የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አመራር ከደህንነት አፋኝ ቡድን ጋር ትብብር እያደረገ መሆኑ ተረጋገጠ::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አመራር ከደህንነት አፋኝ ቡድን ጋር ትብብር እያደረገ መሆኑ ተረጋገጠ:: Minilik Salsawi

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ BNI የሚል ኮድ ያለው እና ከጎኑ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሚል ፅሁፍ ያለው አንቡላንስ የህወሀት የደህንነት አባላት በጎንደር ከተማ
ይዘው እየሰለሉበት መሆኑን በዛሬው ቀን አይተናል፡፡ በተመሳሳይ በደባርቅ የተቃጠለው የጎነደር ዩኒቨርሲቲ መኪና እና በጎንደር መስታወቱ
የተሰባበረው መኪና ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከተሰጠው አላማና ተግባር ውጭ ከአፋኝ ቡድን ጋር ትብብር እያደረገ መሆኑን ደርሰንበታል፡፡

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ንብረት የጎንደር እንዲሁም የመላ ኢትዮጵያ ህዝብ ንብረት በመሆኑ ለሚቃጠሉት ሆኑ ለሚወድሙት የዩኒቨርሲቲው መኪኖች የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አመራሮች በህዝብ ስም ተጠያቂዎች በሆናችሁ ማሳሰብ እነፈልጋለን፡፡ በመሆኑም የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ከዚህ እኩይ
ተግባራችሁ እና የህወሀት እኩይ ተግባር ተላላኪነታችሁ እንድትወጡ በመላ አማራ ህዝብ ስም እናሳስባለን፡፡ ዩኒቨርሲቲዎች የእውቀት እና የዲሞክራሲ ዜጎች ማምረቻ እንጂ የዲሞክራሲ አፋኞች ተባባሪዎች አይደሉም፡፡