ዶናልድ ትራምፕን ኢላማ ያደረገው ለየት ያለው ተቃውሞ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ዶናልድ ትራምፕን ኢላማ ያደረገው ለየት ያለው ተቃውሞ
====== Dawit Solomon Yemesgen
የሪፐብሊካን ፓርቲን በመወከል ለአሜሪካ ፕሬዘዳንትነት ለመወዳደር የኮንቬንሽኑን ይሁንታ ይጠባበቁ የነበሩትን ዶናልድ ትራምፕን ለመቃወም ከ100 የሚልቁ ፈቃደኛ ሴቶች በክሊቭላንድ ዝግጅታቸውን አጠናቅቀው ነበር፡፡
ሴቶቹ ልብሳቸውን ሙሉ ለሙሉ በማውለቅ መስታወቶችን በመያዝ የሪፐብሊካን ፓርቲ ስብሰባ የሚካሄድበትን አዳራሽ ለመውረር ተዘጋጅተው ነበር፡፡
የተቃውሞው ሀሳብ አመንጪ የኒውዮርክ ነዋሪ የሆነው የፎቶግራፍ ባለሞያ ስፔንሰር ቱኒክስ ስለመሆኑ ተነግሯል፡፡የፎቶግራፍ ባለሞያው ብዛት ያላቸውን ሰዎች እርቃናቸውን ፎቶ በማንሳት ለህዝብ በማቅረብ እንደሚታወቅም ይነገርለታል፡፡
ቱኒክስ በቅርቡ 3000 የሚደርሱ ሰዎችን ‘Sea for Hull’ለሰየመው ፕሮጀክቱ ማሳያ እርቃናቸውን በማድረግና ሰውነታቸውን በሰማያዊ ቀለማት በመቀባትና አራት የተለያዩ ቀለሞችን በመጠቀም ጥላዎችን በመፍጠር ማራኪ ፎቶግራፎችን ለዕይታ ማቅረቡ ይነገራል፡፡ሰዎቹን የቀባቸው ሰማያዊ ቀለም ውሃን እንደሚያመለክት መናገሩንም መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡


ትናንት የሪፐብሊካኖች ኮንቬንሽን ከመጀመሩ ቀደም ብሎ ከመቶ በላይ የነበሩት ሴቶች እርቃናቸውን በመሆን ትልልቅ መስተዋቶችን በመያዝ ወደ አዳራሹ ለመግባት ያደረጉት ሙከራ ባይሳካም የፎቶግራፍ ባለሞያው የተቃውሞ ፕሮጀክት የተሳካ ስለመሆኑ ተነግሮለታል፡፡ሴቶቹ እርቃናቸውን የተነሱበት ተቃውሞ “Everything She Says Means Everything” የሚል መጠሪያ ተሰጥቶት ነበር፡፡
ሴቶቹ ሪፐብሊካኖች ስብሰባቸውን ባደረጉት አዳራሽ ቅርጽ የተሰራ መስታወት በመያዝ መስታወቶቹን ወደአዳራሹ አቅጣጫ በማንጸባረቅ ፎቶግራፎችን ተነስተዋል፡፡የተቃውሞው አዘጋጅ ‹‹ሴቶቹ እርቃናቸውን መሆናቸው ተፈጥሮን የመስታወቶቹ ወደአዳራሹ ብርሃን ማንጸባረቅ ደግሞ ከተፈጥሮ ከሴት ልጅ የሚወጣውን እውቀትና ተፈጥሮ ለማሳየት ነው ማለታቸው ተዘግቧል፡፡
አወዛጋቢው ዶናልድ በትናንቱ የሪፐብሊካኖች ጉባኤ የፓርቲው ዕጩ በመሆን ለፕሬዘዳንታዊው ፉክክር እንዲቀርቡ ይሁንታ አግኝተዋል፡፡