በጎንደር ከተማ ብቻ ሳይሆን በአካባቢዋ እያየን ያለነው ወደ ሁለት ድምዳሜዎች እንድንደርስ ያደርገናል፡


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በጎንደር ከተማ ብቻ ሳይሆን በአካባቢዋ እያየን ያለነው ወደ ሁለት ድምዳሜዎች እንድንደርስ ያደርገናል፡

“ከአዘዞ ፒያሳ አራዳ መናሀሪያ ወለቃ አንባ ጊወርጊስ ገደብየ ደባት ደባርቅ …ጎንደር …አውን ያለበት ሁኔታ ለማየት የተንቀሳቀስኩባችው ቦታወች

Girma G. Kassa's photo.

የነዋሪወችን አስተያየት እንሆ” በሚል አንድ ጦማሪ የጎንደር የተለያዩ ቦታዎችን በመቅኘት የሚከተለውን አቅርቧል። ይሄ የአይን እማኝ ያስቀመጠው፣ ነዋሪዎች በተለያዩ ቦታዎች ለአሜሪካን ጽም ራዲዮ፣ ለኢሳት የተናገሩትን የሚያስረግጥማ በጎንደር የሚኖሩ በሶሻል ሜዲያ የሚጦምሩትን የሚያጠናክር ነው።

በጎንደር ከተማ ብቻ ሳይሆን በአካባቢዋ እያየን ያለነው ወደ ሁለት ድምዳሜዎች እንድንደርስ ያደርገናል፡

1. የሕወሃት አገዛዝ በሕዝቡ እንደተጠላ እና
2. ህዝብን ፍርሃንት አዉልቆ፣ ለመታገል እንደቆረጠም በቃኝ እንዳለ

100% አሸንፈናል፣ ህዝብን ይወደናል፣ ሕዝብ የኛ ነገር አኡሆንለትም ብለው ሲመጻደቁ የነበሩ ገዢዎች በዚህ መልኩ ሶሪያና ሞጋዲሾ ይመስል ሰላማዊ ህዝብ ባለበት ቦታ ብረት ለብስ የታጠቁ ወታደሮቻቸው ማሰማራታቸው መቼ ይሆን የሚቆመው? 200% ድጋፍ ሲያገኙ ? መልሱን ለደጋፊዎቻቸው እተዋለሁ። እስከዚያ እንሆ ከስፋራው የተጠናክረ ዘገባ

ከሞላ ጎደል ሁለት መሰረታዊ ደሜዲኡ

================
ከአዘዞ ፒያሳ ኮሌጂ አውቶፓርኮ ፒያሳ አውህንም አድማ በታኝ ፓሊስ መከላከያ በመኪናም በጉርፕ እየተንቀሳቀሱ ነው !!!አራዳ ፒያሳ ብልኮ የወታደሮች ቁጥር
ይጨምራል። ተራራ ሆቴል እስከ ወለቃ ባለው መስመር የመከላከያ አቀማመጥ ቦታ አያያዝ ለቆረጣ እንዲመቻቸው ቦታ ይዘዋል። በዚህ ቦታ የገበሬው ጦር ይገባበታል ተብሎ
የሚጠበቅበት ቦታ ነው !!!

ከአንባ ጊወርጊስ ገደብየ ባለው መስመር ቁጥሩ፣ ከ40 የበበለጠ መከላከያ አድማ በታኝ አይቻለውህ።

በዳባትና ደባርቅ ከተማዎች መፈራራት ውጥረት ጨምሯል። የጦር ቀጠና መስሎል። አንድ የደባርቅ ነዋሪ በ45 አመቴ በመከላከያ ታጅቤ እየተንቀሳቀስኩ ነው ። ሁሉም ነዋሪ አጃቢ የተመደበለት ይመስላል። ብዙ ሰው ታስሮል። ኔትወርክ መብራት ችግር ነው። ከክረምቱ ጋር ከፍተኛ መንገላታት ይታያል። የፎቶ እና video መረጃወችን ይዠ ወደ ጎንደር …..

የጎንደር ነዋሪወች ❖❖❖ የመንግስ ደህንነተቸ ፀጉረ ልውጥ ሰወች አዳዲስ ታርጋ ያለጠፉ መኪኖች ይንቀሳቀሳሉ። መከላከያ መትረየስ ታጥቀው ሰላማዊውን ነዋሪ ሰላም
ነስተዋል !!! ነዋሪዎች አሁንም፣ በራስ መተማመን፣ የሚያዩትን ሁሉ በንቃት እየተከታተሉ መረጃወችን እየተለዋወጡ አንድነታቸውን እያጠናከሩ ይነኛሉ። አንድ በ20ዎቹ እድሜ የሆነ ወጣት እንዳለው… “ከመቼውም ጊዜ በላይ ህዝቡ ቆርጧል። የቆረጠና ምክንያት ያለውን ህዝብ በየትኛውም መሳርያ ማስፈራራትም ማስቆምም አይቻልም !!!”

ይሄንን አጭር ጥንቅር ወደናተ ለማድረስ ኔትወርክ ስሌለለ፤ ወደ አዲስ ዘመን ተመልሻለሁ።
======================