በቃ አየህ ሲያስፈልግ ዝም ብለህ ታወራለህ፡፡ የኛ ሕዝብ ትያትር ይወዳል፡፡ የወያኔው ሚኒስትርና የኣሜሪካ ምርጫ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


 

  • በቃ አየህ ሲያስፈልግ ዝም ብለህ ታወራለህ፡፡
  • ለማንኛውም እኔ ያልኩዎት ይኼንን ነው፡፡
  • ምንድን ነው ያልከኝ?
  • የአሜሪካ ምርጫ ቴአትር አይደለም፡፡
  • የእኛ ቴአትር ነው እያልከኝ ነው?
  • እህሳ፡፡
  • ግን ለምን ቴአትር እንደሆነ ታውቃለህ?
  • አላውቅም፡፡
  • በሕዝቡ ፍላጐት ነዋ፡፡

 

[የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ ቢሮ ቁጭ ብሎ የአሜሪካንን ምርጫ በቲቪ እየተከታተለ ነው፡፡ ክቡር ሚኒስትሩ ስልክ ደወሉለት]

  • አቤት ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • በአስቸኳይ ቢሮ ና፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር ቲቪ እየተከታተልኩ ነበር፡፡
  • ስማ በሥራ ሰዓት ዛራና ቻንድራ ታይልኛለህ?
  • ኧረ ሌላ የሥራ ጉዳይ ነው እየተከታተልኩ ያለሁት፡፡
  • ምን አሁን ኢቢሲ ላይ ምን አጓጊ ነገር ኖሮ ነው?
  • አይ የአሜሪካን ምርጫ እየተከታተልኩኝ ነው፡፡
  • እኔ ጠፋሁ!
  • ምነው?
  • ዋነኛው ኒዮሊብራሊስት አጠገቤ ተቀምጦ ኖሯላ?
  • እንዴት ክቡር ሚኒስትር?
  • የእነሱን ምርጫ ምን ሊያደርግልህ ነው የምትከታተለው?
  • ከእነሱ እኮ ብዙ የምንማረው ነገር አለ፡፡
  • እየቀለድክ ነው?
  • ኧረ የእውነቴን ነው፡፡
  • አሁን ማን ይሙት እነሱ ከእኛ ይማራሉ እንጂ እኛ ከእነርሱ እንማራለን?
  • እነሱ ደግሞ ከእኛ ምን ይማራሉ?
  • ለምሳሌ ምርጫ መድፈን እንደሚቻል፡፡
  • ብለው ነው?
  • እህሳ? ከእነሱ ግን ምን መማር እንችላለን?
  • ለምሳሌ ባለፈው ለመጀመሪያ ጊዜ በአሜሪካ ጥቁር ፕሬዚዳንት ሥልጣን ይዟል፡፡
  • እኛስ ለመጀመሪያ ጊዜ 100 በመቶ ወንበር ይዘናል አይደል?
  • ከዚያም ባለፈ አሁን ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት ፕሬዚዳንት ልትሆን ትችላለች፡፡
  • እኛም እኮ በፓርላማ ባሉን ሴቶች ብዛት ከአፍሪካ አንደኛ ነን፡፡
  • ቢሆንም አሜሪካ እኮ ሴት ፕሬዚዳንት ሊኖራት ይችላል እያልኩዎት ነው?
  • ግን ያ እንዴት ሊሆን ይችላል?
  • ምን ችግር አለው?
  • ሴት የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ልትሆን?
  • ለምን አትሆንም?
  • ያው ትንሽ …
  • ክቡር ሚኒስትር ሴቶች ኢምፓወር መደረግ አለባቸው እያሉ በየቦታው ሲያወሩ አልነበር እንዴ?
  • የምታወራውን ሁሉ ታደርገዋለህ ማለት አይደለም፡፡
  • እኮ እንዴት?
  • በቃ አየህ ሲያስፈልግ ዝም ብለህ ታወራለህ፡፡
  • ለማንኛውም እኔ ያልኩዎት ይኼንን ነው፡፡
  • ምንድን ነው ያልከኝ?
  • የአሜሪካ ምርጫ ቴአትር አይደለም፡፡
  • የእኛ ቴአትር ነው እያልከኝ ነው?
  • እህሳ፡፡
  • ግን ለምን ቴአትር እንደሆነ ታውቃለህ?
  • አላውቅም፡፡
  • በሕዝቡ ፍላጐት ነዋ፡፡
  • እንዴት ሆኖ?
  • በየቴአትር ቤቱና ሲኒማ ቤቱ ሕዝብ እንዴት እንደሚሰለፍ አይተሃል?
  • በደንብ አይቻለሁ፡፡
  • ስለዚህ ሕዝብ ቴአትር ይወዳል ማለት ነው፡፡
  • እ…
  • አየህ ምርጫው ላይም የነበረውን ሰልፍ ታስታውሰዋለህ?
  • አዎን፡፡
  • በቃ ስለዚህ ለዛ ነው የሕዝቡ ፍላጐት ቴአትር ነው ያልኩህ?
  • የአሜሪካ ምርጫ ግን ቴአትር አይደለም፡፡
  • ነው እንጂ፡፡
  • እንዴት ሆኖ?
  • ለፕሬዚዳንትነት የሚወዳደረው የቲቪ ሾው የነበረው አክተር አይደል እንዴ?
  • ዶናልድ ትራምፕን ነው?
  • ታዲያስ እሱ አክተር/ፖለቲከኛ ነው፡፡
  • እርስዎ ግን ምን እንደሆኑ ያውቃሉ?
  • ምንድን ነኝ?
  • ኮሜዲያን/አክተር!

[የክቡር ሚኒስትሩ ልጅ ስልክ ደወለላቸው]

  • ዳዲዬ!
  • ወዬ፡፡
  • ና በእናትህ፡፡
  • ምን ሆነህ ነው?
  • ምን እዚህ…
  • አፍህ እየተኮላተፈ ነው፡፡
  • አንድ ጌ…ጃ… ትራፊክ…
  • ምንድን ነው የምታወራው?
  • እዚህ…
  • ጠጥተሃል እንዴ?
  • ትንሽ… ነው… የቀማመስኩት፡፡
  • ምን?
  • አንድ… ሦስት… ብርጭቆ… ዊስኪ ናት፡፡
  • የት ነው ያለኸው?
  • የሆነ የሚያስጠላ… ቦታ ነው፡፡
  • ሰክረህ ነው?
  • በእናትህ… ዳዲ… አታካብድ፡፡
  • ጠጥተሃል ወይ?
  • ትንሽ… ነው… የቀመስኩት፡፡
  • አጠገብህ ማን አለ?
  • እንካ አናግረው፡፡

[የጣቢያው አዛዥ ከክቡር ሚኒስትሩ ጋር ማውራት ጀመረ]

  • ሄሎ!
  • ማን ልበል?
  • ማን ልበል ነው ያልከኝ?
  • አዎን ጌታዬ፡፡
  • በእርግጥ ጌታህ ነኝ፡፡
  • ምንድን?
  • ክቡር ሚኒስትር ነኝ፡፡
  • እንዴ ክቡር ሚኒስትር?
  • እንዴት ሆኖ ነው ልጄን ያሰርከው?
  • እኔ መቼ አወቅኩ?
  • ሥራህ ምን ሆነና?
  • የትራንስፖርቱን ሥርዓት ማስከበር ነዋ፡፡
  • ከዛ በፊት ማድረግ ያለብህ ነገር አለ፡፡
  • ምንድን ነው?
  • የእኔ ቤተሰቦችን ማንነትና ምንነት ማወቅ፡፡
  • እሱ የሥራ ኃላፊነቴ ውስጥ እንዳለ አላውቅም ነበር፡፡
  • ለዚህ ደግሞ ትቀጣለህ፡፡
  • ኧረ ይቅርታ ጌታዬ፡፡
  • ምን አድርጐ ነው ልጄ?
  • ጠጥቶ ሲያሽከረክር ተይዞ ነው፡፡
  • እኮ በአስቸኳይ ይለቀቅ፡፡
  • ሕግ ጥሷል ግን፡፡
  • እኔ ጠፋሁ፡፡
  • በዛ ላይ አንደር ኤጅ ነው፡፡
  • አዋልደኸዋል አንተ?
  • እንደሱ ማለቴ አይደለም፡፡
  • እኮ በአስቸኳይ ልቀቀው፡፡
  • ቤት ማን ያደርሰዋል?
  • አንተ ምን ትሠራለህ?
  • እሺ አደርሰዋለሁ፡፡
  • ከዛ እኔና አንተ እንገናኛለን፡፡
  • ምን ለማድረግ?
  • እየጠጣን ለማውራት!

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሾፌራቸው ጋር ወደ ቤት እየሄዱ ነው]

  • ምን ሆነህ ነው አንተ?
  • ጉንፋን ይዞኛል ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • የክረምቱ ቅዝቃዜ ለነገሩ ከባድ ነው፡፡
  • ቅዝቃዜው ሳይሆን ሌላ ነው፡፡
  • ስማ ይኼ ክምር ምንድን ነው?
  • የቱ ክቡር ሚኒስትር?
  • ከተማው ውስጥ የሽምቅ ውጊያ ተጀምሯል እንዴ?
  • የምን የሽምቅ ውጊያ?
  • በየቦታው የከረጢት ክምር አያለሁ፡፡
  • እንደ እርስዎ ዓይነት ቀልደኛ ሚኒስትር አይቼ አላውቅም፡፡
  • እንዴት?
  • መቼም በየቦታው የሚያዩት የከረጢት ክምር ለድርቁ የተሰጠን ዕርዳታ ነው አልልዎትም?
  • ታዲያ ቀልደኛው ማን ነው?
  • እርሱ አይደል እንዴ ጉንፋን ያስያዘኝ?
  • ቀልዱ ነው?
  • ኧረ በየቦታው ያዩት የቆሻሻ ክምር፡፡
  • ለምንድን ነው ቆሻሻው የማይነሳው?
  • ያሳመመኝ እሱ ቀልድ ነው አልኩዎት እኮ፡፡
  • የምን ቀልድ?
  • የቆሻሻ ቀልድ!

[ክቡር ሚኒስትሩ የከተማው አስተዳደር አንድ ኃላፊ ጋ ደወሉ]

  • አቤት ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ልትጨርሱን ነው እንዴ?
  • በምን?
  • በጉንፋን፡፡
  • ድምፅዎት ግን ጉንፋን የያዘው ሰው አይመስልም፡፡
  • ሕዝቡ በጠቅላላ ተለክፏል አይደል እንዴ?
  • በምን ክቡር ሚኒስትር?
  • በበሽታ፡፡
  • እ…
  • ቆሻሻው ለምንድን ነው የማይደፋው?
  • አልሰሙም እንዴ?
  • ባለፈው አንድ ቢሊዮን ብር ያወጣ የቆሻሻ መጣያ ሲመረቅ ጠርታችሁኝ አልነበር እንዴ?
  • እኮ መጣል አትችሉም አሉን፡፡
  • እነማን?
  • የአካባቢው ገበሬዎች፡፡
  • ምን?
  • አዎ፣ እኛ ቆሻሻ መጣያ አይደለንም አሉ፡፡
  • እኔ ጠፋሁ፣ እና ምን አላችኋቸው?
  • ምን እንላለን?
  • ነገ ደግሞ በዚህ በኩል በመኪና ማለፍ አትችሉም ቢሉስ ምን ልትሉ ነው?
  • ምን ማለት እንችላለን ክቡር ሚኒስትር?
  • እንዴት አትችሉም?
  • ይኼ እኮ የፌደራሊዝም መዘዝ ነው፡፡
  • እኔ ጠፋሁ እና በበሽታ እንለቅ?
  • በምን በሽታ?
  • በአተት፡፡
  • እሱ እኮ ስሙ ተቀየረ፡፡
  • ምን ተባለ?
  • መተት፡፡
  • የምን አባህ መተት ነው አንተ መተተኛ?
  • አይ እሱኛውን መተት አይደለም፡፡
  • ታዲያ መተት ምንድን ነው?
  • መደበኛ ተቅማጥና ትውከት!

[ክቡር ሚኒስትሩ ቤት ሲገቡ ከሚስታቸው ጋር ማውራት ጀመሩ]

  • ሰላም ውዴ፡፡
  • እንዴት ዋልሽ ውዴ?
  • አንተን እኮ በሌላ ማዕረግ መጥራት ናፈቀኝ፡፡
  • በምን ዓይነት ማዕረግ?
  • ለምሳሌ ዶክተር ብሎ መጥራት ናፈቀኝ፡፡
  • መቼም ከዚህ በኋላ ሜዲካል ዶክተር መሆን አልችልም፡፡
  • እሱንማ አውቃለሁ፡፡
  • ወይም ደግሞ ፒኤችዲ አልማር?
  • በየትኛው አቅምህ?
  • ታዲያ ምንድን ነው የምታወሪው?
  • ጥያቄዬ የአንተ ተራ መቼ ነው የሚለው ነው?
  • የምን ተራ?
  • የክቡር ዶክትሬት የምታገኝበት ጊዜ ነዋ፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር ነኝ እኮ፡፡
  • እስቲ ክቡር ሚኒስትር ከክብር ዶክትሬት ጋር ሲሆን ያለውን ክብር አስበው፡፡
  • እሱስ ልክ ነሽ፡፡
  • የቀበሌ ሊቀመንበር ሳይቀር እየተሰጠው እኮ ነው፡፡
  • እ…
  • 12ኛ ክፍል ሳይጨርሱ በአቋራጭ ዶክተር ሲባሉ?
  • እ…
  • የሚመስለው አምስት ለአንድ እያደራጃችሁ የምትሰጡ ነው እኮ፡፡
  • ምን?
  • ታዲያ አንተ መቼ ነው የሚደርስህ?
  • በቃ ተይው መላ አለኝ፡፡
  • ምን ልታደርግ?
  • ዩኒቨርሲቲ አቋቁማለሁ፡፡
  • ምን የሚያደርግ?
  • የክቡር ዶክትሬት አዳይ!