የአገር ውስጥ ቅኝ አገዛዝ ? Muluken Tesfaw
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
እሑድ ግንቦት 21 ቀን 2008 ዓ.ም. የወጣው ሪፖርተር ጋዜጣ ‹‹አገር በቀል ኮንትራክተሮች የነገሡበት የ5.6 ቢሊዮን ብር የመንገድ ግንባታ ስምምነቶች›› በሚል ርእስ ስድስት የሚሆኑ አገር በቀል ኮንትራክተሮች፣ ሰባት የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለመገንባትና ለመጠገን፣ ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ጋር ስምምነት መፈራረማቸውን አስነብቦናል፡፡ ሪፖርተር እንደገለጸው፣ ከ626 ኪሎ ሜትር በላይ ርዝማኔ ካላቸው ሰባት የመንገድ ሥራ ፕሮጀክቶች ውስጥ ሁለቱን ፕሮጀክቶች ያሸነፈው ሱር ኮንስትራክሽን ነው፡፡ የአገር ውስጥ ኮንትራክተሮች ነግሰውበታል በተባለው በዚህ የመንገድ ፕሮጀክቶች ኮንትራት ስምምነት፣ ሱር ኮንስትራክሽን ሁለቱን ፕሮጀክቶች በ3.3 ቢሊዮን ብር በላይ ለመገንባት የሚያስችለውን ውል መፈራረሙ ተገልጿል፡፡
ሱር ኮንስትራክሽን ‹‹በጨረታ›› አሸናፊ የሆነባቸውን ሁለት የመንገድ ፕሮጀክቶች፣ ማለትም በአማራ ክልል የሚገኙትን የሶሮቃ-አብረሃጂራ-አብደራፊ (92 ኪሜ) በ1.43 ቢሊዮን ብር፣ እንዲሁም ከአይከል-ዙፋን-አንገረብ ድረስ ያለውን (69 ኪሜ) መንገድ በ1.95 ቢሊዮን ብር ዋጋ እንደሚሠራ ታውቋል፡፡ ልብ እንበል፣ 5.6 ቢሊዮን ከሚያወጣው ፕሮጀክት ውስጥ ሱር ኮንስትራክሽን 3.3 የሚያወጣውን ሲረከበው፣ ለሌሎች 5 ድርጅቶች የደረሳቸው 2.3 ቢሊዮን ብር የሚያወጣው ብቻ ነው፡፡ ምን ማለት ነው?
እንደሚታወቀው ሕወሓት የፌደራሉን መንግሥት ገንዘብ (የሕዝብ ሀብት) በመጠቀም የራሱን ከበርቴዎች በመገንባት ላይ ነው፡፡ ይህን ሒደት ከሚመሩት ተቋማት መካከል የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን አንዱ እንደሆነ በግልጽ የሚታወቅ ሲሆን፣ ከትናንት እስከዛሬ ድረስ የመንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር የሚሆኑትም ትግሬዎች ናቸው፡፡ በተጠቀሰው ስምምነት መርሐ ግብር ላይ ለምሳሌ 3.3 ቢሊዮን ብር የሚያወጣውን ውል የተፈራረሙት የመንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ግርማይ እና የሱር ኮንስትራክሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ታደሰ የማነ ናቸው፡፡ ይህ ምን ማለት ነው? ገንዘቡን ከግራ ኪስ ወደ ቀኝ ኪስ ከማዘዋወር በምን ይለያል? ከእኛው ለእኛው ነው ነገሩ፡፡
ሕወሓት ለመንገድና ሌሎች መሠረተ ልማቶች ተብሎ በብድርና እርዳታ የሚገኘውን እና ከድሃው የኢትዮጵያ ሕዝብ በልዩ ልዩ መንገድ የሚሰበሰበውን ገንዘብ የትግራይን ገዥ መደብን ለመገንባት እየተጠቀመበት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገነቡ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ውስጥ በግንባታ፣ ሲሚንቶ፣ ብረትና ሌሎች የግንባታ ጥሬ እቃዎችን በማቅረብ፣ በማማከር ወዘተ. የሚሳተፉት የዚኸው ገዥ መደብ ድርጅቶች ናቸው፡፡ በሕዳሴው ግድብ ግንባታ ከቁጥቋጦ ምንጠራ እስከ ሲሚንቶ፣ ብረትና ሌሎች የግንባታ ግብዓቶች አቅርቦት፣ ከቁጥጥር እስከ ካፍቴሪያ ድረስ ያሉት እነማን ናቸው?