ተደጋጋሚው እብደት ፦ ዜጎች በጨለማ እየኖሩ ኤሌክትሪክ ለጎረቤት ኣገር መሸጥ ያሳፍራል። በዜጎች ላይ የሚፈጸመው ሕገወጥ ደባ ነው። ‪


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


#‎Ethiopia‬ ተደጋጋሚው እብደት ፦ ዜጎች በጨለማ እየኖሩ ኤሌክትሪክ ለጎረቤት ኣገር መሸጥ ያሳፍራል። በዜጎች ላይ የሚፈጸመው ሕገወጥ ደባ ነው። ‪#‎MinilikSalsawi‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ከዚህ ቀደም የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የወያኔው ኣገዛዝ ለጎረቤት ኬንያ በስድስት ወር ውስጥ የሸጠው መብራት ሰላሳ ኣምስት ሚሊዮን ብር ሲያተርፍ በሃገር ቤት መብራት ተቋርጦባቸው ስራ ካልሰሩ ፋብሪካዎች ለሃገሪቱ ያስገባሉ ከተባለው ውስጥ ስድሳ ሚሊዮን ብር ብር ኪሳራ ደርሳል። ይህን መመዘን የኣንባቢ ድርሻ ሲሆን ባለፉት ቀናት ኬንያ የቆየው የወያኔ ኣሻንጉሊት ሃማደ ገልፋጩ የኣራት መቶ ሜጋ ዋት ሓይድሮ ፓወር ለኬንያ ለመሸጥ ውል ፈርሞ ኢትዮጵያውያንን በጨለማ በማሳደር የሃሰት ፕሮፓጋንዳውን እየነዛ ጎረቤቶቻችንን ኣድምቆ ለማኖር ቃል ገብቶ ተመልሷል፤ ይህ ኣገዛዝ ለዜጎቹ ደንታ ቢስ መሆኑን የሚያመለክት ሲሆን ከስልጣን እስካልተወገደ ድረስ በፍጹም ለውጥ እንደማያመጣ ከበፊቱ የተረጋገጠ ነው።

Minilik Salsawi's photo.

ይህ በወያኔ ኣገዛዝ የሚፈጸም ተደጋጋሚ እብደት ዜጎች የሚፈልጉትን የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሳያሟላ ለጎረበት ኣገር መሸጥ ለሕዝብ ያለውን ንቀት ያሳያል።እንዲሁም እንደፈለገ ወደ ኬንያ ምድር እየገባ የሚያፍናቸውን ለኣገዛዙ ተቃዋሚ የሆኑ ዜጎችን የበለጠ ለማፈን ይረዳው ዘንድ የኬንያን ኣገዛዝ ለማለሳለስ ይጠቀምበታል።ይህ የመብራት መሸጥ ጉዳይ በኬንያ ብቻ ሳይሆን ለሱዳን ለጅቡቲ ለሰሜን ሱማሊያ እና እስከ ታንዛንያ የተስፋፋ ነው።በዜጎች ላይ የሚፈጸመው ሕገወጥ ደባ መሆኑ ኣይካድም።

በሃገር ቤት የሚገኙ ፋብሪካዎች በሃይል እጥረት ኪሳራ ላይ ሲወድቁ ሰራተኞቻቸውን ሲቀንሱ ሕዝብ ለድህነት ሲዳረግ የወያኔ ባለስልጣናት የኤሌክትሪክ ሃይል ኀጠው የሚያገኙትን ዶላር ወደየ ግል ኣካውንታቸው ያዘዋውራሉ።ምንሊክ ሳልሳዊየኣፍሪካ ሕብረት መቀመጫ እና የኣስር ሺዎች ዲፕሎማቶች ከተማ የሆነችው አዲስ ኣበባ በጨለማ ማስዋጥ ኣገዛዙ የሚሰራው ሕገወጥ ተግባር ሽፋን መስጫ ነው። ተማሪዎች ከትምህርት ጥራት በደል በተጨማሪ የኤሌክትሪክ ሃይል እጥረት በፈጠረው ጨለማ ውስጥ ማጥናት ኣሊያም መማር ስለማይችሉ በቂ እውቀት ማካበት እየከበደ መጥቷል። እናቶች በሃይል ማጣት እንዲሁም በማገዶ እጥረት ያቦኩትን ሊጥ ተበላሽቶ እስከመድፋት ሲደርሱ የመንግስት ስራ በደል የባንክ ሲስተምን አበላሽቶ በኪሳራ የምትኖረዋን ኣገር ለኪሳራ ዳርጓል።ይህ ተደጋጋሚው እብደት ፦ ዜጎች በጨለማ እየኖሩ ኤሌክትሪክ ለጎረቤት ኣገር መሸጥ ያሳፍራል። በዜጎች ላይ የሚፈጸመው ሕገወጥ ደባ ነው። የወያኔ ኣገዛዝ እስካልተወገደ ድረስ ዜጎች ሰላም እና እድገት ኣይኖራቸውም።‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬