ወያኔ በዳባት ህዝብ ላይ ጦርነት ከፍቷል:: (VIDEO)


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ወያኔ በዳባት ህዝብ ላይ ጦርነት ከፍቷል:: ዳባት ከተማ ከቀላል እስከ ከባድ መሳሪያ በታጠቁ ቅልብ የወያኔ ልዩ ሃይልና በፌደራል ሃይል ተወራለች።
በዛሬው እለት ከፍተኛ ድብደባ ጉዳትና እስር በህዝቡ ላይ እየተፈፀመ ነው።በጥይት የቆሰሉ አሉ።ብዙ ወጣት ታስሯል…የተወሰኑትን ስም ዝርዝር ይዘናል…
[youtube http://www.youtube.com/watch?v=qzCTIDQ2X6g]
ትናንት በነበረው ስብሰባ የዳባት ወጣት ግልብጥ ብሎ ወደ አዳራሹ በመግባት መፈክር አሰምቷል በአዳራሹም መፈክር ለጥፏል። 25 አመት ያለ መንግስት ኖረናል አሁንም አንፈልጋችሁም ሂዱልን። ወያኔ ሌባ። ዳባት የጠላት ግንባር ብላችሁ ለስቃይ ዳረጋችሁን።ባቅራቢያው ያለችው የደባርቅ ህዝብ በነገው እለት ሰልፍ በመውጣት ለዳባት ህዝብ ድጋፉን እንዲገልፅ ወረቀት ተበትኗል። ውጥረቱ በጣም ተባብሷል።የጎንደር ከተማ ህዝብ በቅርብ እየተከታተለው ነው። የወገኑን ጥቃት አይፈቅድም ጎንደሬ ጥንትም ሆነ ዛሬ።የታሰሩና በጥብቅ ክትትል ስር ያሉ የዳባት እንቁ ልጆች የሚከተሉት ናቸው ልንታደጋቸው ይገባል… መታሰራቸው የታወቀ
1.ታጠቅ በቀለ
2.ጥላሁን አደመ
3.ፍሲል ደጌ ናቸው።
በጥብቅ የሚፈለጉ፦
1.ሚኪያስ ንጉሴ
2.ግርማቸው መስፍን
3.ይርጋ አለሙ
4.ፍትህአለው አረጋዊ
5.ተስፍሁን በጋሻው
6.ዬናስ አበበ
7.አስፍውወሰን መስፍን
8.ሸጋው ውበት
9.አምሳሉ አየልኝ እና ሌሎችም