መብሰል መከባበር መደማመጥ የምንጀምረው ከየትኛው ጫፍ ይሆን? የምንሄድበት መንገድ ሁሉ ዝግ ነው!! የስድብ እና የፍረጃ ፖለቲካ ይሰለቻል::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) የማህበራዊ ድረገጽን ለመልካም ነገር ማዋል ከቆመ ቢያንስ 2 አመታት ተቆጥረውታል:: ማህበራዊ ድረገጽ በተለይ(ይብልጡኑ ፌስ ቡክ በተሳዳቢዎች ባልበሰሉ ፖለቲከኛ ነን ባዮች ባልሰለጠኑ እና ጽፈው የሰጧቸውን በሚለጥፉ ሲልም በስም አጥፊዎች ብሎም በዘላፊ እና በአጨብጫቢ ስሜተኞች ባለሥሥ ብልት አሸማቃቂ ተሸማቃቂዎች ሳትፈለግ እንድትናገር በሚኮረኩሩ ድኑዞች ተወሯል:: አልሰለጠንም …. ስልጡን ፖለቲካ የሚከተሉ ጥቂት የማይባሉ ውድ ኢትዮጵያውያን በእነዚሁ ጋጥ ወጥ ሰዎች ተሸፍነዋል:: የማህበራዊ ድህረገጽ ተጠቃሚ ይሁን አይሁን በፌስቡክ ምን ተባለ የሚሉ ጠያቂዎች አስከትለው ከጉዳዩ ጋር ጥያቄ የሚያነሱ ዜጎች በርካታ ናቸው:;ልብ እንበል ልብ ካለን::ካለፉት የኩርኩም ሂደቶች እና ሾኬዎች ምን እንማራለን?? ምንስ አትርፈናል???
ለቁም ነገር ጽሁፎች ቁብ የማንሰጥ የወሬ ቃራሚዎች ከሆንን ሰነባብተናል::እንካካድ እባካቹ ራሳችንን እንፈትሽ:: በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ እንዲመጣ እንታገላለን ስንል የሃሳብ ልእልናን ማመን እና መቀበል ያስፈልጋል:: የምንታገለው ዜጎች ከአፈና ተላቀው ሃሳባቸውን የፈለጉትን በነጻነት እንዲገልጹ ነው::ዜጎች ባመቻቸው መንገድ ሃሳባቸውን ሲገልጹ ሃሳብ ይዳብራል አዲስ ነገር ይፈጠራል::በእስር ቤት ያሉ ዜጎች ጋዜጠኞች የፖለቲካ ሰዎች ሌሎችም የታሰሩት ሃሳባቸውን በነጻነት ስለገለጹ ነው::ይህ ደግሞ የአምባገነኖች ባህሪ ስለሆነ ይህ እንዲወገድ ሁላችንም እየሰራን ነው::ሰዎች ተነስተው በተናገሩ በጻፉ ቁጥር እየተነሳን የምንደነፋ የነገር ቃታ የምንስብ ከሆነ በምንታገልለት ድርጅት ላይ ይሁን በለውጥ ሃይል ላይ ጥያቄ እንዲነሳ እንጋብዛለን ይህ ብቻ አይደለም የሰዎችን መብት ስንጋፋ የኛ ማንነት ጥያቄ ውስጥ ከመግባቱም በላይ በዲያስፖራው ለውጥ ሃይሉ ላይ ታማኝነት እንዳይኖር ከማድረጉም በላይ የነገ ተስፋ የሆነውን የአምባገነኖችን የማስወገድ የትግል ሂደት ላይ ጥቁር ነጥብ ከመጣል በላይ እንዳይሳካም ደንቃራ እንደምንሆን መዘንጋት የለብንም::ልብ ያለው ብቻ ልብ ሊል ይችላል::ሃሳብን የሚከለክሉ እነማን ናቸው? ነገ ስልጣን ቢይዙ ምን ሊያደርጉን ነው? ወዘተ የሚሉ የጥንቃቄ ጥያቄዎች ከሕዝብ ጉያ እንደሚፈልቁ እንርሳ!!!
የስድብ እና የፍረጃ ፖለቲካ ይሰለቻል:: እንብሰል እንብሰል እንብሰል … ካልሆነ የምንሄድበት መንገድ ሁሉ እሾህ መሆኑን አንዘንጋ::እኔ በስያለሁ የሚል ሰው ካለ ራሱን መልሶ ይመርምል የሚሄድበት መንገድ ይፈትሽ::ለዚህ ነው መብሰል መከባበር መቻቻል መደማመጥ የሚያስፈልገን::አንዱ የለውጥ ሃይል ነኝ የሚል ድንገት በባዶ የስሜት ሆዱ ብድግ ብሎ ቢጮህ የወያኔ መሳቂያ መሳለቂያ የሌሎች ደግሞ መታዘቢያ እንደሚሆን መዘንጋት የለበትም ሰከን ብለን እናስብ::በስሜት የተለወጠ አገርም ይሁን ትውልድ የለም::ስሜታዊ የሆያሆዬ ፖለቲከኛ አሊያም ለውጥ ፈላጊ መሆን ትውልዱን ይገላል::በኢትዮጵያ አዲስ የአንድነት እና የዲሞክራሲ አስተዳደር መመስረት የሚቻለው በሰከነ የአስተሳሰብ ውጤት ነው እንጂ ዜጎች ሃሳባቸውን በነጻነት ገለጹ ብሎ በመደንፋት በመሳደብ በማስፈራራት አይደለም::ይህን የሚያደርጉ ክንፎች የትም አይደርሱም::ትርፉ ለለውጥ ሂደቱ ጠንካራ የነበረው የድርጅቶቻቸውን አሊያም የራሳቸውን ማንነት ከማደብዘዝ ውጪ ለአሽሟጣጮች ተዳርጎ ባለህበት እርገጥ የሚለውን አሁን የያዙትን የወሬ ፖለቲካ ከመደጋገም ውጪ አዲስ መጽሃፍ አይኖራቸውም::እያንዳንዳችን ለዲሞክራሲያዊ ስርኣት መስፈን እስከታገል ድረስ በሃሳብ ልእልና ልናምን ይገባል::የያዝነው መንገድ ሁሉ ራሳችን እየዘጋነው መሆኑን እንርሳ ከባለፈው ልንማር ይገባል በሂደት በራሳችን ላይ አዳዲስ ለውጦች ማድረግ አለብን::መጣፊያው ሳያጥረን(አሁንም አልተረጋገጠም)ሁላችንም ሃሳባችንን በነጻነት እንድንገልጽ እንከባበር እንቻቻል::እንፋቀር እንከባበር እንደማመጥ እንተራረም ይበልጥ ደግሞ እንብሰል:: #ምንሊክሳልሳዊ