እሱ ማነው ? (ይድነቃቸው ከበደ)
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
እሱ ማነው ? ——- “አቶ መለስ ዜናው በመተማ መሬት በምክር ቤት የሞገተ፣ እሱ ባሲያዘው አጀንዳ የውሳኔ ሃሳብ በማቅረብ ከአቶ መለስ ጋር ከፍተኛ ክርክር በምክር ቤት ካደረጉት መካከል አቶ ተመስገን ዘውዴ ይገኙበታል” ——— በ1997 ዓ.ም የህዝብ እንደራሴ በመሆን ቅንጅትን በመወከል በተወካዮች ምክር ቤት አባል ነበር ።
የቅንጅት መፍረስ ተከትሎ፣አንድነት ፓርቲ ሲመሰረት ፣የፓርቲው አባል በመሆኑ የሚጠበቅበትን ግዴታ ሲወጣ ቆይቷል።ይሁን እንጂ አንድነት ፓርቲ ውስጥ በተፈጠረው መከፋፈል ከፓርቲው እራሱን ያገለለ ሲሆን፣ የሰማያዊ ፓርቲ መስራች አባል በመሆን ፣ታህሳሥ 22 ቀን 2004 ዓ.ም ሰማያዊ ፓርቲ ምስረታዉን በይፋ ባካሄደበት ወቅት፣የሰማያዊ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል ሆኖ ተመረጠ።
ለእስር እስከ ተዳረገበት ጊዜ ድረስ የሰማያዊ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል እና የሰሜን የጎንደር አስተባባሪ በመሆን ፣ከፓርቲው የተሰጠውን ኃላፊነትና ግዴታ በአግባብ ሲውጣ የቆየ ትጉህ ጓድ ነው። እሱ ፣እጅግ በጣም ሲበዛ ትሁት እና ሰው አክባሪ ነው። ስለ-እሱ እሱን የሚያውቁት ሁሉ ይህን እውነታ ይመሰኩርለታል።ሰው አክባሪነቱና ትህትናው በሚያመቸዉ ቦታ እና ጊዜ ብቻ ሳይሆን የትም ለማንም ነው። ያለውን ለማካፈል የእሱ መስፈርት፣ የእሱ ኪስ ባዶ አለመሆኑን ብቻ ነው።
ከእድሜው በላይ የአስታዋይ ሽማግሌ ባህሪና ሥራ አብዝቶ ይታይበታል፣ ለዚህም ነው በ23 ዓመቱ በሰሜን ጎንድር ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ የህዝብ እንደራሴ ሆኖ የቅንጅት ተወካይ የሆነው። እሱ ልጅ ሆነ በ9 ዓመቱ የእነሱን ሰፈር አልፉ አዲስ አበባ የገባው ፣ አምባገነኑ የውያኔ ስብስብ፣ ለመቃውም የልጅነቱ ጊዜ ጨርሶ ፣ የወጣትነት ዘመኑ በጀመረ ማግስት ነው። ተፈጥሮ ካደለችው እሱም አጥብቆ ከያዘው የሰው ሰውኛ መልካም ባህሪ በተጨማሪ ፣ በትምህርቱ የሕግ ተመራቂ ነው። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በነበረው ቆይታ፣የአገዛዙ ስርዓት ዋና መሪ የሆነት ሟቹ አቶ መለስ ዜናው፣ በመተማ መሬት በምክር ቤት የሞገተ እሱ ነው። እሱ ባሲያዘው አጀንዳ የውሳኔ ሃሳብ በማቅረብ ከአቶ መለስ ጋር ከፍተኛ ክርክር በምክር ቤት ካደረጉት መካከል አቶ ተመስገን ዘውዴ ይገኙበታል።
ይሄን ጉዳይ አስመልክቶ የሆነውን ሁሉ ምስክርነታቸውን መስጠት ይችላሉ። በወቅቱ ሪፖርተር ጋዜጣ በፊት ገጹ፣ የአቶ መልስ ዜናዊ እና የሰሜን ጎንድር ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ የህዝብ እንደራሴ የሆነዉ ፎቶ በመያዝ፤ ስለ መተማ መሬት ሰፊ ዘገባ ይዞ ቀርቦ ነበር ፣የጋዜጣው ሚዛናዊነት ማጋደሉ እንደተጠበቀ ሆኖ እንዳለ። እሱ ፣የአገዛዙ ስርዓት እንዲለወጥ እስከ-ታሰረበት ጊዜ ድረስ ለ9 ዓመት ያህል በሰላማዊ መንግድ ፤ በቅንጅት ፣ በአንድነት እና በሰማያዊ ፓርቲ የሚቻለዉን ሁሉ አድርጓል ። ይህ ጽሑፍ ለንባብ እስከ በቃበት የእስር ዘመኑ ፣ባጠቃላይ ለ11 ዓመት ያህል ፣ በአገር ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ መስል የትግል አጋሮቹ ጋር በመሆን የአገዛዙን ሥርዓት ጠበንጃ አልባ በሆነ ትግል፤ በሰላማዊ መንገድ ሲገጥም ቆይቷል። አሁን ለእስር ከተዳረገ አንድ አመት ከ7 ወር ሆኖታል። የአገዛዙ ስርዓት ማሰቃያ ቦታ በሆነው መዓከላዊ እስር ቤት ለ5 ወር አስቸጋሪውንና ፣ችግሩ ይሄ ነው ተብሎ ለመግለፅ የሚክብድውን የስቃይ ጊዜ ያሳላፍ ሲሆን፣አሁን ደግሞ በቃሊቲ የማጎሪያ እስር ቤት ይገኛል። ይህ ሰው፣ አሁን ላይ ለእስር የተዳረገው ” የአርበኞች ግንቦት ሰባት ፣ዓላማና ተልእኮ ማስፈጸም ” የሚል ክስ ቀርቦበት ነው።
የገዢው ስርዓት አስመሳይ የሕግ ሽፍን በመስጠት ፣የነፃነት ታጋዮችን በፍርድ ቤት አቅርቦ ለእስርና ለስቃይ የሚዳርገው አቃቤ ህግ፤በእዚህ ሰው ላይ ያቀረበው ክስ፤ 1ኛ.”ቀኑና ወሩ በትክክል ተለይቶ ባልታወቀበት በ2006 ዓ.ም አማረ ሽፈራው በተባለ የሽብር ድርጅት ተወካይ፣ስልጠና ለመውሰድ እና ተልእኮ ለመፈጸም መስማማቱ። 2ኛ.ቀኑ በትክክል ተለይቶ ባልታወቀ በጥር ወር 2006 ዓ.ም ከኢሳት ጋዜጤኛ መሳይ መኮንን ጋር (የኢትዮጵያ መንግሥት በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉትን፣ እያሰረና እያሰቃየ ነው) በማለት ከሽብር ድርጅት አባል ከሆነው ከመሳይ መኮንን ጋር ቃለ መጠይቅ በማድረጉ። 3ኛ.በየካቲት ወር 2006 ዓ.ም (ኢትዮጵያ ውስጥ በሰላማዊ መንግድ መታገለ አይቻልም፤ የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን መንግሥት ተሰጥቷል) በማለት በኢሳት ተናግሯል የሚል ክስ ነው የቀረበበት።
ክስ አቅራቢዎቹ በእዚ ሰው ላይ ምንም አይነት የሰው ማስረጃ ወይም ምስክር ማቅረብ አልቻሉም ፣አለን የሚሉት የሰነድ ማስረጃ ማቅረብ አለመቻላቸው ብቻ ሳይሆን ፤ ከጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ጋር ቃለ መጠይቅ ማድረግ የሽብር ተግባር መሆኑ የአገዛዙ ልኬልሽ አምባገነናዊ ስርዓት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው። አዎ ኢትዮጵያ ውስጥ በሰላማዊ መንገድ መታገል ፣ ሕይወትን ያሳጣል ፣ለእስር እና ስቃይ ይዳርጋል! ይህን ማለት ሳይሆን፣ ይሄን ቀፋፊ ተግባር መፈጸም ነው ሽብር የሚሆነው። ይሁን እንጂ እነ ሽብሩ ሰላማዊ የነፃነት ታጋዩን አሸባሪ ብለው ከሰሱት። እሱ፣ “የታሰርኩት የመተማ መሬት ለሱዳን መሸጡን በመናገሬ ነው፡፡ ትናንትም መሬቱ መሸጡን ስናገር ቆይቻለሁ፡፡ ወደፊትም እናገራለሁ፡፡ የተከሰስኩት በመሬቱ ጉዳይ ነው እንጅ አሁን የተከሰስኩበትን ወንጀል ፈጽሜ አይደለም፡፡” ሲል የእምነት ክህደት ቃሉን በፍርድ ቤት ፤ በሚገርም ወኔ በልበ ሙሉነት ቃሉን ሰጥቷል፡፡ በወቅቱ በፍርድ ቤት በመገኘት ይህን ለመታዘብ ችያለው። ግንቦት 11/2008 ዓ.ም ፍርድ ቤት በቀረበበት ጊዜ የቂሊንጦ እስር ቤት አስተዳደር ግፍ እያደረሰብኝ ነው፣ በማንነቴ ላይ በደል እየተፈጸመብኝ ነው ፣ እኔ ዘረኛ አይደለሁም ግን ፍጹም ዘረኛ በሆነ በማንነቴ ብቻ እያሰቃዩኝ ነው። በማለት አቤቱታ አሰምቶ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ‹‹ጨለማ ቤት እናስገባሃለን›› እያሉ እንደዛቱበትም በወቅቱ ገልጾ ነበር፡፡
እንዳለው ሆነና ግንቦት 17/2008 ዓ.ም ጀምሮ በሚታሰብ የሁለት ወራት ጨለማ ክፍል እስር ቅጣት አስተላልፈውበታል፡፡ ከግንቦት 17 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ ይህ ጽሑፍ ለንባብ እስከ በቃበት ድረስ፤ ቂሊንጦ በሚገኘው ጨለማ ክፍል ውስጥ ይገኛል።በቂሊንጦ ሁለት ጨለማ ክፍል የሚገኝ ሲሆን፣ እሱ የሚገኝበት ክፍል ከእሱ ውጪ የፖለቲካ እና የህሊና እስረኛ የሌለ ሲሆን ፣እጅግ በጣም አደገኛ የሆኑ ወንጀለኞች የሚቀጡበት ክፍል ነው። በጨለማ ክፍል ውስጥ ከመታሰሩ በተጨማሪ በማንም እንዳይጠየቅ ክልከላ ተደርጎበታል።ከፍተኛ የሆነ ድብደባም እየተፈጸመበት እንደሆነ ከውስጥ የሚወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ። ይህ ሰው ጨለማ ክፍል ውስጥ ከመግባቱ በፊት ፣ በእስር ቤት ሄደዉ ለሚጠይቁት ሁሉ ፣ ስለ ሰማያዊ ፓርቲ አውርቶ አይጠግብም ፤ “አደራ ፓርቲያችን ጠብቁ” በማለት ተማጽኖ ጭምር የማይለየው የእሱ የሁል ጊዜ ትልቁ መልእክት ነው። ሰኔ 13 ቀን 2008 ዓ.ም በተከሰሰበት ክስ የመጨረሻ ብይን እንደሚሰጥ በፍርድ ቤት ቀጠሮ ተይዟል ። ሰኔ 13 ቸር ወሬ ፈጣሪ ያሰማን ፣አሜን።ይህ ሰወ አግባው ሰጠኝ ይባላል!!! (ይድነቃቸው ከበደ)