ወጣቱ የዓረና ኣባል ዝናቡ ሃይሉ(ሰንችሪ) ተገደለ።ዓረና ከተመሰረተ በኋላ የተገደሉ ሰለማዊ ታጋዮች 4 ደርሰዋል።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።

ወጣቱ የዓረና ኣባል ዝናቡ ሃይሉ(ሰንችሪ) ተገደለ።
የዓረናው ኣባል ወጣት ዝናቡ ሃይሉ ( ሰንችሪ) ትናንት 24 / 10 / 2008 ዓ/ም በሚሰራበት ኩርማዓጋ በሚባል የዓፋር ቦታ (መቐለ _ኮምቦልቻ የባቡር ጣብያ ግንባታ መስመር) በመስራት ላይ እያለ ሞቶ ተገኝተዋል።
ዝናቡ ከመሞቱ በፊት እስከ ምሳ ሰዓት በሙሉ ጤናው እየሰራ የነበረ ሲሆን ከ5 የስራ ባልደረቦቹ ምሳ ከበሉ በኋላ ሂወቱ ሊያልፍ ችለዋል።
ከወጣት ዝናቡ ሃይሉ(ሰንችሪ) የግድያ ወንጀል በተያያዘ 5 ሰዎች በተጠርጣሪነት ተይዘው ዓዲ ጉደም ፖሊስ ጣብያ ታስርው ይገኛሉ።
ወጣት ዝናቡ በሕንጣሎ ወጃራት የዓረና ኣደረጃጀት እንዲጠናከርና ወደ ሌሎች ኣከባቢዎች እንዲሰፋ ከፍተኛ ኣስተዋፅኦ ያደረገ ጠንካራ ኣባል ነበር።
ግድያው ለማጣራት ሬሳው ወደ መቐለ ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል ተወስዶ በዶክተር የታየ ቢሆንም ውጤቱ ለፖሊስ ኮምሺን እንጂ ለናንተ ኣናሳይም በሚል ምክንያት የግድያው ውጤት ሳይታይ ቀርተዋል።
ወጣት ዝናቡ በምርጫ 2007 ዓ/ም በነበረው ከፍተኛ ኣስተዋፅኦ ምክንያት በተደጋጋሚ ታስሮ ነበር። ኣንድ ግዜም የድብደባ ወንጀል ተፈፅሞበት ነበር።
ዝናቡ ሃይሉ(ሰንችሪ) በሕንጣሎ ወጅራት ወረዳ ፀሓፍቲ ቀበሌ ፀሓፍቲ በተባለ ጎጥ የተወለደ የ35 ዓመት ወጣት የዓረና ኣባል ነበር።
ዓረና ከተመሰረተ 2000 ዓ/ም በኋላ የተደደሉ ሰለማዊ ታጋዮች 4 ደርሰዋል።
1) ኣረጋዊ ገብረዮውሃንስ
2) ልጃለም ካልኣዩ
3) ታደሰ ኣብረሃ
4) ዝናቡ ሃይሉ(ሰንችሪ) ተገድለውብናል።
መንግስት ሰለማዊ ስትራተጂ መርጠው በሰለማዊ መንገድ የሚታገሉ የዓረና ኣባላት ማሳደድ፣ መደብደብ፣ ማንገላታት፣ ማሰርና መግደል ያቁም።
ለትግል ጓዳችን ዝናቡ ሃይሉ(ሰንችሪ) እግዝኣብሄር ነብሱ በገነት ያኑርልን።
መላ ቤተሰቦቹና የትግል ጓዶቹ ፅናት ይስጠን።
ነፃነታችን በእጃችን ነው።
it is so.
