የአላሙዲ “ኤሳ ዋን” (AESA One) የቨርጂኒያ ዝግጅት ከፍተኛ ተቃውሞ ተደግሶለታል


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ከ33 ዓመታት በፊት የተቋቋመውን የኢትዮጵያ የባሕልና ስፖርት ፌዴሬሽን (ESFNA) ለመቆጣጠርና ለወያኔ መፈንጫ ለማድረግ በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ቢረጭምያልተሳካለት መሃመድ አላሙዲ ያቋቋመው “ኤሳ ዋን” የሚባለው ድርጅት ዘንድሮም እንደቀደሙት ዓመታት ባዶ ስታዲዮም ሊታቀፍ አሌክሳንደሪያ ውስጥ ዝግጅት ማድረጉ ተገልጾልናል።  ባለፉት አምስት ዓመታት ኢትዮጵያውያን በወሰዱት ቆራጥ ውሳኔ በተመልካች ድርቅ በተከታታይ ሲመታ ቢቆይም “ካፈርኩ አይመልሰኝ”ብሎ የተነሳው አላሙዲ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በመክፈል ያዘጋጀው ድግስ ላይ ኢትዮጵያዊያን እንዲታደሙ ከፍተኛ የማወናበድ ስራ በማሰራት ላይ ቢገኝም የዘንድሮው ካለፉት ዓመታት የባሰ እንጅ የተሻለ እንደማይሆን ሁኔታውን የሚከታተሉ በመናገር ላይ ናቸው።

ከአምስት ዓመታ በፊት በፌዴሬሽኑ ውስጥ የተሰገሰጉ የአላሙዲ ተቀላቢዎች ፌዴሬሽኑንን ለወያኔ አሳልፈው ለመስጠት በሚፈስላቸው ዶላር በመጠቀም አልህ አስጨራሽ ትንንቅ ያደረጉ ቢሆንም፣ በድርጅቱ ውስጥ የነበሩ አገር ወዳዶች ባደረጉት እርብርቦሽ በዝረራ ተሸንፈው ከጨዋታ ውጭ መሆናቸው አይዘነጋም። እነዚህ የወያኔ ተላላኪዎች ተዋርደው ከድርጅቱ ቢባረሩም በገንዘብ የሰከሩና ወያኔ በሚሰጣቸው ድጋፍ የታወሩና የልብ ልብ የተሰማቸውና  ስለነበሩ  ከዕጃቸው የወጣውን ድርጅት ለመሰንጠቅና  ከፋፍለው ለማዳካም የተጭበረበረ ክስ በፍርድ ቤት መስርተው የነበረ ቢሆንም አሜሪካ ውስጥ የወያኔ “ዳኞች” ስለሌሉ በፍርዱ አደባባይ የሽንፈትን መራራ ጽዋ እንዲጎነጩና “ፌዴሬሽን” የሚል ስም እንዳይጠቀሙ የተወሰነባቸው መሆኑ አይረሳም። ሆኖም በፖለቲካ ድርጅት ላይ ሌላ ፖለቲካ ድርጅት፣ በሙያ ማሕበራት ላይ ሌላ ተለጠፊ የሙያ ማሕበር፣ በፓትርያርክ ላይ ሌላ ፓትርያርክ፣ በሲኖዶስ ላይ ሌላ ሲኖዶስና በመጅሊስ ላይ ሌላ መጅሊስና የመሳሰሉትን መሰሪ ድርጊቶችን መፈጸመ  ሙያው አድርጎ የያዘው ወያኔ ተለጣፊ የሆነውን “ኤሳ ዋን” አቋቁሞ በያመቱ ውርደቱን እያተሸከመ ይገኛል። አንዳንድ ሁኔታውን ጠንቅቀው የሚያውቁ ሰዎች እንደሚናገሩት “ኤሳ ዋን” ዘፋኞንች ጭምር በገንዘብ እየደለለ በማቅረብ ነጻ ምግብና መጠጥ እያደለ ሁሉም ነገር በነጻ ሆኖ ታዳሚና ተመልካች ማጣቱ አላሙዲን በጣም ያበገነው ቢሆንም ዝግጅቱ ተጨማሪ የገቢ ምንጭ የሆነላቸው ሁለቱ ወንድማማቾች አብነትና ብስራት የመጣው ቢመጣ መቀጠል እንዳለበት የተሳሳተ ምክር እንደሰጡት ይናገራሉ።

የዘንድሮው ዝግጅት ላይ የዲሲ ግብረ ኃይል ሁልጊዜ እንደሚያደርገው ተቃውሞውን እንደሚያደርግ በለቀቀው ቪዲዮ አሳውቋል። በቪዲዮም ላይ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን የተለመደ ተሳትፏቸውን እንዲያሳዩ ጠይቋል።