ተቃውሞ ና የሹፌሮች ስራ ማቆም አድማ በምእራብ ሸዋ ተካሄደ፤ወያኔያዊ ሽብርተኝነት ቀጥሏል
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
#Ethiopia #Oromoprotests ተቃውሞ እና የሹፌሮች ስራ ማቆም አድማ በምእራብ ሸዋ ተካሄደ:: ፀረ-ሕዝብ መንግስታዊ ሽብርተኝነት ቀጥሏል:: #MinilikSalsawi
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በምእራብ ሸዋ ጀልዱ እና ጊንጪ ተቃውሞና የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶችና የሚኒባስ የስራ ማቆም አድማ የተደረገ ሲሆን በጀልዱ ከተማ በርካቶች በወያኔ አግኣዚ ጥይቶች ተመተው ክፉኛ መቁሰላቸው ታውቋል::ይኸው ተቃውሞ በግንደበረት እና አጎራባች አከባቢዎች የተደረገ ሲሆን ሕዝቡ መንገድ በመዝጋት ተቃውሞ መግለጹ ታውቋል::በጊንጪ እና በአከባቢው ከተሞች የአውቶብስ መናኸሪያዎች የሹፌሮችን አድማ ተከትሎ በርካቶች አውቶብሶችን አጥተው የተመለሱ ሲሆን በምእራብ ሸዋ የሚገኙ አውቶብስ መናኽሪያዎች በተሳፋሪዎች ተጨናንቀው ተስተውለዋል::ምንሊክ ሳልሳዊ
በጀልዱ ወረዳ እና በአከባቢው ከተሞች በተካሄደ ተቃውሞ በጎጆ ከተማ በጥይት ተመትተው የቆሰሉ
1ኛ- ብርሃኑ ጫላ – ሸንኩቱ ከተማ ታሶ አከባቢ
2. በይሳ ቀልቤሳ – በቾ
3. አቡሽ ነጋሳ – ጎጆ
4. ደጀኔ ቡልቻ በቾ
5. ሲሳይ ደበላ – ጎጆ
6. ባይሳ ኦልጋ – ጎጆ ሲሆኑ በሸንኩቴ ከተማ ማምሻውን ድረስ ተቃውሞ የቀጠለ ሲሆን መንገዶች በሙሉ ተዘግተዋል:: ፀረ-ሕዝብ መንግስታዊ ሽብርተኝነት ቀጥሏል::#ምንሊክሳልሳዊ




