የሕወሓት የቂም በቀል ሰለባ የሆነው ሃብታሙ ኣያሌው ከሃገር ወጥቶ እንዲታከም የሆስፒታሉ ቦርድ ውሳኔ ተጠየቀ።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የሕወሓት የቂም በቀል ሰለባ የሆነው ሃብታሙ ኣያሌው ከሃገር ወጥቶ እንዲታከም የሆስፒታሉ ቦርድ ውሳኔ ተጠየቀ።

Minilik Salsawi – mereja.com ኣቶ ሃብታሙ ኣያሌው በከፍተኛ የሕመም ስቃይ ላይ ሲገኝ የወሰደው የባሕል ሕክምና በፈጠረበት ችግር እንዲሁም ሕመሙ አያደገና እየሰፋ መሄዱ የፈጠረው እጅግ ከባድ ችግር ሕክምናው ኢትዮጵያ ውስጥ ስለሌለ ከሃገር ውጪ በመውጣት ኣስቸኳይ ቀዶ ሕክምና ማድረግ ኣለበት ሲል የካዲስኮ ኣጠቃላይ ሆስፒታል በሐምሌ 1 / 2016 ማረጋገጫ ሰጥቶታል።
በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በርካታ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ፣ጋዜጠኞች ፣ ጦማሪዎች፣ ፖለቲከኞች እና የሀብታሙ ቤተሰቦች ዳኛው ቢሮ በር ላይ ቆመዋል ዳኛው ኣቶ ዳኜ መላኩ ውስጥ ስብሰባ ላይ ነው ዝም ብላችሁ ጠብቁ ተብለው ከማለዳው ጀምሮ ሲጠብቁ በመዋል በድጋሚ ከምሳ መልስ ተመልሳቹ በፍርድ ቤቱ ጽ\ቤት በኩል ጠይቁ በመባል ሲጉላሉ ውለዋል።
ከሰኣት በኋላ የተመለሱት የፍርድ ቤቱን ውሳኔ የደረሳቸው ሲሆን አቶ ሃብታሙ ኣያሌው ከሃገር ወጥቶ እንዲታከም የሆስፒታሉን ቦርድ ውሳኔ በጠቅላይ ፍርድ በት ዳኛ መጠየቁ ታውቋል። የሃብታሙ ኣያለው ጉዳይ በኣንድነት ውስጥ ድል እንዳለ ትምህርት ይሰጣል።
