­

ህዝባዊ ትግል ማገዝ እንጂ ማደናቀፍ የሃቀኛ ፓርቲ መገለጫ አይደለም!


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በተለይ ሰማያዊ ፓርቲ ህዝባዊ ትግል ለማገዝና ለመምራት በእውነተኛ የለውጥ ፈላጊ አመራሮችና አባላቶች በተከፈለና ወደፊትም በሚከፈል መሰዋዕትነት የቆመ ፓርቲ ነው።ይህ ሁሉ የሚሆነው የህዝብ ጥያቄ ትክክለኛ ምላሽ እንዲያገኝ ነው። ይህም በመሆኑ በአገራችን በአራቱም አቅጣጫ በአገዛዙ ሥርዓት ላይ የተነሣው ህዝባዊ ተቃውሞ “የእኔ ነው ፣የእኔ” ዓይነት ለአምባገነኑ አገዛዙ የሚመች፣ የለውጥ ፈላጊው አንድ ስንዝር የማያራምድ ባለህበት እርገጥ፣ አሰልቺ ፓለቲካ የእኔን ትውልድ የማይመጥን ፤ከምንም በላይ ደግሞ የአገራችንን ነበራዊ ሁኔት እንደ-መርሳት የሚቆጠር ጭምር ነው። ሰማያዊ ፓርቲ በውስጣዊ ችግሮቹ ለላፋቱ ወራት ታች-ላይ ማላቱ ለማንም ግልፅ ነው።

አሁን ላይ ችግሮቹን ለይቶ ህዝባዊ ትግሉን ለማገዝና ለመምራት ሥራዎቹን እያጠናቀቀ ይገኛል።ከችግሮቹ ወጥቶ ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲደርስ የፓርቲው ከፍተኛ አመራርና አባላት ያደረጉት በጎ አሰተዋአዖኦ ወደፊት በፓርቲያችን ታሪክ እንደ ማሳያ የሚጠቀስ ነው። በፓርቲያችን ውስጥ ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት ሲያስጨንቃቸው እና ሲያሳስባቸው የነበረ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊን ስለ ፓርቲያችን መልካም ዜና የሚሰሙበት ቀን እሩቅ አይደለም ። ከላይ ለገለጽኩት ለመልካሙ ዜና እና ለበጎ ምኞቴ የአመራሩና የአባላቱ ጥረት ታሳቢ በማድረግ ብቻና፣ ብቻ! ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ ወደ ተነሳውበት ሃሳብ ስመለስ፣ ህዝባዊ ትግል ማገዝ እንጂ ማደናቀፍ የሃቀኛ ፓርቲ መገለጫ አይደለም! የሚለው የጽሑፊ መግቢያ፣ ለሰማያዊ ፓርቲ ሙሉ በሙሉ የሚያገለግል ነው።

ፓርቲያችንም የአገዛዙ ሥርዓት ከምስረታው ጀምሮ ከህዝብ ጎን በመቆም ሲታግልና ሲያትግል እንጂ ለደቂቃም ቢሆን ያደናቀፈበት የትኛው ዓይነት አጋጣሚ የለም፣ወደፊትም አይኖርም። በዚህም መሰረት በአገራችን የሚካሄደው ህዝባዊ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፎች ፓርቲያችን እንደ-አግባቡ እና አስፈላጊናቱ እውቅና በመስጠት ፣ ህዝብ በራስ ተነሳሽነት የጀመረውን ሰላማዊ የትግል እንቅስቃሴ ለእራሱ ለባለቤቱ (ለህዝብ) ቅድሚያ መሰጠት አለበት ብዬ አምናለሁ ።ምክንያቱም ጥቅሙ ብዙ ስለሆነ። ፓርቲ ህዝብን እንጂ፣ እንዴት ህዝብ ፓርቲን ይመራል፤ ከሚባለው ሃስተሳሰብ ይሄኛው መንገድ በብዙ መልኩ ይለያል። መንገዱ አይለይም ቢባል እንኳን አሁን ላይ ያለው ተጨባጭ ሁኔታ ታሣቢ መደረገ አለበት። በዚህም መሰረት ፓርቲያችን የህዝቡ ሰላማዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴ በንቃት በመከታተል፣ ተገቢውን ድጋፍ በመስጠት ፣ጠንካራና ደካማ ጎን በመለየት ፓርቲው በራሱ ለሚያደርጋቸው እንቅስቃሴ እንደ-ማመላከቻ ሊወስዳቸው ይገባል የሚል (የግል) ምልከታ አለኝ። ምልክታዬን ለሚጋራኝ ይሄን ለማድረግ አሁንም ጊዜው አልረፈደም ! የፓርቲው የሥራ አስፈፃሚ አባላት ወቅታዊ የአገራችን ሁኔታ እና የህዝቡ ሰላማዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴ በአግባቡ መርምረው ፤በፓርቲያችን ላይ የተፈጠረውን ብዥታ በማከም ፣ በአገራችን በሁሉም አካባቢ የተጀመረው ህዝባዊ እንቅስቃሴ ከፓርቲያችን ፕሮግራም ጋር በተጣጠመ መልኩ የሚያግዝ እና አቅጣጫ የሚያሲዝ ውሳኔ በአስቸኳይ እንደሚያሳልፉ ተስፋ አደርጋለሁ ። የኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!

Yidinekachew kebede