በጾረና ግንባር በተደረገ ጦርነት ከ200 በላይ ገድዬ ከ300 በላይ የሕወሓት ወታደሮችን አቁስያለሁ ሲል የሻእቢያ መንግስት ኣስታወቀ።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በጾረና ግንባር በተደረገ ጦርነት ከ200 በላይ ገድዬ ከ300 በላይ የሕወሓት ወታደሮችን አቁስያለሁ ሲል የሻእቢያ መንግስት ኣስታወቀ።
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) የሻእቢያ የማስታወቂያ ሚኒስቴር በዛሬው እለት በለቀቀው መግለጫ ከወያኔ ሰራዊት ጋር በጾረና ግንባር ከእሁድ እስከ ሰኞ ጠዋት ባደረገው ውጊያ ከ200 በላይ የወያኔ ወታደሮችን ገድሎ ከ300 በላይ ማቆሰሉን በመግለጫው ኣትቷል።መግለጫው እጅግ በርካታ መስዋትነት የተከፈለበት ያለው ይህ ጦርነት የወያኔ ወታደሮች ከነበሩበት ቦታ በማፈግፈግ መሸሻቸውን ጠቅሷል።
ይህ ደም ኣፋሳሽ ጦርነት ለምን ተካሄደ በምንስ ምክንያት ለምንስ ኣላማ ሲል የጠየቀው መግለጫው ራሳቸው ወረውን ራሳቸው ጉዳተኛ ሆነው እፍረትን ተከናንበዋል ብሏል፤ ለመሸፋፈን ቢሞክሩም ተጋልጠዋል ሲል ሚኒስቴሩ ጽፏል።ከፍተኛ የፖለቲካና ዲፕሎማቲክ ኪሳራ ተከናንበዋል ሲል ማስታወቂያ ሚኒስቴሩ ኣስቀምጧል።#ምንሊክሳልሳዊ
