­

ድምፃዊ መሐሙድ የፈረንሣዩን የቼቪለር ኦፍ ዘ ኦርደር ኦፍ አርትስ ኤንድ ሌተርስ የክብር ሽልማት አገኘ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Legend Singer Mehamud Ahmed has Received the French Order of Arts and chēvileri of the letters prize of honor

ድምፃዊ መሐሙድ የፈረንሣዩን የቼቪለር ኦፍ ዘ ኦርደር ኦፍ አርትስ ኤንድ ሌተርስ የክብር ሽልማት አገኘ

ድምፃዊ መሐሙድ አህመድ በፈረንሣይ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የቼቪለር ኦፍ ዘ ኦርደር ኦፍ አርትስ ኤንድ ሌተርስ ተሸልሟል፡፡ ድምፃዊው ሐምሌ 12 ቀን 2008 ዓ.ም. በፈረንሣይ ኤምባሲ ሽልማቱን ተቀብሏል፡፡ በዕለቱ በኢትዮጵያ የፈረንሣይ አምባሳደር ብሪጅት ኮልት የተገኙ ሲሆን፣ ሽልማቱን አበርክተውለታል፡፡ መሐሙድ ሽልማቱን ሲረከብ ‹‹ይህ ሽልማት የኔ ብቻ ሳይሆን የመላው ኢትዮጵያውያን አርቲስቶች ነው፤›› ብሏል፡፡

አምባሳደሯ መሐሙድ አነስተኛ ገቢ ካለው ቤተሰብ ወጥቶ፣ በሊስትሮነትና ሌሎችም ሥራዎች አልፎ ህልሙን በማሳካቱና የአገሩን ባህል በማስተዋወቁ ረገድ ያበረከተው አስተዋጽኦ የላቀ በመሆኑ ሽልማቱ ይገባዋል ብለዋል፡፡

ቼቪለር ኦፍ ዘ ኦርደር ኦፍ አርትስ ኤንድ ሌተርስ እ.ኤ.አ. በ1957 የተጀመረ የፈረንሣይ የክብር ማዕረግ ሲሆን፣ በኪነ ጥበብ ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ሰዎች ይሰጣል፡፡

በፈረንሣይ ሕግ መሠረት አንድ ፈረንሣዊ ይኼንን ሽልማት ለማግኘት ቢያንስ ሠላሳ ዓመት ሊሞላውና ለፈረንሣይ ባህል ዕድገት አስተዋፅኦ ሊያደርግ ይገባዋል፡፡ ሽልማቱ ከአገሪቱ ውጪ ላሉ ሰዎች ሲሰጥ ግን የዕድሜ ገደብ የለውም፡፡

ሽልማቱ በሦስት እርከን ይሰጣል፡፡ እነዚህም ኮማንደር፣ ኦፊሰርና ናይት (ቼቨለር) ናቸው፡፡ ከአንዱ ደረጃ ወደ ተከታዩ ለማደግ ቢያንስ አምስት ዓመት መጠበቅ አለበት፡፡

ድምፃዊው የኢትዮጵያን ባህል በመላው ዓለም በማስተዋወቁ ይጠቀሳል፡፡ እንደ ዓለምዬ፣ ኧረ መላ መላና ትዝታ ያሉ አልበሞቹና ሌሎችም ዕውቅ ሥራዎቹ ባህር ተሻጋሪ ናቸው፡፡ የትዝታው ንጉሥ በሚል የሚታወቀው መሐሙድ፣ የበርካቶችን ቀልብ በገዙ ሥራዎቹ ተወዳጅነትን አትርፏል፡፡

የፈረንሣዩ ሽልማት ከሁለቱ ሳምንት በፊት ለኪውሬተርና አንትሮፖሎጂስት መስከረም  አሰግድና ተወዛዋዡ መላኩ በላይ ተበርክቶላቸዋል፡፡ የመሐሙድ እስካሁን ከተሰጡት በእርከን የበለጠ ነው፡፡