የ ESFNA ዓመታዊ ዝግጅት ባማረና በደመቀ ሁኔታ መካሄድ ጀመረ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የኢትዮጵያ ስፖርትና ባሕል ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ በየዓመቱ የሚካሂደውን የስፖርትና የባሕል ዝግጅት ቶሮንቶ፣ ካናዳ ውስጥ በደመቀና ባማረ ሁኔታ እልፍ አዕላፍ ኢትዮጵያዊያን በተገኙበት በዛሬው ዕለት መጀመሩን ከስፍራው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል። ፌዴሬሽኑ ዘንድሮ  የሚያካሂደው ዝግጅት ለ33ኛ ጊዜ መሆኑም ታውቋል። በተለይም ከ5 ዓመት በፊት አላሙዲ ገንዘብ አስታቅፎ ያዘመታቸው ጥቂት የቀድሞው የፌዴሬሽኑ አባላት ድርጅቱን በወያኔ ጉያ ለመወሸቅ ያደረጉት ጥረት በጠንካራና እውነተኛ ኢትዮጵያዊያን ትግል የከሸፈ ሲሆን ህዝብ ኃይል መሆኑንን ፍንትው አድርጎ ማሳየቱን የሚናገሩ በርካቶች ናቸው። የመክፈቻውን ዝግጅት የሚሳይ ቪዲዮ በ ECADF ድረገጽ ላይ የተለቀቀውን ለመመልከት እዚህ ላይ ይጫኑ። http://ecadforum.com/2016/07/03/ethiopia-esfna-toronto-2016-opening-day-2/