤት እንደሆነ ሊያውቁ ግድ ይላቸዋል። ሰልፉ ኣልተፈቀደም በሚል ብቻ የሕዝብን መብት እጋፋለሁ የሚል የሕወሓት ኣገዛዝ ኣካል ቢኖር ዋጋ ያስከፍለዋል፥ እያስጠነቀቅ ያለነው በጎንደር እንደተካሄደው ሁሉ በኦሮሚያ እና በባህር ዳርም የሚካሄደው ሰልፍ በሕዝብ የበላይነት ስለሚመራ ሰላማዊ እና እንከን የሌለበት ታላቅ ሰልፍ ነው፤ይሆናልም።
ስለዚህ ሕወሓትም ሆኑ ኣሽከሮቹ ብአዴንና ኦሕዴድ በሕዝብ ላይ የሚያደርጉትን ዛቻ ኣቁመው እጃቸውን ሰብስበው በመቀመጥ የሕዝብን ጥያቄ ኣድምጠው ስልጣን ለሕዝብ እንዲያስረክቡ ይፈለግባቸዋል።የወያኔ የጎሳ ፖለቲካ ኣገሪቷል ለመበጥበጥ የማይቆፍረው ጉድጓድ እንዳሌለ ይታውቃል በዚህ ጉድጓድ ግን የሚቀበረው ራሱ ወያኔ መሆኑን ሊያውቅ ይገባል። የፊታችን ቅዳሜ በመላው ኦሮሚያና እሁድ በባህር ዳር እና በሌሎች ከተሞች የሚደረጉ ሰልፎች በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይፈጸማሉ።ሞት ለወያኔና ኣሽከሮቹ። #ምንሊክሳልሳዊ