የሕወሓት መሪዎች ኣሁንም የሕዝብን ጥያቄ ለማስተናገድ ፈቃደኞች ኣለመሆናቸውን በሚዲያዎቻቸው ዘለፋ እየመሰከሩ ነው። ስርዓቱን መገርሰስ ብቸኛ መንገድ ነው።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የሕወሓት መሪዎች ኣሁንም የሕዝብን ጥያቄ ለማስተናገድ ፈቃደኞች ኣለመሆናቸውን በሚዲያዎቻቸው ዘለፋ እየመሰከሩ ነው። ስርዓቱን መገርሰስ ብቸኛ መንገድ ነው።
Minilik Salsawi – mereja.com ይህ ሕዝብ ባላጸቀው ሕገመንግስት ባላጸደቀው ሕግ ባልመረጠው መንግስትና ፓርላማ በግዳጅ እየተመራ እንደሆነ ከግንዛቤ ልናስገባለት ይገባል። ዛሬው የጎንደርን ተቃውሞ ያልተፈቀደ ሰልፍ በማድረግ የአገሪቱ ሰንደቅ አላማ ያልሆነ ባንዲራን ማውለብለብ ህገ፡መንግስቱን የጣሱ እና የአገሪቱን አንድነት የሚሸረሽሩ ጥያቄዎችና ድርጊቶች ታዩ በማለት በሕዝብ ላይ ያላቸውን ንቀት በሚዲያዎቻቸው ኣሳይተዋል። ሕዝብ የጠየቀውን ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ ሕዝብን በሚዲያዎቻቸው በመወንጀል ተግባር ላይ ተሰማርተዋል። በሚዲያዎቻቸው የሚሊዮኖችን ጩኸት የኣንድ ተራ ሰው ወንጀል ኣድርገው ለማቅረብ ሞክረዋል።የወያኔው ኢቢሲ በበኩሉ የሕዝብን ጉዳይ ገልብጦ በመዘገብ ወያኔ በቃኽኝ በሽፍታ መንግስት ኣልመራም ሲል የዋለውን በልማት ስም የሃገርን ሃብት መዝረፍ መንግስታዊ ሽፍትነት ነው አያለ መፈክር ያሰማን ሕዝብ የልማትና የመልካም ኣስተዳደር ጥያቄ ኣቀረበ በማለት የወልቃይትን ጥያቄ ለመሸፈን ሞክሯል።ለመላው ኢትዮጵያ በደል የተጮዀን የሕዝብ ድምጽ ለማናናቅ ሞክረዋል። ኣልተሳካላቸውም እንጂ።
በሚሊዮኖች የሚቆተር የኦሮሞ ሕዝብ በሚሊዮኖች የሚቆጠር የኣማራ ሕዝብ ኣደባባይ በመውጣት ለወያኔ ኣገዛዝ በቃከን ሲል ነግሮታል ይህ ሕዝብ ባላጸቀው ሕገመንግስት ባላጸደቀው ሕግ ሕግ ባልመረጠው መንግስትና ፓርላማ በግዳጅ እየተመራ እንደሆነ ከግንዛቤ ልናስገባለት ይገባል። የባንድራ ህግ ኣሊያም ሕገመንግስት የሰላማዊ ሰልፍ ሕግ ኣሊያም ሌላ ሕግ ቢነገረው መስሚያ ጆሮ የለውም ለምን ቢባል በሕጉ ላይ ምንም ተሳትፎ የለውም።የኢትዮጵያ ሕዝብ ጨዋ ሕዝብ ስለሆነ ማንኛውንም ተቃውሞ በሰላም በፍቅርና በኣንድነት ያካሂዳል።
VIDEO
https://www.facebook.com/100007836377373/videos/1757155331222329/
የኣማራን ሕዝብ የኣገሪቱን አንድነት የሚሸረሽር ብሎ መዝለፍ ኣንድን ህዝብ እመራለሁ ከሚል ኣገዛዝ ባይጠበቅም ወያኔ ግን የሕዝብን ጥያቄ ሁሉ እንደ እሾህ ስለሚመለከት በፍጹም መልስ ለመስጠት ኣይፈልግም ይልቁኑ ሕዝቦችን በገዛ ኣገራቸው ባልሰሩት ወንጀል መብታቸውን ብቻ ስለጠየቁ አሸባሪ ተብለው ወህኒ ይወርዳሉ።ሕወሓት በሚዲያዎቹ በኩል ሕዝብን መዝለፍ እና መወንጀል ማቆም ኣለበት።ስልጣኑንም ለሕዝብ ኣስረክቦ ሕዝቡ ለጥያቄዎቹ መፍት ሄና መልስ ቢያበጅለት የተሻል ይሆናል ካልሆነ ግን ሕዝቡ በጋራ ቆሞ በኣገዛዙ ላይ ከባድ ክንዱን ሲያሳርፍ ከባድ ኣደጋ እንዳለ ማወቅ ግድ ይላል። #ምንሊክሳልሳዊ