ሰማያዊ ፓርቲ በገዢው መደብ ጫና የባህርዳሩን ስብሰባ አስረዘመው።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ ማሳሰቢያ
ሰማያዊ ፓርቲ በሰኔ 26 2008 በባህርዳር ከተማ በሙሉአለም አዳራሽ ሊያደርግ የነበረውን የአባላትና የደጋፊዎች ውይይት በአምባገነኑ የህውኃት ሴራ ምክንያት ከአስር በላይ አመራሮችንና አባላትን እንዲሁም የቅስቀሳ መኪናዎችንና መሳሪያዎችን በማሰር ቅስቀሳ ማድረግ አትችሉም፣ አዳራሹ ቢፈቀድም ጸጥታ ማስከበር አንችልም በሚል ተልካሻ ምክንያት አምባገነናዊ ስልቱን እየቀያየረ በመሆኑ የነገውን ህዝባዊ ውይይት ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን ለህዝባችን እያስታወቅን የባህርዳር አካባቢ ህዝብና የፓርቲው አባላት በኢሕአዴግ የአፈና ሴራ ትግላችን የማይቋረጥና የማይጨናገፍ መሆኑን አውቃችሁ በሰማያዊ ፓርቲ ጥላ ስር መሰባሰባችሁንና መደራጀታችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ እናሳስባለን፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ
ሰኔ 25 ቀን 2008