የጎንደሩ ትዕይንተ ሕዝብ የህወሃትን መውደቅ አይቀሬትን ያረጋገጠ ነበር፣ ቪዲዮ ይመልከቱ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በዛሬው ዕለት በጎንደር ከተማ ሁልቆ መስፍርት የሌለው ሕዝብ ወደ አደባባይ ወጥቶ በመትመም ህወሃት በአገሪቱ  ውስጥ የሚያደርገውን የመብት ጥሰት በከፍተኛ ቁጣ አውግዟል።  ይህ ታላቅ ስልፍ በጎንደር ከተማ ውስጥ ከአሁን በፊት ከተደረጉ ሰልፎች ሁሉ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ የተሳተፈበት መሆኑ እየተገለጸ ነው።ሰልፉ በሰላም ተጀምሮ በሰላም ከመጠናቀቁም በላይ በኦሮሚያ ክልል በመደረግ ላይ ላለው ህዝባዊ ተቃውሞ ድጋፍ የተሰጠበትና የወያኔ ከፋፍለ ግዛ ፖሊሲ አከርካሪውንም የተመታበት ነበር። ህዝቡ የወያኔ አስከፊ አርማ ያልተለጠፈበትን ንጹሁን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ አንግቦ ያሰማቸው ከነበሩ መፈክሮች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፣

  • የሻቢያ ተላላኪ ህወሃት እንጂ ወልቃይት አይደለም
  • የተሸጠው ድንበራችን በአስቸኳይ ይመለስ
  • አማራና ቅማንት አንድ ነን
  • የታሰሩ የወልቃትና ጠገዴ ኮሚቴ አባላት በአስቸኳይ ይፈቱ

https://www.youtube.com/watch?v=e0cFIOfwzzw