ግፈኞች ዝም ባይና ታጋሽ ሁሉ ፈሪ ይመስላቸዋል::ከንቱ ሃሳብ!!!
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
#Ethiopia ግፈኞች ዝም ባይና ታጋሽ ሁሉ ፈሪ ይመስላቸዋል::ከንቱ ሃሳብ!!! #MinilikSalsawi
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ግፈኞችና ወንጀለኞች በጥፋታቸው ላይ በዘወተሩ ቁጥር መልካም ስራ ላይ ያሉ እየመሰላቸው ዳንኪራ እየረገጡ በስህተታቸው ላይ ይገሰግሳሉ። ኧረተዉ በወንጀል ላይ ነው ያላችሁት ቆም ብላችሁ አስቡ ሲባሉ : የምን ወንጀል ባሳመርን ፣ ባስተካከልን ፣ ባለማን ……..እያሉ እራሳቸውን አስተማሪና መካሪ አድርገው በመቁጠር : በተቃራኒው ተዉ ቆም ብላችሁ አስቡ የሚላቸውን ሁሉ ወንጀለኛ አድርገውት ቁጭ ይላሉ።
ወንጀል በዘወተርክበትና በተላመድከው ቁጥር መልካም ስራ እስኪመስልህ እያጣጣምከውና እየተደሰትክበት ትቀጥላለህ። መስማት የምትፈልገው በዙሪያህ ያሉ የመሰሎችህን ንግግር ብቻ ይሆናል።….ከአንተ ሃሳብ በተቃራኒ የሆነ ሀሳብ የሚያቀርቡልህን ፣ የምትሰራውን ወንጀል የሚቃወሙህን ድምፃቸውን መስማት፣ መልካቸውን ማየት እስኪያስጠላህ ትጠላቸዋለህ ፣ ትርቃቸዋለህ ።
ዛሬ ላይ የምትጠሏቸው የምትገርፏቸው የምታስሯቸውን ብታውቁ ኖሮ ለናንተ መካሪ አማካሪ ታደርጓቸው ነበር በምክራቸውም ተጠቃሚ በሆናችሁ ነበር ።ግፈኞች ዝም ባይና ታጋሽ ሁሉ ፈሪ ይመስላቸዋል ይህ የነሱ ከንቱ ሃሳብ ነው እውነታው በተቃራኒው ነው። ጊዜ ብዙ ነገር ያሳየናል ትላንት የነበሩ አምባገኖች መጨረሻቸው ምን ያክል የከፋ እንደነበር ታሪክ ነግሮናል: እኛም በእድሜያችን የብዙ አምባገነኖችን መጨረሻ አይተናል።የዛሬዎችም አምባገነኖች የእውነተኛ መካሪዎችን ምክር ሰምተው ካሉበት የጥፋት ጉዞ የማይመለሱ ከሆነ እንደትናንት አምባገነኖች ሁሉ የዛሬዎቹም አምባገነኖች መጨረሻ ጥፋት መሆኑ ጥርጥር የለውም ።#ምንሊክሳልሳዊ