በጂንካ ሁለት ወንድማማቾች እየተሰቃዩ ነው::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በጂንካ ሁለት ወንድማማቾች እየተሰቃዩ ነው// ከአርባምንጭ ከተማ አርበኞች ግ7 የተቀላቀሉ ወጣቶችንና ግንባሩ በቅርቡ በከተማዋ ያካሄደውን ኦፕሬሽን ተከትሎ በህዝቡ ላይ የሚደርሰው ስቃይና በከተማው የነገሰው ውጥረት አድማሱን አስፍቶ ጂንካ ከተማ ስለመድረሱ መረጃዎች ደርሰውናል፡፡ የደረሱን መረጃዎች ከዚህ በፊት የኦሞ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት /ኦሕዲኅ/ ምክትል ሊቀመንበር ጨምሮ ሦስት ነዋሪዎች አዋሳ ተወስደው መታሰራቸውን ፣ አንድ የአርባምንጭ ወጣት ለወንድሙ ቀብር ጂንካ በመጣበት ታስሮ መወሰዱን አስታውሰው ፤ የአሁኑ ግን ከሁሉም የከፋና አንድ ቤተሰብን በበቀል ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት የተወሰደ እርምጃ አካል እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡ ዝርዝሩም፡- ትናንትናሰ 25/08 ወንድሙ ሥራ ፍለጋ መጥቶ ያሳረፈው የጂንካ መሰናዶ ት/ቤት የቢዝነስ መምህር ሰመረ አበበ ቤት ተፈትሾ ምንም ባልተገኘበት፣ አቶ ሰመረና ወንድምዬው ወጣት በረከት አበበ በካቴና ታስረው ወደ ጂንካ ልዩ ጥበቃ ተወስደው በልዩ ኃይል ቁጥጥር ሥር ይገኛሉ ፡፡ የአቶ ሰመረ እጅ ዛሬ ከካቴና ቢላቀቅም ወጣት በረከት ዛሬም በካቴና እንደታሰረ ነው፡፡ በዚህ መረጃ መሰረት የሰመረ አባት የአቶ አበበ ቤተሰብ ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ መግባቱንና በረከትም ወደ ወንድሙ ጂንካ የመጣው ከዚሁ ቀውስ ጋር በተያያዘ ሥራ ፍለጋ ሆኖመሆኑን ፣ አቶ ሰመረም ወንድማቸውን ከግል እንጨት ሥራ ድርጅት ሥራ አስጀምረው እንደነበር ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ የተገኘው መረጃ –የአቶ አበበ አንዱ ልጅ ከኣመታት በፊት ኤርትራ ሄዶ አርበኞች ግ7 ትን የተቀላቀለ ስለነበር በቅርብ ግንባሩ በአርባምንጭ ባካሄደው ኦፕሬሽን ላይ ተሳትፎ ጠፍቷልና እንዲያመጡት በሚል ተይዘው ቤታቸው ተፈትሾ ምንም ሳይገኝ እስከዛሬ ድረስ ከሴት ልጃቸው ጋር በእስር ላይ ናቸው፡፡ አሁን ጂንካ ላይ የተያዘው በረከት አስመራ የሄደውና በኦፕሬሽኑ ላይ ተሳትፎ ‹ተሰወረ › የተባለው ወንድማቸው መስሎኣቸው እንደሆነ የመረጃ ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡ በዚህም በአሁኑ ሰዓት አቶ አበበና ሶስት ልጆቻቸው በእስር ፣ አንዱ ልጃቸው በነጻነት ትግል ላይ በመሆኑ የአቶ አበበ ቤተሰብ ሙሉ በሙሉ ተበትኗል ማለት ይቻላል፤ እናት ብቻቸውን ያለ አንዳች ገቢና ደጋፊ ቀርተዋል፡፡ የቤተሰብ ቀውሱ ወደ ልጃቸው ሰመረ ቤተሰብም ተዛምቷል ማለት ነው፡፡ አቶ ሰመረ ‹ በማያውቁት ጉዳይ ለምን እንደታሰሩ፣ ወንድማቸው በወንጀል ቢጠረጠር እንኳ ስለእሱ መጠርጠርም ሆነ በህግ መፈለግ ምንም መረጃ በሌላቸው ሁኔታ፣ እንዲሁም ቤተሰባቸው በተበተነበትና የገቢ ምንጫቸው በተቋረጠበት ወንድሙን ማስጠጋትና መርዳት ማኅበራዊ ግዴታው እንደሆነ በሚታወቅበት ስለምን እንደታሰረ › ልዩ ኃይሎችን ሲጠይቅ– ትናንት ‹‹ ስላንተ ተነጋግረን እንወስናለን ፣ ስለወንድምህ ግን ምንም የምናውቀው የለም ›› ብለው የመለሱት አሳሪዎች ዛሬ ደግሞ ‹‹ስለጉዳዩ ምንም እንደማያውቁና ከማዕከል ወንድምዬው እንዲያዝ በታዘዙት መሰረት ሁለቱም መታሰራቸውን ፣ምናልባትም ወንድምዬው ወደ ማዕከል ሊወሰድ እንደሚችልና ለሁሉም ከማዕከል መመሪያ እየጠበቁ መሆናቸው… ›› እንደተገለጸለት ምንጮቹ አስረድተዋል ፡፡ ስለ ሰመረ የጠየቅናቸው የሥራ ባልደረቦቹና የከታማ ነዋሪዎች ‹‹.. አቶ ሰመረ የስራ ባልደረቦቹንና ሥራውን አክባሪ፣ ከነዋሪው ጋር ተግባቢ፣ ለእንዲህ ዓይነት እስራት ቀርቶ ሊያስጠረጥረው የሚችል ባህሪይም ሆነ የተለየ እንቅስቃሴ የሚታይበት አይደለም… የተረጋጋ በከተማዋ ከ6 ዓመታት በላይ የኖረ የቤተሰብ ኃላፊ ነው . . . ›› በማለት ገልጸውታል፡፡ በደቡብ ኦሞ ዞን የመከላከያ ልዩ ኃይልና የክልሉ ልዩ ፖሊስ ካለፈው ዓመት የሀመር ወጣቶችና መንግስት ግጭት ጀምሮ በጂንካ ከተማ መግቢያዎችና በየወረዳዎች በቋሚነት ሰፍረው እንደሚገኙና በከተማዋ የሰፈሩት ታጣቂዎች በተለያየ ጊዜ ከከተማዋ ወጣቶች ጋር ጸብ እየፈጠሩ በከተማዋ ውጥረት መንገሱ ይታወቃል፡፡ Eyob Alem– Jinka.