የመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ መዘግየት ለችግር እያጋለጣቸው መሆኑን ገለፁ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ መዘግየት ለችግር እያጋለጣቸው መሆኑን ገለፁ
በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሚሰሩ ስራተኞች ወርሃዊ ደሞዝ ከሚከፈላቸው ግዜ በላይ በመዘግየቱ የተነሳ ለችግር እየተጋለጡ መሆኑን እየገለፁ እንደሚገኙ ሰራተኞቹን ዋቢ ያደረጉ ምንጮቻችን ገልፀዋል ፡፡
እንደምንጮቻችን ገለፃ በአዲስ አበባ ገቢዎችና ጉምሩክ የሚሰሩ ሰራተኞች ወርሃዊ ደሞዛቸው የሚከፈላቸው ወር በገባ እስከ 22 ቀን ባለው ግዜ ውስጥ እንደሆንና ምክንያቱ ባልታወቀ ምክንያት ግን የዚህ ወር ደሞዛቸው ባልተለመደ ሁኔታ እስካሁን ባለመከፈላቸው ለችግር መዳረጋቸውን የገለፁ ሲሆን በተያያዘ ሁኔታ በአማራ ክልል በደብረማርቆስ ከተማ የሚገኙ የመንግስት ስራተኞች ደሞዛቸው ሊከፈላቸው ባለመቻሉ ለችግር መጋለጣቸውን እየገለፁ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሎዋል፡፡