በምርጫ 2007 ታፍሰው 11 ወር በስልጠና ስም አፋር አሚባራ እስር ቤት የቆዩ ወጣቶች በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ተገኝተው መግለጫ ሰጡ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በምርጫ 2007 ታፍሰው 11 ወር በስልጠና ስም አፋር አሚባራ እስር ቤት የቆዩ ወጣቶች በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ተገኝተው መግለጫ ሰጡ

ጎንታናሞ በኢትዮጵያ Yidinekachew kebede

ህዝባዊ ተቀባይነት የሌለው የህወሓት የኢህአዴግ አምባገነን መንግሥት በዜጎች ላይ የሚያደርሰው መንግስታዊ በደል አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡ የ2007 አገር አቀፍ ምርጫ ተከትሎ 16 ሺህ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያንን በግዳጅ በማፈስ ስፍራው ወዳልታወቀ ቦታ መሰወራቸው የሚታወቅ ነው፡፡የህዝብ ጥቆማና ጥያቄ እያየለ በመጣበት ወቅት መንግስት ጉዳዩን ለማለዘብ ፣በጎዳና ላይ የሚገኙ ሥራ ፈቶችን ነው ሰብስቤ ወደ-ማሰልጠኛ ያስገባሁት፣ በማለት ማስተባባያ መስጠቱ ይታወሳል፡፡ይህ የተባለው ቦታ በአፋር ክልል ውስጥ በሚገኘው አሚባራ አካባቢ ነው፡፡

ይሁን እንጂ ዛሬ ጠዋት ከ250 እስከ 300 የሚሆኑ ወጣቶቹ ተሰባስበው እንደገለጹት ከሆነ፣ በሚታፈሱበት ወቅት የሰማያዊ ፓርቲ ደጋፊዎች ናችሁ፣ፓርቲው በከተማ ውስጥ ለሚፈጥረው ግርግር ያዘጋጃችሁ ናችሁ እየተባልን ፣በግዳጅ እንደታፈሱ የተናገሩ ሲሆን፡፡ለ11 ወራት ከፍተኛ የሆነ እንግልት እና ስቃይ ይደርስባቸው እንደነበር አክለው ተናግራዋል፡፡በማጎሪያ ካንፕ ውስጥ በነበራቸው ቆይታ የተለያየ ስልጥና የተሰጣቸው ቢሆንም መንግስት በገባው ቃል መሰረት አሰልጥኜችዋለሁ ባለው ሙያ አልቀጠራቸውም፡፡ሰልጣኞቹ ለምን አልተቀጠርንም በማለት ለሚጠይቁት ጥያቄ የተሰጣቸው ምላሽ፣ በተለያየ የመንግስት መስሪያ ቤት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት መቅጠር አንችልም በማለት መልስ የሰጣቸው ሲሆን፣በስልጠና ላይ በነበሩበት 11 ወር ውስጥ ከፍተኛ ስቀይና መከራ እንደደረሰባቸው በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ተገኝተው ለጋዜጠኞች ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ሰልጣኞቹ የደረሰባቸውን በደል መንግስታዊ ለሆኑ አካላት ፣ችግራቸውን ለማመልከት በሄዱበት ቦታ ሁሉ በፖሊስ እንዲሰደዱ ተደርጓል፡፡በተለይ እንባ ጠባቂ ተቋም ሄደው ሲያመለክቱ በደህንነቶችና በፖሊሶች ከፍተኛ የሆነ ወከባ እና ድብደባ የተፈጸመባቸው ሲሆን ፣እራሳቸውን ለማዳን የሸሹ ከ250 የማያንሱ ወጣቶች ሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በመገኘት እራሳቸውን ከጥቃት ለመከላከል ጥረት አድርገዋል፡ወጣቶቹ እንደገለጹት እዛ በነበሩበት ወቅት ለሚያነሱት የመብት ጥያቄ ፣ማሰልጠኛ የሚል ስም በተሰጠው የማጎሪያ ካንፕ ውስጥ እስካሁን በእስር ላይ ያሉ እንዳሉም መረጃው የሚጠቁም ሆኖ በሞትም የተለዩአቸው ጓደኞቻቸው እንዳሉ በኃዘን በተጎዳ ስሜት ገልጸዋል፡፡

በተለይ የምርጫው ዕለት ማታ አቶ ገቡሩ ገብረጻድቅ የተባለ ((በበረሃ ስማቸው ጉና)) ተብለው የሚጠሩ የካንፕ ኃላፊ ወጣቶቹ በድምጽ ማጎያ እንዲጠሩ በማድርግ ፣”ወደዳችሁ ጠላችሁ ኢህአዴግ ምርጫውን አሸንፏል” በማላት ማስፈራሪያ እና ዛቻ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡የ250 ተወካዮች በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በመገኘት ለጋዜጠኞች በጉዳዩ ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

Yidnekachew Kebede's photo.