የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት ሪያድ ሳውዲ አረቢያ አላማውን የሳተ ስልጠና


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት ሪያድ ሳውዲ አረቢያ አላማውን የሳተ ስልጠና

ሰሞኑን የኢትዮጵያ አለም አቀፍ ት/ት ሪያድ ሳውዲ አረቢያ ስልጠና ወይስ ስይጠና በሚያሰኝ መልኩ ለ አምስት ቀናት ሲሰጥ የነበረ ሲሆን እኔም እዛው ሆኜ ስልጠናውን ስከታተል ቆይቻለሁ ስለሆነም የተቻለኝን አጠር ያለች እይታዬን ላጋራችሁ ወደድኩ

የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት መምህራንና ሰራተኞች በኢትዮጵያ የትምህርት ፖሊሲ እና ተዛማጅ የስርዓተ ትምህርት መርሆዎች በተካሄደው ስልጠና ዙሪያ አንዳንድ የራሴ የሆኑ እይታዎችን በኔ እምነት መሞጫጨር አስፈላጊ ሆኖ ታየኝ
ሥልጠናውን በተመለከተ አጭር እይታዬ የሚከተለው ይሆናል
1ኛ ፡ አሰልጣኝ አቶ አይሸሹም መኮንን ሊመሰገን በሚችል መልኩ ስልጠናውን መስጠት ችለዋል ለዚህም ምስጋናዬ የላቀ ነው
2ኛ፡ ት/ት ቤቱ እንደሌላው ተቋም ሁሉ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ያሉበት ሆኖ ሳለ በሁለተኛው አሰልጣኝ በኩል የቀረቡ ፖለቲካ አዘል ትምህርቶችን በተመለከተ :-
ሥልጠናው አላማውን የሳተ ስለመሆን የሚከተሉትን ማሳያዎች መጥቀስ እወዳለሁ
• አሁን ባለው የት/ት ቤቱ የማናጅመንት እና መምህራን የጎንዮሽና የአግድም መናበብ ደስ ያላሰኛቸውን ወገኖች ለማስደሰት የተዘጋጀ መሆኑ
• አንዳንድ የስልጣን ጥማት ያሰከራቸው የት/ት ቤቱ መምህራን አቻ ጓደኞቻቸውን በኢምባሲው በኩል በማስጠራት የስልጣን ጥማታቸውን ለመጎንጨት ማሰብ
• በዋናነት የኮሚኒቲ ማህበረሰብን ግንኙነት ሊያውክ በሚችል መልኩ መቀረጹ ለዚህም ኮሚኒቲው ውስጥና ሃገራችን ላይ እንቁ የሆኑ መምህራንን አረብ ሃገር ብቻ በመኖራቸው ምክንያት እውቀት የላቸውም እኛ ዶ/ር ነን እናውቅልሃለን ከሚል እሳቤ በቅጡ የሳኡዲ የት/ት ሚኒስቴር መተዳደሪያ እና ደንብ እንዲሁም የሃገራችንን የት/ት ስርአት ያላነበቡ ብቻ እራሳቸውን ከማስተዋወቅ አኳያ ሲለፉ የነበሩ ግለሰቦች የታዩበት
• ይህን ማህበረሰብ የጥላቻ መንፈስ እንዲያዳብር እርስ በርስ ከመከባበር ይልቅ መናናቅ ላይ መሰረት ያደረገ ምሳሌዎችን ሲያቀርቡ እንደነበረ ሃቅ ነው ለዚህም የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አጭር መምህር ተነስተው የተወረፉበት
• ስለ አንድ ለአምስት የጥርነፋ አወቃቀር መጠቀም አግባብነት መደስኮሩ
• የውጪ ዜጎች ጭምር ትዝብት ውስጥ ያስገባ የሰአት አጠቃቀም የነበረበት
• ስልጠናው ቀድሞውንም ታስቦበት እና ታቅዶበት ያልነበረ መሆኑ ለዚህም ግማሽ ያህሉ መምህራን ወደ ሃገር ቤት የተሳፈሩበት ሁኔታ መኖሩ
• እንደሚታወቀው አሁን ባለው የሳኡዲ አረቢያ የአየር ሁኔታ 45 ዲግሪ ሴንቲግሬድ እና በላይ በሆነበት ሁኔታ የሙስሊም መምህራንን የጾም አቅም ያላገናዘበ የሰአት ቆይታ መደረጉ
• ሌላው ግርም የሚለው ነገር “ የራሷ እያረረ የሰው ታማስላለች “ እንደሚባለው ሃገር ውስጥ ያለውን የት/ት ስርአት በትንሹ ለማሳየት ያክል
o በቅርቡ የ12ኛ መልቀቂያ ፈተና መሰረቅ
o ከ 4 አመት በፊት የአዳማ ዩኒቨርሲቲ ወንድ ተማሪዎች “crazy day” ብለው ከሰብአዊነት ደረጃ ዝቅ በሚያሰኝ ሁኔታራቁታቸውን ከነ ብልቶቻቸው የታዩበት ትእይንት ለዚህም ማጣቀሻ ይሆን ዘንድ እነዚህን ማስፈንጠሪያዎች ጠቅ አድርጉልኛማ https://dawitworku.wordpress.com/2012/05/17
https://www.youtube.com/watch?v=uuJm5xF-61w

o በአሁኑ ጊዜ ዩኒቨርሲቲዎቻችን የተማረ መሳይ ትውልድ የሚያመርቱበት እናም የት/ት ጥራቱ እጅጉን ያሽቆለቆለበት ሁኔታ ለዚህም ማስረጃ ይሆን ዘንድ ትውልዱ ከት/ት ይልቅ ዳንሰኛ ፣ ሙዚቀኛና ሞዴል ለመሆን ግብ ግብ የተያያዘበት
o ተቋማት አዲስ ተመርቀው ለሚወጡ ተማሪዎች በክህሎት ማነስ ምክንያት የስልጠና በጀት የሚያወጡበት በዚህም የሃገር ሃብት ያላስፈላጊ ቦታ ላይ ብክነት
o በየዩኒቨርሲቲው ለማየት እንደሚቻለው ቡና ቤቶች እንደ አሸን የፈሉበት ብሎም ሴት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቀን ቀን ተማሪ ማታ ማታ ደግሞ ሴተኛ አዳሪዎች የሆኑበት ለዚህም ማጣቀሻ ይሆን ዘንድ እነዚህን ማስፈንጠሪያዎች ጠቅ ብታደርጉልኝ ደስታዬ የላቀ ነው http://www.ojcmt.net/articles/24/242.pdf
http://www.addisstandard.com/2011/africa/category.php?fn_mode=fullnews&fn_id=151
እነዚህንና መሰል ችግሮች ከግምት ውስጥ ማስገባትና ከመፍታት ይልቅ እዚህ ተልካሻ የፖለቲካ ጥቅም ፍለጋ መምጣት አግባብ ነው ብዬ አላስብም መጀመሪያ ቤትን አጽድቶ ነው የሌላው ቤት ማጽዳት የሚቻለው በተረፈ ሊሰጡን ያሰቡትን ባለ አንድ መቶ ቅጠል ወረቀት ላይ የሰፈረ ስትራቴጂ እቅድ እናንተው ጋር ያለውን ችግሮች ለመፍታት ትጠቀሙበት ዘንዳ እየተማጸንኩ
በስተመጨረሻም ስልጠናው አላማውን የሳተ በአንጻራዊ ሰላማዊ የነበረውን የግንኙነት መስመር ለማዋከብ ብሎም መተማመን እንዳይኖር ለማድረግ እናም በተወሰነ መልኩ ት/ት ቤቱ ላይ የስልጣን ጥማት ያላቸውን ግለሰቦች ለማርካት የታሰበ እንጂ ከዚህ የዘለለ አላማ እንዳልነበረው ለመረዳት ችያለሁ::

አመሰግናለሁ