ደቡብ ጎንደር ዞን እብናት ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ መዘርፋ ታውቋል ።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ደቡብ ጎንደር ዞን እብናት ወረዳ ዛሬ ምሽት ማለትም በሐምሌ 22 /2008 ዓ.ም ለሐምሌ 23/2008 ዓ.ም አጥቢያ የፖሊስ ጣቢያ መጋዘን መዘርፋ ታውቋል ።ማንነታቸው ባልታወቁ ሰውች የተዘረፈው መካዝኑ የተለያዩ የጦር መሳሪያወችንናየፖሊስ አልባሳትን እንዲሁም የፖሊስ መገልገያ ቁሳቁሶችን የያዘ እንደነበር ታውቋል ።ዛሬ እስከ እኩለ ቀን ድረስ በወረዳው ፖሊስ አዛዥ ንጉሴ የሚመራ ቡድን የመሳሪያ ቆጠራ እያደረገ ሲሆን 12 ክላሽንኮፍ መሳሪያ አለመኖራቸው ተረጋግጧል።
ይህ የመሳሪያ ዘረፍ በሰሜን ጎንደር የተጀመረው የማንነት ጥያቄ በተነሳው አመፅ ጎንደር ውጥረት ውስጥ ባለችበትና ነገ ማለትም ሐምሌ 24/2008 ዓ.ም በሚካሄደው ህዝባዊ አመፅ ድራር ላይ መሆኑ የወረዳው ና የዞኑ አመራሮችን ድንጋጤ ውስጥ ከቷል ።አንጋጋሪነቱም ጨምሯል ፤እስካሁን በድርጊቱ የተጠረጠሩ ሰወችን ለማደን የአመራሮቹ አይን በምሽቱ የጥበቃ ዘብ ያደረው የፖሊስ አባል ላይ አፍጥጠዋል ።