“ውሸት ነው፤ የራሳቸውን የውሸት የፈተና ወረቀት አዘጋጅተው ነው ወሬውን ያሰራጩት” ሽፈራው ሽጉጤ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ከሰኞ ሐምሌ 4 ቀን የሚጀመረው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተሰረቀ በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ድረ-ገፆች የተሰራጨው ወሬ ሃሰተኛ መሆኑን የት/ት ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ አስታወቁ፡፡ 26 የፈተና ወረቀቶች ተሰርቀው መውጣታቸውን አንዳንድ ድረ ገፆች ያስታወቁ ሲሆን በማህበራዊ ሚዲያዎችም የእንግሊዝኛ ፈተና መሰረቁን የሚያመላክት መረጃዎች ተሰራጭተዋል፡፡ የትምህርት ሚኒስትር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ፣ ፈተናው ተሰርቋል የተባለው “ውሸት ነው፤ የራሳቸውን የውሸት የፈተና ወረቀት አዘጋጅተው ነው ወሬውን ያሰራጩት” ብለዋል፡፡

ቀደም ሲል ፈተናው ግንቦት 22 ቀን እንዲካሄድ ታስቦ በነበረበት ወቅት የፈተና ወረቀቶች ስለመሰረቃቸው በተለያዩ ድረ ገፆችና ማህበራዊ ሚዲያዎች ሲገለፅ እንደነበረ የሚታወስ ነው፡፡ መንግት መረጃውን እያስተባበለ ቆይቶ፣ በፈተናው መስጫ እለት ነው በድንገተኛ መግለጫ ፈተናው እንዲቋረጥ የወሰነው፡፡