የፕሮፌሰር ጌታቸው ሃይሌ “ግዕዝ በቀላሉ ከናሙና ድርሰቶቹ ጋራ” መጽሃፍ በገበያ ላይ ዋለብ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የፕሮፌሰር ጌታቸው ሃይሌ “ግዕዝ በቀላሉ ከናሙና ድርሰቶቹ ጋራ” መጽሃፍ በገበያ ላይ ዋለ።
የፕሮፌሰር ጌታቸው ሃይሌ ኣዲሱ መጽሃፍ “ግዕዝ በቀላሉ ከናሙና ድርሰቶቹ ጋራ” በገበያ ላይ መዋሉን እና መጽሃፉን በተመለከተ ደራሲው በፌስቡክ ገጻቸው የሚከተውን ኣስፍረዋል።
አጭር ማስታወቂያ
በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርስቲ አስተማሪ በነበርኩበት ዘመን “ግዕዝ ባዲስ ዘዴ” ማስተማሪያ አዘጋጅቼ ነበር። እስካሳትመው ድረስ ረቂቁ ተባዝቶ ሳስተምርበት ሳለሁ፥ ባልተጠበቀ አጋጣሚ ተሰደድኩ። ሆኖም እኔን የተኩ አስተማሪዎች እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ሲያስተምሩበት ነበር። አሁን የአምላክ ፈቃድ ሆኖልኝ፥ ረቂቁን አሻሽየ፥ ከግዕዝ ሥነ ጽሑፍ ውስጥ በብዙ ያልታወቁ ግን ጠቃሚ ትምህርት ያዘሉ ድርሰቶች ለናሙና መርጬ “ግዕዝ በቀላሉ ከናሙና ድርሰቶቹ ጋራ” በሚል ርእስ አሳትሜ ለሽያጭ አቅርቤዋለሁ. አቀራረቡ ማንም አማርኛ ተናገሪ ያለ አስተማሪ ግዕዝ ለመማር እንዲችል፥ ግዕዝ የሚያውቅም የማያቀውን የግዕዝ ሥነ ጽሑፍ እንዲያውቅ ተደርጎ ነው።
መጽሐፉ አዲስ አበባ በየመጻሕፍት መደብሩ ተደርድሯል። አማዞንም (amazon.com) ከሌሎቹ መጽሐፎቼ ጋር ለሽያጭ አቅርቦታል። Books by Getatchew Haile ብላችሁ ብታሥሡ ታገኙታላችሁ። ስሜን በትክክል Getatchew ብላችሁ በመጻፍ ፈንታ Getachew ብላችሁ አበላሽታችሁ ብትጽፉት ግን አታገኙትም።