ሰበር ዜና፤ የጎንደር ህዝብ ቃሉን ጠብቆ አደባባይ ወጥቷል
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
- የጎንደር ህዝብ ቃሉን ጠብቆ አደባባይ ወጥቷል
- ተቃውሞው ህዝቡ በራሱ አነሳሽነት የሚያካሄደው እንጅ በማንም ውጭ በሚገኝ ቡድን የሚመራ አንዳልሆነ ታውቋል
- አንዳንድ በስም እንጅ በተግባር የሌሉ ተስፈኛ ቡድኖች ከዚህ ህዝባዊ እንቅስቃሴ ለመቀላወጥና እነሱም እንዳሉበት አድርገው ለማወናበድ ሙከራ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል
የጎንደር ከተማ በሰላማዊ ሰልፈኞች ተጥለቅልቃለች ሕዝቡ ወደ መስቀል ኣደባባይ መጓዙን ይዟል ። የሕወሓት ወታደሮችና ፖሊሶች በግርምት ኣፍጥጠው እያዩ መንገድ እየዘጉ ሰልፈኛውን ለመቁረጥ ጥረት እያደረጉ ነው። ፤በፍርሃት እንዳይወጣ እያደረጉት ያለው ሕዝብ በልበሙሉነት ኣደባባዩ በሚሊዮኖች እየሞላ ነው፤የኢንተርኔት ኣገልግሎት ኣይሰራም።
የወልቃይት ጉዳይ የኣማራና የኣማራነት ማረጋገጫ እንደሆነ በተግባር እየታየ ነው። አትነሳም ወይ አትነሳም ወይ ይሄ ባንዲራ ያንተ አይደለም ወይ በሚለው ከፍተኛ ጩሀት ያሰማል የክልሉ ፓሊስ ከህዝብ ጋር ሙሉ ለሙሉ ተቀላቀለ አንድነት ሀይል ነው ህዝብ ሀይል ነው።ሁለም አቅጣጫ በተለይም በፒያሣ አካባቢ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሠልፋ ታዳሚ በመፈክሮችና በቀሥቃሽ ሙዚቃዎች ታጅቦ ወደ መሥቀል አደባባይ እየተመመ እንደሚገኝ የሠልፋ ተሣታፊ ከሥፍራው ነግሮኛል። ከኦሮሞ ሕዝብ ጎን መቆሙን አማራው በተግባር በሚሊዮኖች ድምጹ ኣረጋግጧል። በሕዝብ ዘንድ ጥላቻና ዘረኝነት እንዳሌለ የጎንደሩ ሰልፍ ለገዢዎች ኣሳይቷል። በጎንደሩ ሰልፍ የህዝብ ችግር ወያኔዎች እንደሆኑ እንጂ በሕዝብ መካከል ችግር እንደሌለና ኢትዮጵያዊነት እንዳስተሳሰረ በተግባር ከመመስከሩም በላይ የወያኔን ባንድራ ተቀባይነት እንዳሌለው ታይቷል።
የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ከሥፍራው እንደሌሉ እና አጋዚ ግን ከትናንት ጀምሮ ቢኖርም ህዝቡ ፍጹም ጨዋነት በተሞላበት ሰላማዊ መንገድ የሰልፉን ግብ ለማሳካት እርብርብ ላይ መሆናቸውን ለማወቅ ችያለሁ። http://mereja.com/album/1092
ሰልፋን እየመሩት የሚገኙት የኃይማኖት አባቶች የክርስትያኑና የሙስሊሙ ሲሆኑ ምንም ያልተለጠፈበትን ንጹሁን የኢትዬጽያ ሰንደቅ ዓላማ እየተውለበለበ ይገኛል፡፡ በዚህ ሰዓት አንድም ፌደራል አይታይም፡፡ አሁን የሚሰማኝ ስሜት ልክ አባቶቻችን ጣልያንን ሲያሸንፉ፤ ልክ እንደ አድዋ ድል በማለት ደስታውን ገልፆልኛል፡፡ በቦታው ኮረኔል ደመቀ የላከው መልክት ሊነበብ እንደሆነም ገልፆልኛል፡፡ በአደራ የሰጠናችሁን ልጃችን ኮለኔል ደመቀ ዘውዱን መልሱልን! በግፍ የታሰሩ የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት በአስቸኳይ ይፈቱ! የሚሉና ሌሎችም የሕዝቡን ብሶትና ምሬት የሚገልጹ መፈክሮች ከፍ ባለ ድምጽና እጅግ በሞቀ ስሜት በመሰማት ላይ ናቸው።