ኮ/ል ደመቀ ወደ አንገረብ እስር ቤት መወሰዳቸውን ተከትሎ የህዝብ ተቃውሞ የተከሰተ ሲሆን የተኩስ ድምጽ ይሰማል።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።


የደርግ ፕሮፓጋንዳና እጥፍ አምባገነንነት የወያኔ የዘረኝነት ስሌት – #ዳግማዊ_ደርግ
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) የደርግ ስርኣት ሊወድቅ ሲቃረብ በአንድነት ሽፋን በወያኔ ላይ ሲነዛቸው ከነበሩት ፕሮፓጋንዳ መካከል እኛ ክወረድን ኢትዮጵያ እንደ ሞኖሮቭያ እና ሶማሊያ ትበጠበጣለች የሚል ሲሆን አሁንም የወያኔው አገዛዝ ፈሊጥ ሕወሓት ስልጣን ከለቀቀች ሃገሪቱ የጦር አውድማ ትሆናለች ከኛ ሌላ ስልጣን ከያዘ ኢትዮጵያ ትበጣጠሳለች ይሉናል::ደርግ በሃገር አንድነት ስም ወያኔ በብሄረሰቦች መብት ስም በጠበንጃ አፈሙዝ እየገዙ ኢትዮጵያ የምትባለዋን ሃገር ባርከው የፈጠሯት ይመስል ያስፈራሩናል::ደርግ ስለወያኔ የሚነግረን ጉዳይ ትንቢታዊ የፍጻሜ ሂደት ውስጥ ቢሆንም የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን የወያኔ ጉጄ አገዛዝ ያመጣበትን አደገኛ አደጋ የተቋቋመ ብረት ሕዝብ መሆኑን አሳይቷል::
ወያኔ ባሰላው ስሌት መሰረት በፈጠራቸው የጎሳ ፖለቲካ አራጋቢዎች በውጪ ሃገር እና በሃገር ውስጥ አበርክቶ ሕዝብን በማፋጀት የራሱን የትግራይ ሪፑብሊክ ለመመስረት ቢቧጥጥም ሕዝቡ ግን ጭራሽ ራሱ ወያኔን አደጋ ውስጥ ከቶታል:: የትግራይን ሕዝብ ከሌላው ሕዝብ ለይቶ በክፋት ወጥመድ ውስጥ ለማስገባት ያደረገው ሙከራ በከፊል ቢሳካለትም በከፊል ግን በጥርጣሬ ቀለበት ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል::በፖለቲካ ጨዋታ ሰበብ ሕዝቦች ከጥቅም ውጪ በማድረግ መግደል ማሰር እና ማሳደድ ስራዬ ብሎ የያዘው ወያኔና የብተናቸው የጎሳ ፖለቲካ አራማጆች ሃገርቷን ሩዋንዳ ለማድረግ እየሰሩ ይገኛሉ:: ለነሱ ስራቸው የሚሳካ መስሏቸው ይንደፋደፉ እንጂ ከባድ ዋጋ አስከፍሏቸው በቆፈሩት ጉድጓድ ይቀበራሉ::
ብሄርተኝነት ይለምልም እያሉ ሲያዜሙ ከርመው በውስጥ አካላቶቻቸው ላይ ጉድ ይዞባቸው መጥቷል:: ራሳቸው በሽኩቻ እየታመሱ ከንፈር ተነካክሰዋል::አራጋቢ ሆዳሞችን ከጎናቸው አሰልፈው እንደለመዱት አባሎቻቸውን ለመብላት አሰፍስፈዋል::ይህ ግን ሩቅ መንገድ አያሻግራቸውም::ሕወሓት ሲነካ ሌላው እንደ ዘረኛ ሲፈረኝ ጋምቤላው ኦሮሞው ኮንሶው ሲዳማው አማራው ሃረሩ ኦጋዴን በአንድ ብሄር የጦር አበጋዞች በሚመራ የአንድ ቋንቋ ተናጋሪ አግኣዚ ወታደሮች ሲቸፈጨፍ ግን ዘረኝነት ብለው ለምን እንደማይናገሩ ያጠያይቃል:: ለዜጎቹ ጥበቃ የማያደርግ መንግስት ፣ ግብር ከፋዩን ህብረተሰብ በፖሊስ የሚያስደበድብ መንግስት ‘ህዝቡን የማገለግል ዲሞክራሲያዊ መንግስት ነኝ’ ሊል አይችልም። በወያኔ መሪነት የኢትዮጵያ ሕዝብ ሉዓላዊነቱን ሊያስከብር፣ ከድህነቱም ሊላቀቅና ዲሞክራሲያዊ መብቱን ሊቀዳጁ እንደማይችል የተረጋገጠ ሆኗል፡፡ሕዝቡ ተማሯል ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ለሕወሓት የጎሳ ፖለቲካ መልስ ይሰጣል::ጥቂቶች ከብረው ሕዝቡ መብቱ ተገፎ እየተዋሸ ደህይቶ መኖር መሮታል::#ምንሊክሳልሳዊ
